liyumedia.net
27/06/2026
ህወሓትን ማስወገጃው ጊዜ አሁን ነው!
ህወሃት ግጭትን ስልጣኑን ማስጠበቂያ ስልት አድርጎ እንደሚጠቀም፤ በሚቀሰቅሰው ግጭት ለሚጎዳው የትግራይ ህዝብ ምንም እንደማይጨነቅ አሁን መላው ዓለም አውቋል። ዓለም ህወሓትን የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና የሰላም ስጋት አድርጎ መመልከት ጀምሯል። ሰሞኑን በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እየተጣለበት ያለው ማዕቀብ እና እየወጡበት ያሉ መግለጫዎች የዚህ ማሳያ ናቸው። የትግራይ ህዝብ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዳለው አውቆ ህወሃትን ለማስወገድ መነሳት አለበት!
25/06/2026
የህዝብ እምባ እና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ምላሽ
የህወሃት አመራሮች በስልጣን ጥማት የፈጸሙት የጭቆና መዋቅር በዜጎች ላይ ታይቶ የማይታወቅ በደል አድርሷል። ሂዩማን ራይትስ ዎች የመሪዎቹን ህዝብ ጠልነት በተጨባጭ ማስረጃዎች ያጋለጠበት መግለጫ እና ይህንን ተከትሎ የመጣው የአሜሪካ ማዕቀብ፣ የአለም ማህበረሰብ ከጭቆና ሰለባዎች ጎን መቆሙንና የአምባገነኖችን ግፍ በዝምታ እንደማያልፈው ያሳየበት ህያው ምስክር ነው።
21/06/2026
ተኩላውን በበግ ለምድ
የአማራ ህዝብ የፋኖንና የህወሓትን ግንኙነት በከፍተኛ ስጋት እንዲመለከት ያደረገው ዋናው ምክንያት የህልውና አደጋ ስላለው ነው። ትናንት ክልሉንና ህዝቡን ለማዳከም ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልነበረው የህወሓት የፖለቲካ መዋቅር፣ ዛሬ በፋኖ ድጋፍ እንደገና ህያው ለመሆን መሞከሩ ህዝቡን «ወደ ቀደመው የጭቆና ቀንበር ለመመለስ የታለመ ሴራ» አድርጎታል። ይህ ስልታዊ ስህተት የትግሉን የሽንፈት ጉዞ ያፋጥናል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa