Tirita Media

Tirita Media

Share

03/06/2026

የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል" ጠ/ሚ አብይ አህመድ

"ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን"።

"‎ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ።

የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፣ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን።

Photos from Tirita Media's post 03/06/2026

የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ) በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ሂደት ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው አስታወቀ።

ፓርቲው ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በምርጫው እለት ደጋፊዎቹ እንዳይመርጡ መከልከላቸውንና የምርጫ ካርዳቸው በሃይል ተነጥቆ ለሌላ ፓርቲ እንዲሰጥ መደረጉን ገልጿል።

ከምርጫው አስቀድሞም ሆነ በምርጫው እለት የአካባቢው ባለስልጣናት እና የጸጥታ ሀይሎች
በፓርቲው አመራሮች እና አባላት ላይ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ፈጽመውብናል ሲልም ፓርቲው ገልጿል።

የቁህዴፓ ፕሬዝዳት ረዳት ፕሮፌስር ገነነ ገደቡ
እንዳሉት፤ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ጭምር በድምጽ መስጫ ክልላቸው ድምጽ እንዳይሰጡ በመንግስት አካላት እገዳ ተጥሎባቸዋል።

ፓርቲው የተፈጸሙትን የመብት ጥሰቶች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለሰብአዊ መብት እና ለፍትህ አካላት ማሳወቁን ገልጾ፣ በአሁኑ ወቅት ምላሽ እየጠበቀ እንደሚገኝ አስታውቋል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Africa Avenue
Addis Ababa