Melat kolefa

Melat kolefa

Share

Photos from A.A Housing Development & Administration Bureau's post 17/09/2024
10/09/2024

ለመላው የሀገራችን ህዝቦችና የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ለ2017 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ተቋማችን ቤት በመገንባት በማስተላለፍ እና በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር የተቋቋመ ሲሆን ላለፉት 20 አመታት ከ350 ሺ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፤ ከ152 ሺ በላይ የመንግስት ቤቶች በማስተዳደር ፤ ከ160 ሺ በላይ በተለየዩ ቤት አልሚ አካላት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር በማድረግ ፤ በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ ከ120 ሺህ በላይ እየለሙ ያሉ ቤቶችን ቢሮው በልዩ ሁኔታ እና በጥብቅ ዲሲፒሊን በመከታተልና ከ35ሺ በላይ ቅን ልቦና ባላቸው በጎ ፍቃደኞች የለማውን ቤት በተለወጠ አስተሳሰብ በማስተባበር ለከተማችን እድገት የራሱን አሻራ ከማኖር አንጻር እየተጋ ይገኛል፡፡

ከዚህም ባሻገር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማበልጸግ የመንግስት ቤቶችንና የጋራ መኖርያ ቤቶችን መረጃ በማደራጀት ፣ በማስተዳደር እና በመቆጣጠር የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በማዘመን እንዲሁም አዳዲስ የቤት ልማት አማራጮችን በመቅረጽና እንዲተገበሩ በማድረግ በከተማችን ያለውን የመኖርያ ቤት እጥረት ለመቅረፍም ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ በመሆኑ ደስታ ይሰማናል፡፡

በቀጣይም የከተማችን ነዋሪዎች ይበልጥ ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን የቤት ልማት አማራጮችን በማጠናከር አገልግሎታችንን የበለጠ በማዘመን እስከዛሬ የተገኙ ስኬቶችን አጠናክረን ለማስቀጠል ቃል በመግባት መጪው አዲስ ዓመት የሰላም ፣ የስኬትና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ

Want your business to be the top-listed Grocery Store in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa