Addis Ababa City Administration Electric Service Administration Authority
29/06/2026
የመንገድ መብራቱ የምሽት ሥጋታችንን ቀርፎልናል — የአካባቢው ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም (መአአባ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የከተማዋን የመብራት መሠረተ ልማት ለማሻሻልና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ አካባቢዎች መጠነ ሰፊ የጥገና እና የስማርት መብራት ዝርጋታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው "ፒስ ሕንፃ" ጀርባ የሚኖሩትን አቶ ኤርሚያስ ዓለማየሁ እና ወ/ሮ ሀብታሜ ዲዲታ የተባሉ ነዋሪዎችን መአአባ አነጋግሯቸዋል።
"ቀደም ሲል በአካባቢያችን በጨለማ ምክንያት ይስተዋሉ የነበሩ የደህንነት ሥጋቶች በአዲሱ ዘመናዊ የመብራት ዝርጋታ ሙሉ በሙሉ ተቀርፈዋል፤" — ነዋሪዎቹ
ነዋሪዎቹ ጨምረው እንደገለጹት፤ በአካባቢው በጨለማ ምክንያት ይፈጸሙ ከነበሩ ሕገ-ወጥ ስርቆቶችና ከተለያዩ የደህንነት ሥጋቶች በመገላገላቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል። በተጨማሪም የተዘረጋው የመብራት መሠረተ ልማት የሕዝብና የሀገር ሀብት በመሆኑ፣ ከመሠረተ ልማት ስርቆትና ውድመት ለመጠበቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
ዘመናዊ መብራት፤ ለብሩህ አዲስ አበባ!
ለተከታታይ፣ ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃ ይህን ሊንክ ይከተሉ
https://linktr.ee/aaca.esaa
29/06/2026
ሰዉ አጠፋዉ፤ ሰዉ አለማዉ!!
ፈጣሪ የሰጠንን ቀበና “ሰዉ “ አጠፋዉ ፤ ይህ የተፈጥሮ ስጦታ መጥፋት ቁጭት ያደረበት “ሰዉ “ ደግሞ ቀበናን ዳግም እንደ አዲስ እንዲወለድ አደረገዉ።
የቀበና ወንዝ ለዘመናት በዘፈን እና በትዝታ ብቻ ስሙ ሲነሳና ሲወደስ ኖሮ ዛሬ ግን ዳግም እንዲወለድ አድርጐ አለማዉ!!
አርቲስት ፀሀዬ ዮሀንስ “ቢሻን ቀበና” እያለ ብዙዎች እየዋኙ ያደጉበትን የልጅነት ትዝታን ሲቀሰቅስ ፣የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ “ቢሻን አዲስ አበባ “ እያለ ሲያደናንቅ በዘመናት ውስጥ ግን ትዝታን ብቻ ተሸክሞ የወንዙ ተፈጥሮዊ ማንነት ጠፍቶ ፣የፍሳሽ መዉረጃና የቆሻሻ መጣያ ሆኖ፣ ጠረኑ አላስጠጋ ብሎ ተረስቶ የኖረ ወንዝ ነበር ።
እነሆ እነዚህ የብክለት ፣ የበሽታ ምንጭና የቆሻሻ ማጠራቀሚያ የነበሩትን ወንዞቻችንን ዛሬ ላይ በትጋት እና በላብ እየታከሙ፣ ለነዋሪው ተስፋን ሀሴትን የሚለግሱ የደስታ ምንጭ እየሆኑ ነው፡፡
በአጭር ጊዜ የተገነባው ይህ ድንቅ ፕሮጀክት፣ ከሌሎች የከተማዋ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ጋር ተዳምሮ አዲስ አበባን የውበት ማማ አድርጓታል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
28/06/2026
ድምቀት ጌጥ እና የውበት ፀዳል!!
"አዲስ አበባችን የነዋሪዎቿን ጥያቄዎችና መሰረታዊ ፍላጎቶች በተጨባጭ እየመለሰች፤ ለህዝባችን ቅድሚያ የሚሰጣቸውንና ከተማዋ የሚመጥናትን ታላላቅ የልማት ስራዎች ሁሉ በላቀ ብቃትና ትጋት እያከናወነች ትገኛለች።"
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
28/06/2026
ዛሬም የረዳን ፈጣሪ ይመስገን !
ዛሬ ለከተማችን ነዋሪዎአች አዲስ ድንቅ ሌላ ስጦታ የሆነውን "የእንጦጦ - ቀበና የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት" እና የቀበና ግድብ ፕሮጀክት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መርቀዉልን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
አዲስ አበባችን የነዋሪዎቿን ጥያቄዎችና መሰረታዊ ፍላጎቶች በተጨባጭ እየመለሰች፤ ለህዝባችን ቅድሚያ የሚሰጣቸውንና ከተማዋ የሚመጥናትን ታላላቅ የልማት ስራዎች ሁሉ በላቀ ብቃትና ትጋት እያከናወነች ትገኛለች።
ዛሬ ለከተማችን አዲስ አበባ ድምቀትና ተጨማሪ ጌጥ እና የውበት ፀዳል ያላበሰውን ይህን የወንዝ ዳርቻ እና የግድብ ልማት በክቡር ቨቅላይ ሚስትራችን ሀሳብ አመንጪነት በተሰጠን የስራ መመሪያ መሰረት በጥራትና በፍጥነት አጠናቀን ለህዝብ አቅርበናል። ፕሮጀክቱ በከተማዋ ከተሰሩት ሌሎች የኮሪዶር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች ጋር ተዋህዶ ሲታይ በእርግጥም አዲስ አበባ በአለም አቀፍ ደረጃ ምርጧ የቱሪስት መዳረሻ ብቻ ሳትሆን የውበት ማማ የሚያደርጋት ድንቅ ፕሮጀክት ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 87.6 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን፣ 10.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። በውስጡም እጅግ ማራኪ የሆኑ የጋራ አገልግሎት መስጫዎችንና የህዝብ መገልገያዎችን አሟልቶ ይገኛል። ይህም 1 ትልቅ ግድብ፣ 16 አነስተኛ ግድቦች፣ 3 ቼክ ዳሞች፣ 1.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሃይኪንግ፣እንዲሁም 20.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የወንዝ ድጋፍ ግድግዳን (Retaining Wall) ያካተተ ነው። የተፈጥሮ ውበቱን ይበልጥ ለማጉላትም 3 ማራኪ ፏፏቴዎች እና 1 የውሃ ምንጭ ግንባታ የተከናወነ ሲሆን፣ የመሬት ጥበቃን ለማረጋገጥ 36,928 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የኮንሶ ጋቢዮንና የኮንሶ እርከን ስራዎች ተሰርተውለታል።
ልማቱ ለተፈጥሮ በሰጠው ልዩ ትኩረት፣ 59.7 ሄክታር የሚሸፍን ውብ የአረንጓዴ ልማት ስፍራን ያበለፀገ ሲሆን፣ 50,330 የተለያየ ዝርያ ያላቸው ዛፎችም ተተክለውበታል። ከመሰረተ ልማት አቅርቦት አኳያ 10.62 ኪሎ ሜትር ዘመናዊ የአስፋልት መንገድ፣ 33.2 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገዶች፣ እና 33.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ዘመናዊ የመንገድ መብራት ዝርጋታ ተከናውኗል። በተጨማሪም 19.13 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ እና የጎርፍ ማስወገጃ መስመር፣ እንዲሁም 23 ንፁህ የመጸዳጃ ቤቶች ተገንብተዋል። ጎብኚዎች ወንዙን በቀላሉና በውበት እንዲሻገሩ ለማስቻል 21 የእግረኛ ድልድዮች፣ 3 ተንጠልጣይ ድልድዮች፣ 6 የእግረኛ የብረት ድልድዮች፣ 1 ሰርኩላር ድልድይ እና 1 የኮንክሪት ድልድይ ተሰርተዋል።
ማህበረሰቡ ዘና እንዲልና የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኝ በማሰብ፤ 9 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ በአንድ ጊዜ 695 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ 7 የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች (ፓርኪንጎች)፣ 4 የመሰብሰቢያ ስፍራዎች፣ 7 ፕላዛዎች እና 4 ፓቪሊዮኖች ተገንብተዋል። ለንግድና ለመዝናኛ አገልግሎት የሚውሉ 32 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ሱቆች፣ 2 አንፊ ቲያትሮች፣ 10 ካፍቴሪያዎች፣ 7 የልጆች መጫወቻ ስፍራዎች፣ እንዲሁም 2 አነስተኛ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ተካተውበታል።
በመጨረሻም፣ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በታለመለት የጊዜ እና የጥራት ደረጃ እንዲጠናቀቅ ሌሊት ከቀን የደከማችሁና የታተራችሁ ያስተባበራችሁና የደገፋችሁ በየደረጃው የምትገኙ አመራሮች፣ እንዲሁም ለመላው የአካባቢው ማህበረሰብ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
26/06/2026
ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
57ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 57ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር ጋር በተፈረሙ ሶስት የፋይናንስ ድጋፍና ብድር ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው ለዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ የእድገት ልማት ፖሊሲ ማስፈፀሚያ የሚውል የአራት መቶ ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ሺ (437,400,000) ኤስ.ዲ.አር የብድር ስምምነት ነው፡፡ ሁለተኛው የማህበረሰብ ተኮር የመሬት አያያዝ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል የአንድ መቶ አርባ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ (145,500,000) ኤስ.ዲ.አር የብድር ስምምነት ነው፡፡ ሶስተኛው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የመስኖ ልማት ለዘላቂ ምርታማነት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሀምሳ አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺ (54,600,000) ኤስ.ዲ.አር የብድር ስምምነት ነው፡፡ ምክር ቤቱም ሶስቱ የብድር ስምምነቶች ከሀገራችን የብድር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ የብድር ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተቋማት ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቷል፡፡ ተቋማቱ ለሚሰጧቸው አገልግሎቶች በውስጥ ገቢ የሚሸፈኑ ወጪዎችን ከአገልግሎት ተጠቃሚዎች በሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ ለመሸፈን እንዲችሉ የአገልግሎት ተጠቃሚውን አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት በጥራት መስጠት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት እንዲያስችሉ ረቂቅ ደንቦቹ ተዘጋጅተው ለምክር ቤቱ ቀርበዋል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
3. ከዚያም ምክር ቤቱ ውይይቱን ያደረገው ለኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ ማቋቋሚያ ስምምነት የአባልነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክን በአባልነት መቀላቀሏ ለሀገራዊ የልማት ፋይናንስ፣ ለመሠረተ ልማት ድጋፍ እና ለማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት አማራጭ የገንዘብ ምንጮችን ለማግኘት የሚያስችላትና ከደቡብ ደቡብ የፋይናንስ ሥርዓቶች ጋር የሚኖራትን ትስስር የሚያጠናክር መሆኑ ስለታመነበት የባንኩን የመመስረቻ ስምምነት ለማጽደቅ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለሀገራችን ዕድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወት እንደመሆኑ በ2006 ዓ.ም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ወጥቶ ላለፉት አመታት ሲተገበር ቆይቷል፡፡ በዚህም በኢንዱስትሪው አንዳንድ ለውጦች የተመዘገቡ ቢሆንም አለማችን ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ እድገት፣ የከተሞች መስፋፋት፣ የመሰረተ ልማቶች ፍላጎት ማደግ አንጻር ሰፊ ክፍተት የነበረበት በመሆኑ የዘርፉን ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን በማሳደግ፣ በስራ ላይ ያሉ የህግ ማዕቀፎችን በማጣጣምና በማዋሃድ እንዲሁም የዘርፉን የመልማት አቅም አሟጦ በመጠቀም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ እንዲያስችል ፖሊሲው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያያበት በኋላ ግብአቶችን በማከል በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ከዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
5. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የከተማ ልማት ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በ1997 ዓ.ም ወጥቶ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በስራ ላይ በቆየው የከተማ ልማት ፖሊሲ በከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት፣ ከተሞች በኢኮኖሚ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ፣ አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ እንዲሆን፣ የገጠርና ከተማ እንዲሁም የከተማ ከተማ ትስስር እንዲጠናከር፣ መሰረተ ልማትና የተለያዩ ማምረቻና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲስፋፉ በተደረገው ጥረት ውጤቶች የተመዘገቡ ቢሆንም ክፍተቶችም የነበሩበት ስለሆነ የነባሩን ፖሊሲ ክፍተቶች ለማረም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተሞች አካባቢ እየታዩ ያሉ አበረታች ለውጦችን ለማጽናት እና የበለጠ ለማጎልበት የከተማ ልማት ፖሊሲ በአዲስ መልክ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያያበት በኋላ ግብአቶችን በማከል በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ከዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
25/06/2026
የ90 ቀናት ዕቅድ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2018 ዓ.ም (መአአባ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን የ90 ቀናት ልዩ የክረምት ንቅናቄ መሪ ዕቅድ ላይ የጋራ ውይይት አካሄደ።
ዕቅዱ ባለስልጣኑ በሁሉም ዘርፎች ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት በላቀ ሁኔታ ለመፈፀምና የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን ለማፋጠን ያለመ ነው፡፡
ውይይቱን የመሩት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን፣ ዕቅዱ ለህብረተሰቡ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን በይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና ዘላቂነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑን አውስተዋል። እያንዳንዱ አመራርና ባለሙያ በቁርጠኝነት ወደ መሬት በማውረድ ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዘመናዊ መብራት፤ ለብሩህ አዲስ አበባ!
ለተከታታይ፣ ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃ ይህን ሊንክ ይከተሉ
https://linktr.ee/aaca.esaa
25/06/2026
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ለአየር ንብረት ጥበቃ ከሚያበረክተው መሠረታዊ አስተዋፅዖ ባለፈ፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የማር ምርት ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። ተፈጥሮንና አካባቢያችንን በመጠበቃችን፣ ደኖች እየተስፋፉ በመምጣታቸው፣ የንብ ዝርያዎችን የሚያግዙና የማር ምርትን የሚያሳድጉ ምቹ ከባቢዎች ምክንያት የምግብ ምንጮች ሊፈጠሩ ችለዋል።
ተስፋን እንትከል!
The beyond its foundational role in climate action, is now delivering real gains in Ethiopia's honey production. By protecting our natural environment, forests are expanding, and with them, the habitat and food sources that sustain bee populations and boost honey harvests.
𝗟𝗘𝗧 𝗨𝗦 𝗣𝗟𝗔𝗡𝗧 𝗛𝗢𝗣𝗘!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
24/06/2026
በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተሰጡ ባሉ አገልግሎቶች ላይ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸው አይካ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸው አይካ ይህን ያስታወቁት ቋሚ ኮሚቴው ባለፉት ቀናት በከተማ ስራ አስኪያጅ እና በተጠሪ ተቋማት ያካሄደውን የአንድ ወር የስራ አፈጻጸም የመስክ ምልከታ አጠናቆ ግብረ መልስ በሰጠበት የዛሬው መድረክ ላይ ነው።
በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ አመራሮች፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሌሎች ተጋባዥ አካላት የተገኙ ሲሆን በከተማ ስራ አስኪያጅና በተጠሪ ተቋማት ባለፉት አምስት ዓመታት እንዲሁም በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቦ የጋራ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸው አይካ እንደገለጹት ቋሚ ኮሚቴው ለከተማው ሥራ አስኪያጅ ተጠሪ በሆኑት የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን፣ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲና በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተከናወኑ የአገልግሎት አሰጣጥና ሌሎች የስራ እንቅስቃሴዎችን በቅርበት መመልከቱን ጠቁመዋል።
በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት እና በተለይም በ2018 በጀት ዓመት ተቋማቱ የከተማዋን ነዋሪዎች ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተጨባጭ እና ውጤታማ ተግባራትን መፈጸማቸውን አስገንዝበዋል።
ዶ/ር ግዛቸው በተጨማሪም፣ የሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ይበልጥ ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ የተሳለጡና የነዋሪውን ፍላጎት በትክክል የሚመልሱ እንዲሆኑ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሀብት፣ በፅዳት፣ በቅድመ አደጋ መከላከልና በአደጋ ምላሽ ሰጪነት የተመዘገቡ ለውጦችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በአጽንኦት አሳስበዋል። በቀጣይም ተቋማቱ በጋራ በመቀናጀት የአገልግሎት አሰጣጡን ከአሁኑ ደረጃ በላይ ማሳደግ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው፣ ባለፉት አምስት ዓመታት እና በ2018 በጀት ዓመት በጽ/ቤቱ ተጠሪ ተቋማት ሰፊ፣ ተጨባጭ እና ለውጥ ያመጡ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው፣ በተለይም የአገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን፣ የሚነሱ ቅሬታዎችን ከመለየትና ከመፍታት፣ እንዲሁም ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ይበልጥ ዘመናዊ እና ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን አስታውቀዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም፣ የከተማዋን ፅዳት ወደ ላቀ ደረጃ ከማድረስ፣ የመንገድ ዳር መብራት መሠረተ ልማት ዝርጋታን ከማስፋፋትና ተደራሽነትን ከማሳደግ፣ የቅድመ አደጋ መከላከል ሥርዓትን ከማጠናከርና የአደጋ ስጋትን ከመቀነስ፣ እንዲሁም የሲቪል ምዝገባ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የአገልግሎት ምዕራፍ ወደ ማሸጋገር በተደረጉ ጥረቶች አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በመጨረሻም፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት እና በ2019 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ በማጠናከር፣ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የማስደገፍ ስራዎችን በማጎልበት፣ የከተማዋን ነዋሪ ህብረተሰብ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ አገልግሎቶችን በተሻለ ደረጃ ለማቅረብ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።
ምንጭ፦ ስራ አስኪያጅ
24/06/2026
በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን በሁሉም ክፍለ ከተሞች 11 (አስራ አንድ) ማዕከላትን እውን በማድረግ ቃላችንን በተግባር አሳይተናል !
ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ግልፅ፣ ከአድሎና ጉቦ የፀዳ ፍትሃዊ አገልግሎት በሁሉም አካባቢ ማግኘት የሚያስችላችሁን ማዕከላት በማግኘታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ!
ዛሬ በአቃቂ ቃሊቲ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ሁለት አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ከፍተን በከተማችን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በ11 (አስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች) ማዕከላትን እውን አድርገናል።
በእነዚህ ማዕከላት ለህብረተሰቡ 50 በመቶ ያህል የመንግስት አገልግሎቶች እጅግ ቀልጣፋ በሆነ መልኩ እየተሰጠ ይገኛል።
ቀጣዩ ስራችን ደግሞ ቀሪዎቹን 50 በመቶ አገልግሎቶች ወደ እነዚህ ማዕከላት እንዲገቡ በማድረግ በአገልግሎት አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ በማዘመን ለነዋሪዎቻችን እርካታና እፎይታን መፍጠር ይሆናል።
ለረጅም ዘመን የተተበተበ ቢሮክራሲ፣ በብልሹ አሰራር ውስጥ የነበረውንና ለመለወጥ ጥረቶች ቢደረጉም ባለመለወጡ የሪፎርም ዝለትና ሊለወጥ አይችልም ወደሚል ተስፋ መቁረጥ ደረጃ ላይ የደረሰውን የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ተግተን በመስራት ትልቅ ሽግግር ያደረግንበት፣ ህዝባችን ጊዜውንና ገንዘቡን ለልማት እንዲያውል በሚያደርግ ማዕከል መተካት ችለናል።
በሀገራችን ሙያተኞች የገነባናቸው እነዚህ ተቋማት የሀገራዊ ህልሞቻችን በለውጥ መገስገስ እንደምንችል ማረጋገጫዎች ናቸው ።የዛሬዎቹን ጨምሮ በአጭር ጊዜ በጥራት በመገንባት፣ በማማከር እንዲሁም ተቋሞቹን በቴክኖሎጂ እንዲሟሉ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ ሁሉ በከተማችን ነዋሪዎች፣ በከተማ አስተዳደሩና በራሴ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
23/06/2026
በገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ትዕግሥት ፍስሀ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ አዲስ የከተማ ልማት ምዕራፍ ውስጥ እየገባች ሲሆን፥ ትኩረቱም ከተሞችን ማሰፋፋት ላይ ብቻ ሳይሆን ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንዲሁም ምቹ፣ ተወዳዳሪ፣ ሁሉን አቀፍና ዘመናዊ ከተሞች ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለጋራ ብልፅግና ቀጣይ ሞተር እንዲሆኑ ማድረግ ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
1000