Capital
03/05/2026
የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የሀብት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ
የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ በሀብታቸው ላይ ከፍተኛ እድገት ማስመዝገባቸው ተሰማ።
እንደ ብሉምበርግ የቢሊየነሮች መረጃ መሠረት፣ የዳንጎቴ ጠቅላላ የሀብት መጠን ወደ 34.0 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል።
ይህ የሀብት ዝላይ በፈረንጆቹ 2026 ዓመት ውስጥ ብቻ 3.99 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ እንዲያገኙ ያስቻላቸው ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥም ወደ 69ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጡ አድርጓቸዋል።
ምንም እንኳን ሌሎች አፍሪካውያን ቢሊየነሮች በዓመቱ ውስጥ ያስመዘገቡት የትርፍ ዕድገት መጠን ከእሳቸው ቢበልጥም፣ ዳንጎቴ አሁንም የአህጉሪቱን ቀዳሚነት በሰፊ ልዩነት እንደያዙ ቀጥለዋል።
ከዚህ የሀብት እድገት ጋር ተያይዞ በሌጎስ የሚገኘው የናይጄሪያው ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጥታ የጄት ነዳጅ አቅርቦት መጀመሩ የተዘገበ ሲሆን፣ ይህም ከአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድ ጋር ያለውን የኢነርጂ ትስስር አጠናክሮታል።
ማጣሪያው በቀን 650,000 በርሜል የማምረት ሙሉ አቅሙን እየተጠቀመ ሲሆን፣ የጄት ነዳጅ ኤክስፖርትም በቀን ወደ 158,000 በርሜል ከፍ ብሏል። በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በተፈጠረው የአቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ለነዳጁ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል።
02/05/2026
የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠናን ውጤታማ ለማድረግ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲጠናከሩ ተጠየቀ
የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነትን በኢትዮጵያ ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ ጠንካራ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና የመንግስታት ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) አሳሰበ።
ምክር ቤቱ ከኤክስፐርቲዝ ፍራንስ እና ከኤኮ ትሬድ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ እንደተገለጸው፤ የነጻ ንግድ ቀጠናው በዓለም ደረጃ ግዙፍ የገበያ ዕድል ይዞ የመጣ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያውያን ኩባንያዎች በተለይም አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት ከዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሰረታዊ ማሻሻያዎች ያስፈልጋሉ።
የአዲስ ቻምበር ምክትል ዋና ፀሐፊ አቶ ካሳሁን ማሞ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ የአፍሪካ ስነ-ህዝብ በ2050 ወደ 2.5 ቢሊዮን ያድጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም ለሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ሰፊ የገበያ አድማስ ይከፍታል።
ሆኖም ይህንን ዕድል ለመጠቀም በኩባንያዎች ደረጃ የሚታዩ የአደረጃጀትና የሰው ኃይል ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የነጻ ንግድ ቀጠናውን ውጤታማ ለማድረግ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ተቋማትን አሠራር ማሻሻል፣ የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎችን በየጊዜው መቃኘትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትን ማጠናከር፣ የሎጀስቲክስ እና የመሠረተ ልማት አውታሮችን በስፋት መዘርጋት እንዲሁም የንግድ ድጋፍ አገልግሎቶችንና የግንዛቤ ማስፋፊያ ሥራዎችን ማከናወን እንደሚገባ ምክረ-ሐሳቦች ቀርበዋል።
01/05/2026
በኢራን ጦርነት አሜሪካ እስከ 2.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የጦር መሣሪያ አጣች
በኢራን እና በአሜሪካ-እስራኤል ጥምረት መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት አሜሪካ ከ2.3 እስከ 2.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የአየር ላይ የጦር መሣሪያ ኪሳራ እንደደረሰባት በዋሽንግተን የሚገኘው የስትራቴጂክ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ማዕከል (CSIS) ይፋ አደረገ።
ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ ጦርነቱ ከተጀመረበት ባሉት 61 ቀናት ውስጥ የኢራን ሚሳኤሎችና ድሮኖች የአሜሪካን የተራቀቁ የራዳር ሥርዓቶች እና የጦር አውሮፕላኖች ኢላማ አድርገዋል።
በተለይም በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የፕሪንስ ሱልጣን አየር ኃይል ጣቢያ ላይ በደረሰ ጥቃት 700 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውና እንደ በራሪ የዕዝ ማዕከል የሚያገለግለው ‘E-3 AWACS’ የተሰኘው የራዳር አውሮፕላን መውደሙ ለፔንታጎን ትልቅ ድንጋጤ መፍጠሩ ተመልክቷል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር የኢራን ወታደራዊ አቅም በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት መዳከሙን ቢገልጹም፣ መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ተቃራኒ መሆኑን የዘርፉ ተንታኞች ይናገራሉ።
በጦርነቱ ወቅት እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ የ‘THAAD’ ሚሳኤል መከላከያ ራዳሮች መውደማቸውና በኩዌት ውስጥ በደረሰ ጥቃት ሦስት የF-15 የጦር ጄቶች መከስከሳቸው የኪሳራውን መጠን ከፍ አድርጎታል።
የአሜሪካ መንግሥት የጉዳቱን መጠን ለሕዝብ ይፋ ከማድረግ ቢቆጠብም፣ ይህ ሁኔታ በመጪው የኅዳር ወር የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ላይ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ ጫና ሊያሳድር እንደሚችል ተገምቷል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Bole Behind Rwanda Embassy
Addis Ababa
P.O.BOX95CODE1110