Aysheshim

Aysheshim

Share

18/07/2018

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላትን አነጋገሩ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 11 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላትን በፅህፈት ቤታቸው አነጋገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላቱ በእርቅና ሰላም ረገድ አርዓያ መሆን እንዳለባቸው ጠቅሰው፥ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላም የሀገር ሰላም መሆኑንም ተናግረዋል።

በቀጣዩ ሳምንት በአሜሪካ በሚኖራቸው ቆይታም ለሰላም የሚከፈልን ማንኛውንም ዋጋ በመክፈል የቤተ ክርስቲያኗ ሰላም እንዲመለስ ጥረት እንዲያደርጉም አደራ ብለዋል።

የአስታራቂ ኮሚቴ አባላቱም የእርቀ ሰላሙ ጉዞ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን ጠቁመው፥ በሁለቱም በኩል ያሉ አባቶችን በማስማማት በቅርቡ የሰላም እና የፍቅር ብስራት በኢትዮጵያ ይሆናል ብለዋል።

በኢትዮጵያም ሆነ በአሜሪካ የሚገኙት የሀይማኖት አባቶች ላደረጉላቸው ቀና ትብብርና ለሰጧቸው መልካም ምላሽም የአስታራቂ ኮሚቴው አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አስራ አንዱ የአሸማጋይ ኮሚቴ አባላት በቀጣዩ ሳምንት ወደ አሜሪካ በሚጓዙበት ወቅት የእርቅ ሂደቱን እንደሚቋጩ እና በአሜሪካ የሚገኘውን ሲኖዶስ ወደ ሃገር ቤት ይዘው እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው።

Want your business to be the top-listed Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa