Sheger mereja

Sheger mereja

Share

08/05/2026

✨ ቅዴዎቼ እንዴት አደራችሁ✨
🌞☕️😁 አንዱ ይበቃችኋል!!🌞☕️😁
✍️ ህይወትህን ተረጋጋትህ መኖር ከፈለክ፣ ተፈላጊ፣ ተመራጭና ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን ከፈለክ አንድ ሙያ፣ አንድ ስራ ወይም አንድ ተግባር በቂህ እንደሆነ አስብ።
👇
ብዙዎች በአንድ ነገር ላይ እምነት የላቸውም፣ አንድ ስራን የመጨረሻ አማራጫቸው ማድረግ አይፈልጉም፤ በአንድ ሙያ መገደብ አይፈልጉም። በሄዱበት ሁሉ አማራጭ እንዲኖራቸው፣ አንዱ ባይሳካ ሌላው እንደሚሳካ እርገጠኛ መሆን ይፈልጋሉ። በአማራጮች ተከበው የተረጋጋ ህይወትህን መምራት ተቀዳሚ ምርጫቸው ነው። ነገር ግን እንደ አማራጭ መካከለኛ አድርጎ የሚያስቀር ነገር የለም። የተለያዩ ሙያዎች እውቀት ይኖርሃል ነገር ግን ተመረጭ አይደለህም፤ ከተለያየ ዘርፍ እውቀት ትሰበስባለህ ነገር ግን በአንደኛውም የጠለቀ እውቀት የለህም፤ ሁሉንም የተረዳህ ይመስልሃል ነገር ግን አንዱንም ለማስረዳት ብቁ አይደለህም። በአማራጮች ተከበህ ነፃ መውጣት አትችልም፤ ምቾት እያንገላታህ፣ ከየአቅጣጫው Secured ለመሆን እየጣርክ ተፅዕኖ መፍጠር አትችልም። ያማረህን ሁሉ ከማድረግ የምርም ልብህ ውስጥ ባለውና በሚያነቃህ ዘርፍ ጠለቅ ያለ ምርምር ውስጥ መግባት ይኖርብሃል።

አንዱ ይበቃሃል! ጫወታው ሁሉን ባሳደደ፣ የትም በተገኘና ሁሉንም በሞከረ አይደለም። የጀመርከውን አንድ ነገር የመጨረስ አቅምህ ምንያክል ነው? ያቋረጥካቸው ተግባሮች ብዛት ስንት ናቸው? ለጅማሬህ ያለህ መነሳሳት ለመጨረስ ከምታደርገው ጥረት ጋር ምን ያክል ይጣጣማል? ወደፊትህን በምን መልኩ ትመለከታለህ? በመጀመርህ ብቻ ሳይሆን በመጨረስህም ጭምር ምንያክል እርግጠኛ ነህ? ያየው ሁሉ፣ የሰማው ሁሉ ለእርሱ እንደሚሆንና ስኬታማ እንደሚያደርገው የሚያስብ ሰው በየትኛውም መንገድ የውስጡን እርካታ ሊያገኝ አይችልም፤ ስኬት ዘወትር የሚያሳድደው ነገር ግን የማይጨብጠው፣ ሁሌም በሰዎች ህይወት ውስጥ የሚመለከተው ነገር ግን ወደእርሱ ህይወት የማይመጣ የህልም እንጀራ ይሆንበታል። መልፋትህ ብቻ የስኬትህ ዋስትና እንዳልሆነ እወቅ።

አዎ! እራስህን ስታባክን ብኩን ማንነት፣ ያልተረጋጋ አስተሳሰብ፣ ፍፁም ያልሰከነ እይታ ባለቤት መሆንህ አይቀርም። እራሱን ለመጠብቅ እንኳን ሰዓት የሌለው ሰው ብዙ ጊዜ ከአንድ በላይ ተግባር ውስጥ በአንዴ የሚገኝ፣ እዚህም እዛም እያለ እራሱን የሚወጥር፣ ህይወቱን በሙሉ በሩጫ የሞላው ሰው ነው። ህይወትህን ተረጋጋትህ መኖር ከፈለክ፣ ተፈላጊ፣ ተመራጭና ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን ከፈለክ አንድ ሙያ፣ አንድ ስራ ወይም አንድ ተግባር በቂህ እንደሆነ አስብ። ዘለህ የማይመለከትህ ቦታ መገኘት አይጠበቅብህም፣ ሮጠህ የሁሉንም እንጀራ ካልቀመስኩ ማለት አይኖርብህም። የእራስህን እንጀራ በሚገባ ከተመገብክ ያንተን ሃላፊነት በልበሙሉነት መወጣት ትችላለህ። እራስህን ሰብሰብ አድርገው፤ ውሎህን ሰብሰብ አድርገው፤ የህይወት አቅጣጫህን መስመር አስይዘው፤ በአንዴ ሁሉም ቦታ ካልተገኘው አትበል፤ ጀግንነት የያዝከውን ይዘህ እስከመጨረሻው መጓዝ እንደሆነ ተገንዘብ።
ምርጥ ጽሁፍ✍️
*
ቅዴዎቼ አንዱ ይበቃችኋል!!! ሰናይ ቅዴ፡፡🌞
ግንቦት 01 ቀን 2018 ዓ/ም
*

01/05/2026

✨ ቅዴዎቼ እንዴት አደራችሁ✨
🌞☕️😁 ጫጬቷ ከእንቁላሉ ለመውጣት ጊዜ ያስፈልጋታል!!🌞☕️😁
✍️
ብዙ ጊዜ ሞክረህ ያልተሳካ ነገር ካለ ያ ጥረትህ ሁሉ እንደ መውደቅ ሳይሆን እንደ መደላድል ነው ማየት ያለበህ፡፡ በሞከርክ ቁጥር ወደ ስኬትህ አንድ እርምጃ እየቀረብክ እንደሆነ ታውቃለህን? ለምሳሌ እንመለከት እንቁላል በባህሪው የማይነቃነቅ፣ እግር የሌለውና ደካማ ነገር ነው። ነገር ግን ጊዜው ደርሶ ሲፈለፈል፣ ያ እግር ያልነበረው እንቁላል ወደ ጫጩትነት ተቀይሮ መራመድ ይጀምራል። ይህ የሚያሳየው የማይቻል የሚመስል ነገር በሂደት እንደሚሳካ ነው።

ማንኛውም ትልቅ ስኬት በአንድ ጀምበር አይመጣም። ጫጩቷ ከእንቁላሉ ውስጥ ለመውጣት ጊዜ እንደሚያስፈልጋት ሁሉ፣ የእኛም ህልሞች እንዲሰምሩ ትዕግስት ያስፈልጋል። ሳይታክቱ መጠበቅና በሂደቱ ማመን ለስኬት ቁልፍ ነው።

እንቁላሉ ውስጥ ያለው ለውጥ በዓይን አይታይም። ጫጩቷ እስክትወጣ ድረስ ምንም ለውጥ ያለ አይመስልም። የአንተም ስራ ዛሬ ውጤት ባያሳይ እንኳን፣ በውስጥ በኩል ትልቅ ለውጥ እየመጣ መሆኑን አትዘንጋ፡፡

"ቀስ በቀስ" ማለት ዝም ብሎ መቀመጥ ማለት አይደለም። እንቁላሉ ውስጥ ህይወት እንዳለ ሁሉ፣ አንተም በየቀኑ የምታደርገው ጥቃቅን ጥረቶች ተደምረው ወደ ትልቅ ውጤት ያመራሉ።
ተስፋ አትቁረጥ ትልልቅ ተራራዎች የሚወጡት በአንድ እርምጃ ነው። ዛሬ የጀመርከው ትንሽ ስራ ነገ ትልቅ ፍሬ ያፈራል። ከራስህ ጋር አትጣላ ለምን ፈጥኜ ውጤታማ አልሆንኩም ብለህ አትጨነቅ። የተፈጥሮ ህግ ሁሉ በሂደት ነዉ የሚሰራው።
ለዝርዝር ነገሮች ትኩረት አትስጥ በየቀኑ የምታደርጋቸው ትናንሽ ነገሮች መጨረሻ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። በዚህ መሰረት ለዓላማችን በመትጋት እንበርታ።
ምርጥ ጽሁፍ✍️
*
ቅዴዎቼ ጫጬቷ ከእንቁላሉ ለመውጣት ጊዜ ያስፈልጋታል!! ሰናይ ቅዴ፡፡🌞
ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ/ም
*

01/05/2026

ከታሪፍ በላይ ክፍያ የዜጎች የዕለት ተዕለት ፈተና ሆኗል።
***
በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች እና የክፍለ ሀገር የጉዞ መስመሮች ላይ የሚታየው ያልተገባ የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ በዝቅተኛው ማህበረሰብ ላይ ከባድ የኢኮኖሚ ጫና እየፈጠረ ይገኛል።

" የነዳጅ አቅርቦት ወደ ቀድሞ እንዲመለስ በመወሰኑ የትራንስፖርት ታሪፍ በተወሰነው ሁኔታ እንዲቀጥል " በሚል መንግሥት መልዕክት ቢያስተላልፍም በብዙ አካባቢዎች ግን ህገ-ወጥ አሰራር ነግሶ ይታያል።

ለአብነት ዛሬ ከጎንደር - ወልቃይት በነበረ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ የታየው የችግሩን ጥግ ፍንትው አድርጎ የሚያረጋግጥ ነው።

አንድ በተለምዶ " አባዱላ " የተባለውና ሰሌዳ ቁጥር 3-31010 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በህጋዊ ታሪፍ በሰው 608 ብር ማስከፈል ሲገባው እስከ 2,500 ብር (ከአራት እጥፍ በላይ) ሲያስከፍል ተገኝቷል።

ለአንድ የ4 አመት ህጻን ሳይቀር 2500 ብር ተቀብሏል።

የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መኪናውን ከያዙት በኋላ ወደ ከ34,000 ብር በላይ ለተሳፋሪው እንዲመለስ ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ምንም እንኳን ከዚህ መኪና የተሳፋሪዎች ብር ተመላሽ ቢደረግም ይህ ድርጊት በየቀኑ በብዙ መስመሮች ላይ የሚፈጸም መሆኑን ነዋሪዎች ይመሰክራሉ።

ችግሩ በጎንደርና አካባቢው ብቻ የተገደበ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ በክፍለ ሀገር ጉዞዎች ላይ የሚስተዋል አሳሳቢ ጉዳይ ነው።

በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ተሽከርካሪዎች ተሳፋሪዎችን ከጫኑ በኋላ " ባላችሁበት ካልተስማማችሁ ውረዱ " የሚል ማስፈራሪያ ያደርሱባቸዋል።

የሚጠሩት ብር ከእጥፍ እጥፍ በላይ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በላይ ደግሞ ትርፍ ስለሚጫን እንግልቱ ከፍተኛ ነው።

" ተሳፋሪው ሳይስማማ መኪናዎች አይነሱም " በሚል መርህ ህዝቡ አማራጭ ስለሌለው ብቻ ከታሪፍ በላይ ለመክፈል ይገደዳል።

በመናኸሪያዎች አካባቢ የሚገኙ ረዳቶች እና ደላሎች በመንግስት የተቆረጠውን ዋጋ ወደ ጎን በመተው የራሳቸውን ዋጋ በመጥራት ህዝቡን ክፉኛ ሲያማርሩ እየተስተዋለ ነው።

አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች ዋና ምክንያት ብለው የሚያነሱት " ነዳጅ አይገኝም ፤ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል ፤ ለነዳጅ ተሰልፈን እናድራለን " የሚል ነው። እነሱ ይህን ለማካካስ በሚያደርጉት ጭማሪ ህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እየደረሰ ይገኛል።

01/05/2026

ትራምፕ በድጋሚ ደስተኛ አይደለሁም አሉ።
***
ኢራን በዛሬው ዕለት ጦርነቱን ለማቆም በፓኪስታን በኩል አዲስ የመደራደሪያ ነጥብ ለአሜሪካ ልካ የነበረ ቢሆንም ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ሀሳብ ደስተኛ እንዳልሆኑ ገልፀዋል።
የኢራን አመራር እርስ በርሱ አልተስማማም፣ የአመራር እዙ ፈርሷል ብለዋል።

ኢራን ለኑክሌየር ያበለፀገችውን ዩራኒየም የማትሰጠን ከሆነ እኛ በሆነ መንገድ እንወስደዋለን ብለዋል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa