Ethio-Mereja

Ethio-Mereja

Share

Photos from Ethio-Mereja's post 10/10/2020

የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ፡፡
ፓርኩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መርቀው ከፍተውታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ በፓርኩ በተለያዩ የስራ መስኮች ለተሰማሩ ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በፓርኩ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ከ460 በላይ በአካባቢው የሚገኙ እናቶችም የስራ መስሪያ ቦታቸውን ቁልፍ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ተረክበዋል፡፡
(fbc)

08/10/2020

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ5000ሜ የአለም ክብረወሰንን ሰበረች!

የ22 ዓመቷ ለተሰንበት ከደቂቃወች በፊት በስፔን ቫሌንሺያ ስታዲዮ ዴል ቱሪያ ባደረገችው የክብረወሰን ውድድር 14:06.65 በመግባት ከዚህ ቀደም በሀገሯ ልጅ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በ14:11.15 ከ12 ዓመታት በፊት ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን አሻሽላለች።

30/09/2020

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም አረፉ

የጂኦግራፊ ምሁሩ ፐሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በ90 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል፡፡
ፐሮፌሰር መስፍን በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ታሪክ ዙሪያ በርካታ መጽሐፍትን የጻፉ እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ምሁር ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፕሮፌሰሩ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የሐሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻቸው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል” ያሉ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
(አል ዐይን)

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa