Abelpappy

Abelpappy

Share

18/12/2024

በሚንሳፈፍ በረዶ ላይ የተኛ ድብ የዓመቱ ምርጥ የዱር እንስሳት ፎቶግራፍ አሸናፊ ሆነ

በሚንሳፈፍ በረዶ ላይ የተኛ ድብን የሚያሳይ ድንቅ ፎቶ ያነሳው እንግሊዛዊ የዓመቱ ምርጥ የዱር እንስሳት ፎቶግራፈር ሽልማትን አሸንፏል።

ጀማሪ የፎቶ ግራፍ ባለሞያ የሆነው ኒማ ሳሪካኒ ሽልማቱን ለማሸነፍ የበቃው በዓመቱ ከተነሱ ውብ እና ጠንካራ መልዕክት ካላቸው የዱር እንስሳት ፎቶዎች ውስጥ በህዝብ ድምጽ ከፍተኛ ውጤት በማግኘት ነው።

ፎቶው እንስሳት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ጋር ያላቸውን ጥብቅ ቁርኝት በማሳየት ምድራችን በዓየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተጋረጠባትን ከባድ አደጋ በጥልቀት እንደሚያስረዳም የእንግሊዙ የተፈጥሮ ታሪክ ሙዚየም ዳይሬክተር ዶ/ር ዳግላስ ጉር ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ የዓለም ሙቀት መጨመር ግግር በረዶን በማቅለጥ በሰዎች እና በእንስሳት ላይ የህልውና አደጋ መደቀኑንም ገልጸዋል።

ኒማ ሳሪካኒ ፍቶውን ለማንሳት ኖርዌይ ውስጥ በሚገኙት እና የአርክቲክ ውቅያኖስ አካል በሆኑት የስቫልባርድ የበረዶ ደሴቶች ለ3 ቀናት እንደተጓዘም ቢቢሲ ዘግቧል።

Want your business to be the top-listed Photography Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa