SymIcon Technology & Promotion
26/02/2023
ወዳጅነት ፖርክ Photo by Eskedar
19/07/2021
#ይነበብ!!!
በአንድ ወቅት አንዲት ድርስ እርጉዝ አጋዘን የመውለጃዋ ሰዓት ደረሰና ለመውለጃ የሚሆን ጥሩ ቦታ እየፈለገች አንድ ወንዝ አጠገብ ደረሰች። ቦታውንም ለመውለድ ምቹ ሆኖ አገኘችው። ወዲያውም ምጥ ጀመራት።
ነገር ግን ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ። በዚህም የተፈጠረው መብረቅ በጫካው ውስጥ እሳት አስነሳ።
በመሀልም አጋዘኗ ወደግራ ስትዞር አንድ አዳኝ ቀስቱን ወደሷ አነጣጥሮ ሲመቻች ተመለከተች። ወደቀኝ ስትዞር ደግሞ አንድ አንበሳ ወደሷ እየተመለከተ አድፍጦ በቀስታ ይጠጋል።
አጋዘኗ ወደፊት ለፊቷ ተመለከተች ፣ ከባዱ የወንዝ ውሃ እያስገመገመ ይወርዳል። ከበስተጀርባዋም በመብረቁ ብልጭታ የተፈጠረው እሳት እየተንበለበለ ነው።
> ለመሆኑ ይህች አጋዘን ምንድን ነው ማድረግ ያለባት?
> ከከበቧት ጠላቶቿ ትተርፍ ይሆን?
> ግልገሏንስ ያለችግር ትገላገል ይሆን?
× እሳቱ ደርሶ ያቃጥላታል?
× ወይስ . . . አዳኙ በቀስቱ ይገላታል?
× የተራበው አንበሳ ገነጣጥሎ ይመገባታል?
× ወይስ . . . በፍርሃት ወንዝ ገብታ ጎርፍ ይወስዳታል?
አዳኝ ፣ እሳት ፣ አንበሳ እና ጎርፍ የከበባት እና በምጥ የተያዘች ይህች አጋዘን ምንድን ነው ማድረግ ያለባት???
በርግጥ አጋዘኗ ምንም አላደረገችም በምጧ ላይ ፣ አዲስ ህይወት በመፍጠር ሂደቷ ላይ አተኮረች።
#እናም . . . ምጧ ተፋፍሞ ባለበት ሰዓት እንዲህ ሆነ . . .
☞ አዳኙ ቀስቱን ሲወረውር የመብረቁ ብልጭታ ሃይሉን ጨመረና ዓይኑ ላይ አበራበት።
☞ የተወረወረው ቀስትም አቅጣጫውን ስቶ አድፍጦ ወደአጋዘኗ በሚጠጋው አንበሳ ላይ አረፈ። አንበሳው ሞተ።
☞ በመብረቅ ታጅቦ ሲያጉረመርም የነበረው ሰማይ ዝናቡን ለቀቀው። በዚህም እሳቱ ካለበት መቀጠል አልቻለም . . . ከሰመ።
አጋዘኗም በሰላም ግልገሏን ወለደች።
#የሰው ልጅም በህይቱ እነዲሁ ነው
በርካታ ችግር ከቦን መውጫ ልናጣ እና ዙሪያው ገደል ሆኖ ሊታየን ይችላል። ቢሆንም ግን ከአጋዘኗ ታሪክ የምንማረው ነገር አለን። ልብ በሉ . . . አጋዘኗ ችግር በከበባት ጊዜ ያተኮረችው ማድረግ በምትችለው ነገር ላይ ነበር። በምጥ ተይዛለችና . . . መውለድ። ምናልባት ትኩረቷን እንዴት ላምልጥ በሚለው ላይ አድርጋው ቢሆን ኖሮ በሰላም መውለዷ ህልም ፣ የአንዳቸው ሲሳይ መሆኗም እውን ይሆን ነበር።
ዙሪያችን በማጥ ቢከበብም ወደኛ የሚመጣው ነገር አብዝተን የተጨነቅንበት ነው። ስለዚህ ውስጣችንን በመልካም እና በምንፈልገው ነገር ብቻ ከሞላነው . . . መልካሙ ይሆንልናል ፣ የምንፈልገውንም ነገር እናገኛለን።
#ትኩረታችሁ በምትፈልጉት ነገር ላይ ይሁን . . . 'የሚያስፈልገኝ ነገር የትኛው ነው?' ብላችሁ እራሳችሁን ጠይቁ . . . መልሱም ወደእናንተው ይመጣል!!!
(አንብበው ሲጨርሱ Share በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ)
15/07/2021
ውሻን ያህል ታማኝ የለውም ይኼ ውሻ ባለቤቱ በሞት ተለየው ውሻው ከፍቅሩ የተነሳ የባለቤቱን መቃብር ቆፍሮ መኖሪያ አደረገው
የሠውልጅ ግን ?.....
አንድ አንድ ቃል ይበሉ
ፔጁን like በማረግ ተከተሉን ; Hasset Entertainment now .....
like
Like
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa