CMTV

CMTV

Share

Photos from CMTV's post 16/05/2026

በክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ምሽት አገልግሎት

ርዕስ ፦ ዛሬ ክብሩን ታያላችሁ

- ፈተናዎቻችን እድሎች ናቸው

- ፈተናዎች የትልልቅ ታምራት መወለጃዎች ናቸው ።

- ፈተናዎች ኮሳሳ እንዳንሆን አቅመ ቢስ እንዳንሆን መንፈሳዊ ጡንቻ መገንቢያዎቻችን ናቸው ።

- ፈተናዎች የክብሩ መገለጫዎች እና ወደ ሚቀጥለው ደረጃ መሸጋገሪያዎቻችን ናቸው ማዕረግ መቀበያዎቻችን ናቸው ።

- በህይወታችን ዉስጥ አለ የምንለው ፈተና መጥፊያችን ሳይሆን መድመቂያችን መክበሪያችን ነው ።

- ፈተናዎች እግዚአብሔርን ማወቂያችን ናቸው ።

- ትልልቅ ታምራት የሚወለደው በፈተናዎች ዉስጥ ነው ።

- እምነት ለፈተናዎች መልስ ሲሰጥ ታምራት ይሆናል ።

- ክብር ማለት የሀይሉ ባለቤት እግዚአብሔር ለኛ ሲታወቅ ወይም ለኛ ሲገለጥ ማለት ነው ።

- ክብር ማለት የሀይሉ ባለቤት እግዚአብሔር ታምራታዊ አድራጊ ሀይሉ በሁኔታዎቻችን ላይ ሲገለጥ ማለት ነው።

- የእግዚአብሔር ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።

- ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ኢየሱስ ክርስቶስን መገንዘብ የእግዚአብሔርን ክብር ማወቅ ነው

- ያለ ክርስቶስ እግዚአብሔርን ማወቅ አይቻልም ።

- እግዚአብሔር ለፍጥረት ለመታወቅ ብሎ እራሱን የገለጠው ራሱን ያስተዋወቀዉ በልጁ በመድሀኒዓለም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው ።

- ኢየሱስ ክርስቶስን ስንቀበል እግዚአብሔርን የምናዉቅበትን ብርሃን እናገኛለን ።

- ኢየሱስን ስንቀበል ስለ እግዚአብሔር ትክክለኛ እዉቀት ይኖረናል እግዚአብሔር ለኛ ያለው ሀሳብ እና እቅድ ይገልጥልናል።

Photos from CMTV's post 11/05/2026

በክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የግንቦት ወር ትንቢታዊ አዋጅ የእሁድ ሁለተኛው አገልግሎት

ርዕስ:- የዝግጅት ወር

- በተለያዩ የህይወት ጎዳናዎች መዘጋጀት ይኖርብናል።

- የመጀመሪያው ዝግጅት የማንነት ዝግጅት ነው ፤ ማንነታችንን ለእግዚአብሔር ማንነት ማዘጋጀት።

- ትልቅ ክንውን ፣ በረከት ፣ ትልቅ የእግዚአብሔር እጅ የፀሎት መልስ የምንፈልግ ከሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ህይወታችን እና ኑሮአችንን ለእግዚአብሔር ማዘጋጀት ይኖርብናል።

- መልሱ የሚመጣው ከራሱ ከሰጪው ጋር ስለሆነ ለሰጪው ዝግጁ የሆነ ቤት እና ህይወት ለስጦታው ዝግጁ ይሆናል።

- ለስጦታው እጃችንን ከመዘርጋታችን በፊት ለሰጪው ልባችንን መክፈት ይኖርብናል።

- የምናዘጋጀው ህይወታችንን ነው ህይወትን የማዘጋጀት እና የማስተካከል ጊዜ ያስፈልገናል።

- ጌታ ሊያመጣ ላለው በጎ ነገር ፤ ሊያደርገው ላለው ታላቅ ነገር የተዘጋጀ የምህረት ዕቃ ለጌታ የሚጠቅም ይሆናል። 2ጢሞ 2: 21

- ዝግጅቱ የክብር የምህረት እቃ ለጌታ የሚጠቅም እቃ እንዳንሆን ከሚያደርጉ ነገሮች ራስን መከልከል ነው።

- የእግዚአብሔርን ማዳን እና ሀይል የምንጠባበቅ መልካም ነገር በመጣ ጊዜ አያልፈንም ፤ ክፉ ነገር ወደ ቤታችን አይገባም።

- እግዚአብሔር ተዘጋጁ የሚለን ልባዊ ፣ የማንነት ዝግጅት ነው።

- የመጀመሪያው ዝግጅት ህይወትን ከእግዚአብሔር መንገድ ጋር የማስተካከል ዝግጅት ነው።

- ነገ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ለመቆየት ከፈለግን ዛሬ ሁኔታዎች ሲቀየሩ ካልተቀየረው ከእግዚአብሔር ጋር መቆም ያስፈልጋል።

- በዙሪያችን እና በጊዜያችን ካለ ነገር ራሳችንን በማንፃት ነው የምንዘጋጀው።

- የልባችንን አቋም በማስተካከል ነው የምንዘጋጀው።

- ሰውን በሰውነት ልኩ እግዘብሔርን በእግዚአብሔርነት ልኩ ማወቅ ትህትና ነው።

- ክርስቶስ ሁለንተናችን እንዲሆን መድሀኒታችን ሀይላችን እንዲሆን ተልኳል።

- የእርሱ ገንዘብ ለመሆን ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን።

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Ararat Round About To Gurd Sholla 1 Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 18:00
Tuesday 08:00 - 18:00
Wednesday 08:00 - 18:00
Thursday 08:00 - 18:00
Friday 08:00 - 19:00
Saturday 08:00 - 18:00
Sunday 07:00 - 15:00