Mesob Creative
03/02/2026
ፕላስቲክ ተከለከለ? ትኩር ብለን እንይ! አዲስ "የፈጠራ በር" ተከፍቷል! ♻️✨
ዛሬ በአዲስ አበባ የፕላስቲክ አጠቃቀም በይፋ ታግዷል። የለመድነው ነገር ሲገታ መጨነቅ ተፈጥሯዊ ቢሆንም፣ እኛ በ Mesob Creative ለውጡን የምናየው በሌላ መነጽር ነው። ትልልቅ የፈጠራ ስራዎች የሚወለዱት በትልልቅ "ግፊቶች" ውስጥ ነው።
ለምሳሌ ኮቪድ ሲመጣ "እንዴት ምርትና አገልግሎት ማግኘት እንችላለን ብለን አሳስቦን ነበር?" ነገር ግን የዲጂታል ክፍያን እና ዴሊቨሪን እንደለመድን ሁሉ፣ ዛሬ ደግሞ ፕላስቲክ ሲታገድ አዲስና ውብ የፈጠራ ባህል ልንጀምር ነው።
📍 ለምን ይሄን እንደ ትልቅ ዕድል (Opportunity) እናየዋለን?
1️⃣ የብራንዲንግ ለውጥ (Branding Evolution): አሁን ደንበኛህ "ፌስታል" ብቻ አይፈልግም። "ለአካባቢ ጥበቃ የቆመ ዘመናዊ ብራንድ" ይፈልጋል። ፕላስቲክ በሚያምር የጨርቅ (ሸማ) ወይም የወረቀት ከረጢት ስትተካ፣ ለደንበኛህ "እኛ ለትርፍ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድም እንጨነቃለን!" የሚል ጠንካራ መልዕክት እያስተላለፍክ ነው።
2️⃣ የዲዛይን አብዮት (Design Revolution): ፕላስቲክ ላይ ሎጎ ከመለጠፍ ባለፈ፣ በሀገራችን ተፈጥሯዊ ቁሳቁሶች ላይ የሚሰሩ ዲዛይኖች የቢዝነስህን ማንነት ይበልጥ "ቄንጠኛ" እና "ኢትዮጵያዊ" ያደርጉታል። ይህ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም አዲስ የስራ እድል የሚከፍት ነው።
3️⃣ ዘላቂነት (Sustainability) እንደ እሴት: የአውሮፓ እና የአሜሪካ ትልልቅ ቢዝነሶች "Eco-friendly" ለመሆን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያወጣሉ። እኛ ግን ይህ እድል በሩጫ መጥቶልናል። ዛሬ የምትወስደው እርምጃ ለወደፊቱ ቢዝነስህ ትልቅ የገበያ ተወዳዳሪነትን ይፈጥርልሃል።
💡 የ Mesob Creative መርህ እኛ የምናምነው "ችግር የፈጠራ እናት ናት" በሚለው ነው። ፕላስቲክ መታገዱ ስራችንን አይገታውም፤ ይልቁንም ይበልጥ ተፈጥሯዊ፣ ይበልጥ ኢትዮጵያዊ እና ይበልጥ ዘመናዊ እንድንሆን ያደርገናል።
ለውጡን አትፍራው፤ ተጠቀመበት! ፕላስቲክ ያልፋል፤ በፈጠራ የታጀበ ብራንድ ግን ለዘላለም ይኖራል።
እናንተስ ከፕላስቲክ ውጭ ምን አይነት "ቄንጠኛ" እና አካባቢን የማይጎዱ አማራጮችን ለቢዝነስህ እያሰባቹ ነው? ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን። 👇
hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag hashtag
25/01/2026
ሰዓት ማሰር 'ጌጥ' ነው፤ ሰዓት ማክበር ግን 'ብራንድ' ነው! ⌚️🇪🇹
በሀገራችን የቢዝነስ ባህል ውስጥ አንድ የሚገርም ፓራዶክስ አለ፦ በእጃችን ላይ ውድ Apple Watch ወይም Rolexእናስራለን፤ ጭንቅላታችን ውስጥ ግን "እየደረስኩ ነው" የሚል የቆየ ሰበብ ይዞራል።
እንደ ብራንድ ስትራቴጂስት አንድ መራራ እውነት ልንገራችሁ፦ ቢዝነስ ሰዓት አይለይም፤ ቢዝነስ የሚለየው "ታማኝነትን" (Integrity) ብቻ ነው።
ሰዓት ማክበርን ከቴክኒካዊ ጉዳይነት አውጥተን በሶስት ጥልቅ የፍልስፍና ምሰሶዎች እንመልከተው፦
1. ጊዜ የኢንተግሪቲ (Integrity) መስታወት ነው
ብራንድ ማለት ቃል መግባት ነው። ሰዓት ደግሞ ያ ቃል ምን ያህል እውነት እንደሆነ የምናይበት መስታወት ነው።
ሰዓትህን የማታከብር ከሆነ፣ ቃላትህ ክብደት የላቸውም። ቃላትህ ክብደት ከሌላቸው ደግሞ ብራንድህ ባዶ ቅርፊት ነው። ውድ ሰዓት አርገህ ለቀጠሮ ስትረፍድ፣ ለዓለም የምታበስረው መልዕክት "የራሴን ውበት እንጂ የእናንተን ህይወት አላከብርም" የሚል ነው። ይሄ የብራንድ ክህደት ነው።
2. ሰዓት ማክበር የሰውን ህልውና ማክበር ነው
"እየመጣሁ ነው" ብለን ቤታችን ሆነን የምንዋሸው ውሸት ከቀጠሮ መጣስ በላይ የሆነ ጥልቅ ስብራት አለው።
አንድን ሰው ቀጠሮ ቦታ 1 ሰዓት ስታስጠብቀው፣ ዝም ብለህ ደቂቃዎችን እያባከንክ አይደለም፤ ከሰውየው እድሜ ላይ የማይመለስ 1 ሰዓት እየሰረቅህ ነው። ሰዓት ማክበር ማለት የሰውን ልጅ እድሜ እና የህይወት ዋጋ ማክበር ነው።
3. ፕሮቶኮል ወይስ ዲሲፕሊን?
ዩኒፎርም የለበሰ ሁሉ ወታደር እንዳልሆነ ሁሉ፣ ሰዓት ያሰረም ሁሉ ባለቀጠሮ አይደለም።
ሰዓት ማሰር የውጭ ማሳያ (Protocol) ነው። ሰዓት ማክበር ግን የውስጥ ማንነት (Character) ነው። ስማርት ዋችህ "ተነስ ተራመድ" እያለ ሲጮህብህ፣ አንተ ግን "ገና ነው" ብለህ የምታሸልብ ከሆነ፣ መሪው አንተ ሳትሆን ስንፍናህ ነው። እውነተኛ ብራንድ የሚገነባው ሰዓቱን ከእጅ ወደ ጭንቅላት ሲያወርዱት ብቻ ነው።
😊ካፌ ገብተን ማኪያቶአችን 5 ደቂቃ ሲዘገይ "ምን አይነት ሰራተኛ ነው?" ብለን እንናደዳለን። እኛ ግን የሰውን ሰዓት ስናባክን "አምስት ደቂቃ... አሁን መጣሁ" እያለን አመታትን እንቀጥላለን። መሞታችን እንደማይቀር ካመንን፣ ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም። የሰው ጊዜም አናባክን።
እኛ በ Mesob Creative የምናምነው ፍልስፍና ይሄንን ነው፦ "Time is the currency of Respect." ጊዜ የመከባበሪያ መገበያያ ገንዘብ ነው። ብራንድህን ከፍ ለማድረግ ከፈለግህ፣ ቃልህን በሰዓቱ ክፈል።
እናንተስ? በቀጠሮ መዘግየት በቢዝነስ ግንኙነታችሁ ላይ ያደረሰባችሁ ትዝታ ምንድነው? ይህን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ ያጋሩኝ። 👇
hashtag hashtag hashtag
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
00251