BC Enlightenment
19/05/2026
ይህ በ 11/09/2018 ዓም በኦሮሚያ ክልል በፍቸ እና ገብረ ጉራቻ መሀከል አሊደሮ ከተማ ወጣ ብሎ የታጠቁ ወንበዴወች ተኩስ ከፍተው ጎማ መስታውት መተው በማስቆም ታሳፋሪወችን አፍነው ወስደዋል የሚል መልዕክት ደርሶናል።
ሌላው ተሳቢ ጎማ መስታውቱ በጥይት ተመቶ ሾፌሩ ተጎድቷል የሚል መልዕክት አለ ይህ አውቶብስ ከፊት በጥይት እንዴት እንደተመታ ይታያል ከመስትውቱ ባለፈ ዙሪያውን መመታቱን ገልፀውልናል።
ወደ ህዝብ ጥይትን የሚተኩሱ በተደጋጋሚ እገታ ግድያን የሚፈፅሙ ሙሉ ተሳፋሪን አፍነው ስልክ ተደዋውለው ተደራድረው የሚኖሩ ወንበዴወችን ከመስመሩ ማፅዳት አነፍንፎ ይዞ በህግ መቅጣት ባለመቻሉ ያሻቸውን እንዲያደርጉ እድል ፈጥሯል።
ይህ የመንገድ ክፍል የዘራፊ መፈንጫ መሆኑ ይታወቃል 43 ኪሎ ሜትር መንገድ መቆጣጠር አለመቻል ሾፌር ተሳፋሪ እንዲታፈን እንዲገደል እያደረገ ይገኛል መንገዱ በአገልግሎቱ እና በችግሩ ግዝፈት ልክ ጥበቃ እና ትኩረት ሊደረግለት ይገባል።
ፍትህ
17/05/2026
''ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ እየመጡ በኢትዮጵያ እድገት እና ለውጥ እየተደመሙ ነው'' አዲስ አበባ ብቻ ኢትዮጵያ ናትን?
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተለያዩ ጊዜያት በሚያደርጓቸው ንግግሮች፤ ዓለም በኢትዮጵያ እድገት እና ለውጥ ቢደመምም በርካታ ኢትዮጵያውያን ግን የተሰራውን ስራ በቅጡ ለመገንዘብ እና ለማድነቅ እንደሚያዳግታቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ቅዳሜ ግንቦት 8፤ 2018 በተካሄደ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ላይ ባደረጉት ንግግርም ይህንኑ አቋማቸውን ደግመውታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ንግግሩን ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንዳነሱት ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ሰዎችን ያስደሰተ ያሉትን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት አንስተዋል።
ኢትዮጵያ 10.2 ፐርሰንት የምታድግ ብቸኛ አገር ናት ያሉ ሲሆን በድፍን አፍሪካ 10.2 ፐርሰንት እድገት የሚያድግ አንድም ሃገር የለም ብለዋል።
አዲስ አበባ ብቻ ኢትዮጵያ ናትን?
ሀሳብዎን ያካፍሉን?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Addis Ababa