KALID ISLAM
አልሃምዱሊላህ
ስታርድ እዝነት ይኑርህ❗️🥺
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِنَّ اللَّهَ كَتَبَ الْإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا الْقِتْلَةَ، وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ فَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ﴾
“አላህ ኢኽሳንን (ማሳመርን) በሁሉም ነገሮች ላይ ፅፏል። የገደላችሁ እንደሆነ አገዳደልን አሳምሩ። አንዳችሁ ባረደ ግዜ አስተራረዱን ያሳምር ማረጃውን ይሳል። የሚታረደውንም እንስሳም ያሳርፍ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1955
በሌላ ሀዲስ፦
﴿جاءَ رجلٌ إلى رسول الله ﷺ فقـال: يـا
رسـول الله إني لأذبحُ الشّـاةَ وأنـا أرحمها،
فقال ﷺ : والشاةُ إن رحِمتَها رحِمَك الله﴾
“አንድ ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ (ﷺ) በመምጣት እንዲህ አላቸው፦ ‘እኔ በጌን አርጄ ለሷም እዝነትን አድርጌ ነበር’ ረሱል (ﷺ) አሉት፦ ‘ለሷ ለበግህ እዝነትን እንዳደረክ አላህ ለአንተም ይዘንልህ።’”
📚 ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 1081
✍️
❗️❗️
⊱⊰━━━━━━━⊱⊰━━━━━━━⊱⊰
18/04/2023
17/04/2023
🛑 ለይለተልቀድር ለሰጋጆችና መስጂድ ውስጥ ላለ ብቻ አይደለም🤔🤔
የወር አበባ ደም ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች...የዚች ለሊት ትሩፋት አይለፋችሁ። በዚክርና መሰል ዒባዳዎች ልትበራቱ ይገባል።በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛትም አትዘንጉ። ለይለተልቀድር ለሰጋጆችና መስጂድ ላይ ላለ ብቻ አይደለም።
ብዙ ሰው መስጂድ ካልሄደ ይሄን ምንዳ የሚያገኙ አይመስለውም። ይህ ስህተት ነው! ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው በኢባዳ ላይ መሆናችን ነው። ለቻለ እና አቅሙ ላለው ሰው ግን የተወዳጁን ነብይ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና(ፈለግ) ለመከተል መስጂድ ላይ ብንሆን ይመረጣል፣ ይወደዳል። ካልቻልን ባለንበት ቦታ ስራ ላይ የሆነም በስራው ላይ እቤቱ የሆነም በቤቱ በኢባዳ ልንበረታ ይገባል!
አላህ ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን!🤲🤲
15/04/2023
የሻም መጨረሻ»
ሻም አላህ በቁርኣኑ «ዞርያውን የባረክነው» ያለው አገር ሲሆን የዓለም መጨረሻ ክስተቶች ሁሉ የሚፈፀምበት ቦታ ነው።
ሻም ማለት በአሁኑ አከፋፈል ሶርያን፥ ፍልስጤምን፥ ጆርዳንን፥ ሊባኖስንና ከፊል ኢራቅን ያጠቃለለ ግዛት ነው።
ነቢዩ (ዐሰወ) በተለያዩ ሐዲሳቸው በሻም ስለሚከሰቱ ጉዳዮች የተረኩ ሲሆን ከእነሱ መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ናቸው፦
♦ የወደፊት የሙስሊሞች መናገሻ ይሆናል።
(አን-ነሳዒ 3561)
♦ መህዲ ኢስላማዊ ኸሊፌት ይመሰርታል።
(አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63)
♦ ደጃል ይነሳበታል። ከየሁዶችም የተወሰኑ ይከተሉታል።
(ቲርሚዚ፥ 2244)
♦ ዒሳ (ዐሰ) ሻም ደማስቆ አቅራቢያ በመውረድ ደጃልን ይገድለዋል።
(ሙስሊም፥ 2937)
♦ ሙስሊሞች የሁዶችን ያጠፉበታል።
(ቡኻሪ፥ 2926)
♦ የመጨረሻዎቹ ሙስሊሞች ይኖሩበታል።
(ቲርሚዚ፡ 2183)
♦ አላህ ከሻም የምትነሳ ነፋስ በመላክ የመጨረሻዎቹ ዘመን ሙስሊሞች በሙሉ እንዲሞቱ ያደርጋል።
(ሙስሊም፥ 2940)
♦ አላህ የቂያማህ ቀንን ፍርድ ይሰጥበታል።
(ተፍሲር አልቁርጡቢ 17/31)
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Meskel Square
Addis Ababa