Cyberigna

Cyberigna

Share

07/10/2022

አለም አቀፍ የሳይበር ወር እና ታሪካዊ ዳራዉ
አለም አቀፍ የሳይበር ወር በወርሃ ጥቅምት በአለምአቀፍ ደረጃ ስለ ሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ከፍ ለማድረግ ታስቦ የሚካሄድ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መርሃ ግብር ነዉ፡፡
የሳይበር ደህንነት ወር ለመጀመሪያ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ በ2004 እ.ኤ.አ የዜጎችን የሳይበር እዉቀት ለመጨመርና ንቃተ ህሊናቸዉን ከፍ በማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀ የሳይበር አጠቃቀምን እንዲተገብሩ ታስቦ መከበር ጀመረ፡፡
ቀስ በቀስ በአዉሮፓ እና ሌሎች የአለም ሀገራት ተቀባይነቱ እየጨመረ መጥቶ፤ ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ በአዉሮፓ ሀገራት ከ2012 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መከበር ጀምሯል፡፡
የተለያዩ ሀገራት ይህን ፕሮግራም ሙሉ ወሩን አልያም ከወሩ ሳምንትን መርጠዉ እንደሚያከብሩት መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡
አዉስትራሊያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለምሳሌ ጋና፣ሳዉዝ አፍሪካ፣ ሞሪሽየስ፣ ኢስዋቲኒ፣ጋምቢያና ሩዋንዳን ጨምሮ ሙሉ ወሩን ባይሆንም ከጥቅምት ወር አንዱን ሳምንት መርጠዉ እንደሚያከብሩት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2012 ዓ/ም የመጀመሪያዉን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በሳምንት ደረጃ በጥቅምት ወር የመጨረሻው ሳምንት “ትኩረት ለሳይበር ደህንነት” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና መርሃ ግብሮችን በማካሄድ ማክበር ጀምራለች፡፡
በ2014 ዓ.ም ደግሞ “የሳይበር ደህንነት የጋራ ሃላፊነት፤ እንወቅ፤ እንጠንቀቅ” በሚል መሪ ቃል 2ኛዉን የሳይበር ደህንነት ንቅናቄ በወር ደረጃ ከ ጥቅምት 1 ቀን እስከ 30 በተሳካ ሁኔታ ለአንድ ወር ያክል በኮንፈረንስ፣ በስልጠና ብሎም በተለያዩ የሚዲያ አውታረ መረቦች ንቅናቄዎች ተካሂደዉ ነበር፡፡
3ተኛዉ የሳይበር ወርም እንዲሁ በጥቅምት 2015 አ.ም በተሳካ ሁኔታ ይከበራል፤ የወሩ አላማወች እና ዝርዝር አላማዎችም የሚከተሉት ናቸዉ
የወሩ ግብ
የሳይበር ማህበረሰቡንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ለማጎልበት የሚያስችል ንቅናቄን በማካሄድ የሃገራችንን የብሄራዊ ጥቅሞችን የማስጠበቅ ተልዕኮን ማገዝ ነዉ፡፡
የወሩ ዝርዝር አላማዎች
• የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ጥቃት ተጋላጭነት ለማሻሻል
• የግሉ ዘርፍ የሳይበር ደህንነትን በማስጠበቅ የሚኖረዉን አስተዋዕፆ ማሳደግ
• የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል የሰዉ ሃብት ልማት ላይ ንቅናቄ መፍጠር ነዉ፡፡
• የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ የሚያሳድግ ንቅናቄ መፍጠር

23/02/2022

ታዳጊዎች የኦንላየን ቴክኖሎጂን በሚጠቀሙበት ጊዜ ሊያጋጥማቸው የሚችሉ ስጋቶች ምንድናቸዉ
1. ተገቢ ያልሆነ ይዘቶች (Inappropriate content)፡ ይህም ሲባል፡-
  የወሲባዊ ይዘት ያላቸው (የህፃናት\አዋቂዎች ፖርኖግራፊ፣ ከፊል እርቃን እና \ወይም እርቃን ምስሎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መመልከት
  የዓመፅና የስቃይ ምስሎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች
  የጥላቻ ቡድኖችን የሚደግፍ የሚያበረታታ ይዘት ያላቸዉ መረጃዎች
  ህገ ወጥ ተግባር የሚያሳዩ ማስታወቂያዎች
  ጽንፈኛ ድረገፆች፤ የሽብርተኛ ድርጅቶችን፣ ቦምብ የሚሰሩ ቦታዎችን ወዘተ መረጃዎች
  አደገኛ ፀባይን የሚያበረታቱ ድረ ገጾች
  ጸያፍ ንግግሮችንና ጸያፍ ድርጊቶችን የሚጠቀሙ ይዘቶችን ያካትታል
2. የቻት ሩም "ጓደኞች" (Chat room “Friends”)
 አንዳንድ አዳኞች(predators) ወደ ቻት ሩም ወይም በማኅበራዊ ድረ ገጾች ተጠቅመው ትንንሽ ልጆችን ማግኘት ይችላሉ። በእነሱ ዕድሜ ላይ የሚገኙ መስለው በመቅረብ ጓደኛ ይሆኗቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ እንደዚህ አይነት ሰዎች በአንድ ወቅት በአካል ለማግኘት ይሞክራሉ ብሎም በታዳጊዎች ላይ ተገቢ ያልሆነ ብዝበዛ ሊፈፅሙ ይችላሉ
3. የሳይበር ጉልበተኝነት (Cyber Bullying)
በማህበራዊ ሚዲያ ድረገፆች አማካኝነት የሚደርስ የሳይበር ጉልበትኝነት (cyber bullying):- ህጻናት በማንነታቸዉ ምክንያት የሚደርስባቸዉ ዘለፋ እና ስድብ ነክ ትችት በስነልቦናቸዉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረስ አልፎ ራስን የመጥላት ብሎም ራስን የማጥፋት ስሜት ዉስጥ ሊያስገባቸዉ ይችላል
4. 4. የኦንላይን (መስመር ላይ) ማጭበርበሪያዎች (Online Scams)
ብዙውን ጊዜ በኢንተርኔት ለሚሰነዘሩ ማጭበርበሪያዎች ዋነኛ ዒላማ የሚሆኑት አዋቂ ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው ቢቆጠርም ልጆችም ለነዚህ አይነት ማጭበርበሪያዎች በጣም የተጋለጡ ናቸው። ታዳጊዎችን በሚፈልጉት እና ሊያገኙት በሚፈልጉት ነገር ጋር በማያያዝ በሀሰት ሊጭበረበሩና ለከፋ ጉዳ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡

28/12/2021

የቴሌግራም አፕ እና የደህንነት ጥንቃቄዎች
የቴሌግራም መተግበሪያ ለአንድሮይድ እና አይኦኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች በተንቀሳቃሽ ስልኮችና እንዲሁም ለዴስክቶፕ በእ.ኤ.አ 2013 ተግባር ላይ የዋለ እና መልዕክቶችን ለመላላክ፣የድምፅ እና የተንቀሳቃሽ ምስል ጥሪዎችን ለማድረግ ብሎም ፋይሎችን ለመጋራት እና ሌሎች ተግባራትን ለማከናዎን ጥቅም ላይ የዋለ መተግበሪያ ነዉ፡፡
ይህ መተግበሪያ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እና ተወዳጅነትን ያተረፈ መተግበሪያ ሲሆን በርካታ ሰዎችም እየተጠቀሙበት ይገኛሉ በሀገራችንም ተወዳጅ ከሆኑ የመተግበሪያዎች ዝርዝር መሀል አንዱ እንደሆነ ይታመናል፤ ታዲያ ይህ መተግበሪያ እንደማንነኛዉም ሌላ መተግበሪያዎች ሁሉ የሳይበር ጥቃት ሊያስተናግድ ይችላል ባለፈዉ በሰኔ ወር እንኳን በርካታ ቴሌግራም ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች እንደተሰነዘሩ ዘ ሀከርኒዉስ ዘግቧል፡፡
የቴሌግራም መተግበሪያ እንዴት ሊጠቃ ይችላል
o የሶሻል ኢንጅነሪንግ ፡ ይህ ማለት በኢምፐርሶኔሽን ዘዴ ተመሳስልው በሚሰሩ መልእክቶች ሰዎች በቴሌግራም የሚላክላቸውን መልእክት በማመን የሚላኩ ሊንኮችን ሊጫኑ አባሪዎችን ሊከፍቱ እና ለጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ
o ፊሺንግ፡ ይህም ፊሺንጎች ተመሳስለዉ በሚሰሩ የማታለያ መንግዶች የሚትገበሩ ሲሆኑ የቴሌግራም ፊሺንጎችም ህጋዊ እና እዉነተኛ ከሚመስሉ አካዉንቶች የተላኩ በሚመስሉ ሃሰተኛ መልዕክቶች የማጭበርበር እና በመተግበሪያዉ ላይ እና በሌሎችም የመተግበሪያዉ ሲስተሞች ላይ ጭምር ጥቃት ማድረስ ነዉ
o ደህንነታቸዉ ያልተጠበቀ ሌሎች አፕሊኬሽኖከች፡ በመተግበሪያችን ላይ ኢንስቶል የምናደረጋቸዉ መተግበሪያዎች ከታወቁ ምንጮች የተገኙ እና ደህንነታቸዉ የተረጋገጠ መሆናቸዉን ካላረጋገጥን የቴሌግራም አካዉንቶችን ወይም ሌሎችን መተግበሪያዎችን ጭምር የሚሰልሉ ሊሆኑ ይችላሉ
o የምንጠቀምበትን መገልገያ በራሱ አለመዘመን
o የመገልገያ አካላዊ መሰረቅ አሊያም መጥፋት
የቴሌግራምመተግበሪያንስንጠቀምማድረግየሚገባንየደህንነትጥንቃቄወችንእንመልከት፡
o የቴሌግራም መተግበሪያን እንደየሚጠቀሙበት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከ ተገቢዉ የ መተግበሪያ ቋት ማዉረድ ተገቢ ነዉ
o በየጊዜዉ ለሚደረጉ ዝመናዎች ትኩረት መስጠት እና ተከታትሎ ማዘመን ተገቢ ነዉ
o አንቲ ቫይረስ እና አንቲ ማልዌር መጠቀም
o የቴሌግራም ቦቶችን መጠንቀቅ ማለትም ማሊሺየስ የሆኑ አለመሆናቸዉን ማረጋገጥ
o በመተግበሪያዉ የተካተቱ መለያዎች(features) በመጠቀም የደህንነት መለያዎችን መተግበር ለምሳሌ የ2 ፋክተር አዉተንቲኬሽንን መተግበር እንዲሁም የ ቴልገራም ፓስኮድ መለያ መተግበር
o በተቻለ መጠን የቴሌግራምንም ይሁን ሌሎች መተግበሪያዎችን ደህንነቱ በተረጋገጠ የአፕሊኬሽን ሎከር መቆለፍ
o በቴሌግራም የሚላኩ ሊንኮች(አስፈንጣሪዎች) እና አታችመንቶች(አባሪዎች) እንደሌሎች የኦንላይን ተግባራት ሁሉ የ ፊሺንግ መንገዶች ስሚሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ
o የምንጠቀምበትን መገልገያ አካላዊ ደህንነት መጠበቅ
o ሌሎች የደህንነት ጥንቃቄዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም ቴሌግራማችን የተጠቃ መስሎ ከተሰማን ሌሎች ሴሽኖችን በሙሉ መቋረጥ ብሎም እስከወዲያኛዉ ማጥፋት ተገቢ ነዉ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


South Africa Street
Addis Ababa
ETH