Bisrat Promotion

Bisrat Promotion

Share

27/07/2024

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ውድ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን ምክኒያት ብሄራዊ ሀዘን ታውጇል ስለሆነም የጣፍጭ መዝናኛ ዝግጅት ክፍል ዛሬ የሚተላለፈውን ፕሮግራም አጥፎል

ውድ ህይወታቸው ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እየተመኘን በሚቀጥለው ሳምንት መደበኛ ፕሮግራማችን የሚቀጥል መሆኑን እንገልፃለን ።

21/06/2024

ለአካል ጉዳተኞች የሚሆኑ የተለያዩ እቃዎችን ከፈለጉ ከብስራት ፕሮሞሽን ያገኛሉ
በ +251115577357 ይደውሉ
ከምንሸጣቸው እቃዎች መካከል በጥቂቱ
Talking watch
Hearing aid
Wheelchair
braille watch
Crutch
Talking calculator and other

Photos from Bisrat Promotion's post 14/06/2024

የአካል ጉዳተኞችን ለማገዝ ዊልቸር በነፃ የምትሰጠው ኢትዮጵያዊት

ገና በልጅነቷ ባጋጠማት የፖሊዮ ህመም ምክንያት የቀኝ እግሯን እንደፈለገች አታዘውም፡፡ ቆማ መሄድ ባለባት የልጅነት አድሜዋ ቆማ እንድትሄድ አላስቻላትም ነበር፡፡ ነገር ግን ጠንካራ እና የተሻለ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ቤተሰቦች ነበሯት፡፡ ስለሆነም ብዙ ወጥተውና ወርደው ብዙ ወጪም አውጥተው በ5 ዓመቷ መራመድ እንድትችል አደረጓት፡፡ ሳባ ተክለማርቆስን፡፡

ሳባ ተክለማርቆስ የአጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ መስራች ነች፡፡ አጋፔ ለአካል ጉዳተኞች በነጻ ዊልቸሮችን የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ሳባ በመላው ዓለም የሚገኙ በጎ አድራጊዎችን አሰባስባ ይህን መልካም ተግባር ታደርጋለች፡፡ ማንም አካል ጉዳተኛ መሬት መንፏቀቅ የለበትም ብላ በማመን የዛሬ አራት ዓመት ይህንን ጉዞ እንደጀመረች ከአዲስ ዋልታ ጋር ባደረገችው ቆይታ ገልጻለች፡፡

በ14 ዓመት እድሜዋ ወደ አሜሪካ ያቀናችው ሳባ ትምህርቷን የጨረሰችውም ሆነ ቤተሰብ የመሰረተችው በዛው በአሜሪካ ነው፡፡ ከ20 ዓመታት ቆይታ በኋላ ለእረፍት ወደ ትውልድ ሀገሯ ስትመለስ የተመለከተችው ነገር አንድ ውሳኔ እንድትወስን አስገደዳት፡፡

ከብዙ ዓመታት በኋላ ስትመለስ ብዙ ነገር ረስታ እንደነበርና ቤተክርስትያን አካባቢ መሬት ላይ እየተንፏቀቁ ምጽዋት የሚጠይቁ በርካታ አካል ጉዳተኞች ስትመለከት ደነገጠች፡፡ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብላም ወሰነች፡፡ ለዚህም ወደ አሜሪካ ተመልሳ አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያን ከአራት ዓመት በፊት አቋቋመች፡፡

በአጋፔ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ሰራተኞች ሳባ በአሜሪካ ከልጇቿና ቤተሰቦቿ ጋር ተመችቷት መኖር ስትችል በየክፍለሀገሩ እየዞረች በጣም ለተጎዱ አካል ጉዳተኞች እና ረጂ ለሌላቸው በነጻ ዊል ቸር ትሰጣለች ሲሉ ደግነቷን ይገልጻሉ፡፡

አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ በሁሉም ክልል እየሄደ በየአካባቢው ያሉ አካል ጉዳተኞችን ይደግፋል፡፡ ከየአካባቢው ፎቶና የተለያዩ መረጃዎች ይላካሉ፡፡ ነገር ግን አንድ የዊል ቼር አይነት ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች አይሆንም፡፡ ስለሆነም እንደየጉዳቱ የተለያየ ዊል ቼር ያስፈልጋል፡፡ እንደየአስፈላጊነቱና እንደጉዳታቸው አይነት ዊል ቼርም የሳባ ድርጅት በነጻ ይሰጣል፡፡

ሳባ በመጨረሻም ማንም አካል ጉዳተኛ መሬት ላይ በመንፏቀቅ ሲሄድ ማየት አልፈልግም ስትል ምኞቷን ገልጻለች፡፡

14/02/2024

15ኛው አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በ2017 ዓም በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቀጣዩ አመት ዓለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ጉባኤው ከጥር 6 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ትብብሩ ጉባኤውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዚሁ ወቅት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የዓለም የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በቀጣይ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ጉባኤውን ከብሔራዊ መስማት ከተሳናቸው ማህበርና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉና የአገራትን ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራትን ዩኒቨርሲቲው እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ ጉባኤው በኢትዮጵያ እንዲካሄድ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
27526