Action For Development - AFD
04/02/2026
በጂንካ ከተማ ተከስቶ የነበረዉን የማርበርግ ቫይረስ ለመቆጣጠር አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ላበረከተዉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከደቡብ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት የምስጋና ሰርተፊኬት ተሰጥቶታል፡፡
አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት በጂንካ ከተማ ተከስቶ የነበረዉን የማርበርግ ቫይረስ ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በመጀመር የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን፣ መድሀኒቶችን፣ የህክምና መሳሪያዎችን፣ ለህክምና ባለሙያዎች የሚሆኑ አልባሳት፣ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች ዉሀ በማቅረብና መታጠቢያዎችን (water facility) በማዘጋጀት አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
ኢትዮጲያ የማርበርግ ቫይረስን በቁጥጥር ስር ማዋሏን የጤና ሚኒስትር ጥር 18/2018 ዓ.ም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
Action For Development received a certificate of appreciation from the Southern Ethiopia Regional Government in recognition of its contribution to the Marburg virus disease response.
By launching an emergency response to halt the virus in Jinka, Action For Development contributed by providing hygiene supplies, medicines, medical equipment, apparel for medical professionals, as well as supplying water and setting water facilities in schools.
It is recalled that the Ministry of Health announced on January 18, 2018 (E.C.), that Ethiopia has brought the Marburg virus under control.
20/01/2026
በምስራቅ ቦረና ዞን የአክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት (AFD) እና የዌልት ሀንግር ሂልፌ (WHH) ጥምረት 990 ሴቶችን በ60 የቁጠባ እና ብድር ማህበራት በማደራጀት፣ መሰረታዊ ፍላጎታቸዉን ለማሟላት የነበረባቸዉን የኢኮኖሚ ችግር ወደ ጥንካሬና ስኬት ታሪክ ቀይሮታል። እነዚህ ሴቶች ከ5.1 ሚሊዮን ብር በላይ መቆጠብ የቻሉ ሲሆን፣ የተለያዩ አነስተኛ ንግዶችን በመጀመር የተሻሻሉ ቤቶች እና እንደቤት እንስሳት ያሉ የሀብት ንብረቶችን ማፍራት ችለዋል። ይህ ፕሮጀክት ከገንዘብ ስኬት ባለፈ፣ ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር እንዲፈጥሩ እና በማህበረሰባቸው ውስጥ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል በራስ መተማመን እንዲገነቡ ረድቷቸዋል።
By empowering 990 women through 60 Savings and Loan Cooperatives, the AFD and WHH partnership has turned the difficulty to make ends meet into a story of resilience in East Borena. These women have mobilized over 5.1 million ETB in savings, started small businesses, and secured essential assets like improved housing and livestock. Beyond financial success, the project has fostered powerful social bonds and the confidence to drive long lasting change in their communities.
01/12/2025
የእሷ ክብር፣ የእኛ ሀላፊነት (English below)
በአለም አቀፍ ደረጃ ከ3 ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ ፆታዊ ጥቃት ይገጥማታል:: በድህነት፣ የሰብዓዊ ቀዉስ በሚከሰትበት ሁኔታ እንዲሁም ለአየር ንብረት ለዉጥ ተፅዕኖ ተጋላጭ በሆኑ ሁኔታዎች ዉስጥ ፆታዊ ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡
ሴቶች ፆታዊ ጥቃት ከደረሰባቸዉ በኋላ የሚገጥማቸዉ የደህንነት ስጋት፣ የፍትህ እጦትና ተያያዥ ተፅዕኖዎች ከህመማቸዉ የማገገም ሁኔታ ላይ እክል ይፈጥርባቸዋል፡፡
አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን በፅኑ የሚቃወም የ16 ቀናትን አከቲቪዝም ተቀላቅሏል፡፡ የሴቶችን ጥቃት ዋጋ ከሚያሳጡ አነጋገሮች በተቃርኖ እንቁም፡፡
Her Dignity, Our Responsibility
Worldwide, one in three women experience sexual or physical violence in her lifetime. Sexual violence increases significantly in conditions of poverty, humanitarian crises, and vulnerability to the impacts of climate change.
After experiencing sexual violence, the safety risks, lack of justice, and related impacts that women face hinder their recovery from the trauma.
Action for Development has joined the 16 Days of Activism, strongly opposing gender-based violence. Let us stand against narratives that trivialize violence against women.
09/09/2025
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
19859
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:30 |
| Tuesday | 08:30 - 17:30 |
| Wednesday | 08:30 - 17:30 |
| Thursday | 08:30 - 17:30 |
| Friday | 08:30 - 17:30 |