Rediet Isaias,Architect

Rediet Isaias,Architect

Share

Photos from Rediet Isaias,Architect's post 26/01/2021

Black and white kitchen-Rediet isaias Arch't.

Photos from Rediet Isaias,Architect's post 05/10/2020

"Vernacular architecture" in a modern expression, Residence Interior Design by Rediet Isaias,Arch't.

'Vernacular architecture' ስንል ምን ማለታችን ነው?

*አንደኛውና ጥንታዊዉ የግንባታ(የዲዛይን) አይነት ሲሆን ይህ አይነት የግንባታ ሂደት መቼ ተጀመረ የሚለዉን ብንመለከት የሰዉ ልጅ መጠለያ እንደሚያስፈልገው አምኖ ስራ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ የሚለው ምላሽ ተቀራራቢ ሆኖ እናገኘዋለን። ይህም ማለት የህንፃ ግንባታ እዉቀት ካላቸው ሰዎች ዉጪ የሚሰራ የግንባታ አይነት ነው፡ ለምሣሌ ያኽል በአገራችን ገጠራማ አካባቤ ብንመለከት የተለያየ አይነት ዲዛይን ያላቸው ጎጆ ቤቶች ይስተዋላሉ፡ የሚጠቀሙት (material) ወይም የግንባታ ግብአት ብንመለከት በአካባቢው በብዛት የሚገኘውን እና ከተፈጥሮ ጋር ጥሩ መስተጋብር ያለው ሆኖ እናገኘዋለን። የሣር ክዳን፣የድንጋይ ቤቶች፣የእንጨት ቤቶች።

ይሁንና አሁን ባለንበት ክ/ዘመን vernacular design ከዘመናዊ የዲዛይን ስልት ጋር በማሐሀድ በህንፃ ዲዛይን ባለሙያዎች ሲሰራ ይስተዋላል።

የቨርናኩላር አርክቴክቸር ጥቅም፡

*የአካባቢውን ብሎም የአገሩን ባህል እና ልምድ በቀላሉ ለመረዳት ያስችለናል።

* በአካባቢያችን ከሚገኙ(material) ስለሚሠሩ አቅምን ያገናዘቡ ናቸው።

*የምንጠቀመው (material) ተፈጥሮ የሠጠችን ስለሆነ ማለትም(processed) የሆነ ስለማይሆን ለሚኖርበትም ሠዉ ሆነ ለአካባቢው ምንም አሢዳማ(toxic) ነገርን አይለቅም።

*አእምሮአችን ላይ ከተፈጥሮጋር የመዋሐድ ወይም የመረጋጋት መንፈስ የመፍጠር አቅም አለው፡ምክንያቱም እጅግ ተፈጥሮአዊ ስለሆነ።
የመዝናኛ ቦታዎች(Resort Hotel) ላይ ይሄ material (wood and stone) ተደጋግሞ የሚታየው ከሰዉ ሰራሽ እጅግ በጣም ያማረ (matetial) ይልቅ ተፈጥሮ የውስጥ ሰላም እና መረጋጋት ስለሚፈጥርልን ነው።

ከዚህም መካከል ቨርናኩላር አርክቴክቸርን ከ ዘመናዊ ዲዛይን ጋር በማዋሐድ የመኖሪያ ቤት(Residence interior design) በዚህ መልኩ ሰርቼዋለሁ።

ስራዎቼን አይታችሁ ከወደዳችሁት ድጋፋችሁን like,share and follow በማድረግ ስራዎቼ ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርሱ ትብብራችሁ እንዳይለየኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡ አመሠግናለሁ።🙏

Photos from Rediet Isaias,Architect's post 29/08/2020

Modern Kitchen Design - by Rediet Isaias,Arch't

Want your business to be the top-listed Home Improvement Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa