EvaSUE
25/05/2026
https://www.youtube.com/watch?v=OKi8379ru_k&t=541s&pp=ygUSIDUga2lsbyBmZWxsb3dzaGlw
የ 5 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት |5kilo fellowship Second semester FULL Manuscript vlog 2018
02/05/2026
ቃል ቅምሻ
እኔ ግን በጸናች ፍቅርህ እታመናለሁ፤
ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
ቸርነቱ በዝቶልኛልና፣
ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።
መዝሙር 13፥5-6
መታመኛ ሚሆን የጸና ፍቅር የእግዚአብሔር ፍቅር ብቻ ነው ። ፍቅረ እግዚአብሔር መወላወል የሌለበት ፣ ማይናወጽ ፣ ወለም ዘለም ማይል ፣ ወረት ማያወቀው ጽኑ ፍቅር ነው ። ፍቅር ለአምላካችን እግዚአብሔር ባህሪው ብቻ ሳይሆን ስሙ ነው ፤ መገለጫው ብቻ ሳይሆን ማንነቱም ነው ።" እግዚአብሔር በማንነቱ ፍቅር በመሆኑ ሌሎችን የሚያፈቅርበት ፍቅር የሚመነጨው ከራሱ ከማንነቱ ነው ። እግዚአብሔር የዘላለማዊ ፍቅር አንድነት ነው ማለት ነው ።ከዘላለምም እንዲሁ ነበረ ። ዓለምን የወደደበት ፍቅርም እርሱ ራሱ ነው ። "¹ እግዚአብሔር ዓለምን የወደደበትን ፍቅር በክርስቶስ በኩል ለዓለም ገልጧል ።
የፍቅር ትርጉሙም ሌላ ዐይደለም ። "እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።( 1 ዮሐንስ 3:16) "ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው።(1 ዮሐንስ 4፥10) " ስለዚህ ፍቅርን ያወቅነው በክርስቶስ መስቀል ነው ፤ ይህም እግዚአብሔርን ይገልጣል ። እግዚአብሔር የሚገኘው የክርስቶስ መስቀል ዘንድ ነውና ።የእግዚአብሔር ፍቅር በአካል ሲገለጥ ለማየት ፣ ኢየሱስን መመልከት ... "² ብቻውን በቂ ነው ።
እግዚአብሔር ጽኑ የሆነውን ፍቅር ፣ አንድያ ልጁ በመስጠት ገለጦልናልና እኛም ነፍሳችንን ፣ ለርሱ እና ለወዳጆቻችን በመስጠት ይህን ፍቅር ልንገልጥ ይገባናል ። ከመግለጥ በፊት ግን ፍቅሩን መረዳት እና በፍቅሩ መታመን ይቀድማል ። ፍቅሩን የተረዳ ፣ በፍቅሩ ይታመናል ።
መታመን መኖርን ያስከትላልና ፣ በፍቅሩ የሚታመን መኖር አይከብደውም ። በክርስቶስ በኩል በተገለጠው ጽኑ ፍቅር መታመን ክርስቲያናዊ ሕይወት መገለጫ በመሆኑ ፤ ሠርክ ማልደን እንደዘማሪው በአንደበታችን " እኔ ግን በጽኑ ፍቅር እታመናለሁ !" እንድንል እንጋበዛለን ። ልባችንንም በማዳን ሥራው ደስ ይሰኝ ።
ልብን ደስ ሚያሰኝ ሌላ ነገር በመሻት አንዛል ፤ ማዳኑን በማሰብ ብቻ በደስታ እንደንሞላ እንሻ ። የበዛውን ዘላለማዊ ቸርነቱን እያወጠነጠንን ኹለንተናችንን ሕያው እና ቅዱስ መሥዋዕት በማድረግ በእውነትና በመንፈስ ለእግዚአብሔር ዝማሬን እናቅርብ ።
✍️ጌታሁን አያኖ
____
1)ጳውሎስ ፍቃዱ የእግዚአብሔር ልጅ ገጽ 32 - 43
2)
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Queen Elizabeth II
Addis Ababa
34354