Fre Habeshawit

Fre Habeshawit

Share

28/05/2020

በ2012ዓ/ም ምድራችን የሚገጥሟት ከባባድ ፈተናዎች በመጋቤ ሀዲስ ሮዳስ
ምድራችን በእኛ አቆጣጠር በ2012 ዓ/ም በፈረንጆቹ 2020 ዓ/ም በከባድ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈች ነው፡፡ እጅግ ጥንታዊው ከ1200 ዓመታት በፊት በነበረው የማያ ዘመን ቀመርአዲስ ያልተለመደ ክስተት የሚጀምርበት ዑደቱ የሚጠናቀቅበት የተፈጥሮ አደጋዎች በዝተው የሚታዩበት 2012 ላይ መሆኑን የሚያሳይበመሆኑ ብዙ አለም አቀፍ ተመራማሪዎች በፈረንጆቹ 2012 ላይ መስሏቸው ብዙ አስተያየት በጊዜው ሲሰጡ ቆይተው ነበር፡፡2012 የሚል አስፈሪ ፊልም ከማያ የዘመን ቀመር በመነሳት የፈረንጆች 2012 ከመድረሱ 3 ዓመት ቀድሞ 2009 ላይ በሆሊውድ ተሰርቶ በሮናልዶ ኤመሪክ ተዘጋጅቶ ሁላችንም ተመልክተናል፡፡
ነገር ግን በፈረንጆቹ 2012 ምንም ሳይከሰት በኛው 2012 ዓ/ም ደርሷል፡፡ የኛው 2012 ዓ/ም ግን ገና ከጅምሩ ለአለማችን አስደንጋጭ ሆኗል፡፡በዚህ አመት ምድራችን የገጠሟት በርካታ ነገሮች ቢሆኑም ከነበሩት አስደንጋጭ ጉዳዮችና በዚህ አመት ከሚያጋጥሟት ዋና ዋናዎቹን ክስተቶች በጥቂቱ መርጬ እፅፋለሁ፡፡
1ኛው ከፈረንጆቹ የልደተ ክርስቶስ በዓል አስቀድሞ እጅግ አውዳሚና አደገኛ 310442(2000ch59)የተባለው ግዙፍ አስትሮይድ(አለት) ከፈረንጆቹ ገና (christmas) በፊት ታህሳስ 16 (December26) በእኛ 4፡54 ወይም 2፡54 am Est ላይ ምድርን አልፏት መሄድ ነበር፡፡ ይህንንም ኢንዲፔንደንት የገና ተአምር በሚል አስነብቦ ነበር ፡፡ይህም አለት ቢወድቅ ኖሮ በኒውዮርክ የሚገኘው1792 ጫማ የሚሆነውን ትልቁን የመገበያያ ማዕከል(Trade center) የሚበልጥ ነበርና ምድር ላይ ከባድ ሱናሚ ያስከትል ነበር፡፡
2ኛው በ2012ዓ/ም ላይ ከመስከረም ጀምሮ እስከ ጥር የተከሰተው ሌላው እጅግ ከባድ የነበረው የአውስትራሊያው ሰደድ እሳት ነበር፡፡ይህ ከባድ እሳት 18.6 ሚሊየን ሄክታር(46 ሚሊየን ኤከር 186000 ስኴር ኪሎ ሜትር 72000 ስኴር ማይልስ) ሲሸፍን 5900 ህንፃዎችን ጨምሮ 2779 ቤቶችን አውድሟል በተጨማሪም የ34 ሠዎች 1ቢሊየን እንስሳትን ገድሎ ማለፉን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
3ኛው ከቻይና ሁዋን እንደተቀሰቀሰ የሚነገርለት የኮሮና ቫይረስ Covid-19 ወረርሺኝ በመላው አለም ግስጋሴውን እየጨመረ ዓለማችንን ከባድ ስጋት ላይ ጥሏታል በእድሜያችን አይተነው በማናውቀው መልኩ በረራዎች ቆመዋል ድንበሮች ተዘግተዋል መላው አለም በአሁኑ ሰአት በጭንቀት ተውጣለች፡፡
4ኛው ቀጣዩ የዚህ አመት የአለማችን ስጋት የሚቀጥለው ወር ሚያዚያ21 (April 29)2012 ዓ/ም የኤቨረስት ተራራን የሚያህል 52768(1998IR2) ተብሎ የተጠራ ግዙፍ አስትሮይድ (አለት) ከሰማይ በሰአት 19.461 እየበረረ ከመሬት በ3,908,791 ማይልስ ርቀት ምድርን ማለፉ ነው፡፡ ቢወድቅ ምድርን ሊጎዳት የሚችለው ይህ አውዳሚ አለት መድርን ስቷት ይሄዳል እንጂ አይነካትምና ተረጋጉ የሚል መልዕክቶች ከናሳ እየወጡ የገኛሉ፡፡
5ተኛ በዚህ አመት እጅግ በዝቶ በምስራቅ አፍሪካ እና አረብ ሀገራት ከየመን የተነሳው የአንበጣ መንጋ እህልን በከፍተኛ ሁኔታ አውድሞ ማለፉና ሄደ ሲባል እንደገና እየተፈለፈለ መምጣቱ ከባድ ነው፡፡
ከሀገራችን ከኢትዮጵያ ጋር ተያይዞ የ2012 ልዩ ክስተት የሚሆነው (June 21)2020 በእኛ አቆጣጠር ሰኔ 14/2012 ዓ/ም ቀለበታዊ የፀሀይ ግርዶሽ ኢትዮጲያ ውስጥ ከምዕራብ ኢትዮጲያ አንስቶ እስከ ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ መታየቱ ነው፡፡ ክስተቱም ወለጋ አካባቢ ጀምሮ ከፊል ጎጃምን ከፊል ጎንደርን አልፎ ወደ ወሎ በተለይ ላሊበላ አካባቢ ድረስ ስለሚታዩና ቀኑ የሚጨልምበት ስለሚሆን በህይወት ዘመናች ልናየው የምንችለው አስደማሚ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በይበልጥ ለማወቅ በአንድሮሜዳ መፅሐፍ ላይ የተፃፈውን ማንበብ ትችላላችሁ፡፡
እግዚያብሔር ምድራችንን ከክፉ ነገረ ይሰውርልን ዓመቱን በሰላም ያሳልፍልን፡

Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa