EAS

EAS

Share

17/05/2026

369

የደስታ ምሽቶች!

ዕለተ እሁድ ግንቦት 09 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

ትናንት በተለያዩ አህጉሮች የፍፃሜ ጨዋታዎች ተከናውነው አሸናፊዎቹ ተለይተው ታውቀዋል።

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የአልጄሪያው USM Alger ዛማሌክን አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በኤሺያ ቻምፕየንስ ሊግ 2 የሮናልዶው አል ናስር በጃፓኑ ጋምባ ኦሳካ ተሸንፎ ዋንጫውን አጥቷል።

ማን ሲቲ ቼልሲን በማሸነፍ በውድድር አመቱ ሁለተኛ ዋንጫውን አሳክቷል።

በስኮትላንድ አዲስ አሸናፊ አልተገኘም።ሴልቲክ የመጨረሻውን ጨዋታ ኸርትስን አሸንፎ ጣፋጭ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

ዛሬ በቆይታችን እነዚህ የፍፃሜ ምሽቶችን እንዳስሳለን።

የእለቱ የፕሪምየርሊግ ጨዋታ

👉 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ፎረስት
👉 ኒውካስትል ከ ዌስትሀም

የብሩኖ የአሲስት ሩጫውን አጠናክሮ ይቀጥል ይሆን?

ፕሪምየሬሊጉ የዛሬ ሳምንት ይጠናቀቃል።የውድድር አመቱ ኮከብ ተጨዋች ለናንተ ማን ነበር?

ማን ያሸንፋል?በኮሜንት ሳጥን ሀሳባችሁን አካፍሉን

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

10/05/2026

368

4 ወር ሙሉ ሽንፈት ያልቀመሰው ቦርንማውዝ!

ዕለተ እሁድ ግንቦት 02 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

የሊግ ውድድሮች የሚጠናቀቁበት እንዲሁም የአውሮፓ የክለቦች አሸናፊዎች የሚታወቁበት የመጨረሻ ወር ላይ ተገኝተናል።

ክለቦች ረጅሙን የውድድር ጊዜ አሳልፈው ወደ እረፍት ሊያቀኑ ተቃርበዋል።

የውድድር አመቱን ለማጠናቀቅ ባልተገመተ ቦታ ላይ ከተገኙት ውስጥ ቦርንማውዝ አንዱ ነው።

ያለፉት አራት ወራት በፕሪምየርሊጉ ጨዋታ ላይ ሽንፈት የሚባል አልቀመሰም።በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ስድስተኛ ቦታን ይዟል።

ዛሬ በቆይታችን ከሌሎች አጫጭር ጉዳዮች ጋር አድርገን የምናነሳው ርዕሳችን አድርገነዋል።

ትናንት በአውሮፓ የሊግ ጨዋታዎች ተደርገዋል

👉 ሲቲ ቢያሸንፍም የ3-0 ድሉ ጨዋታውን የሚገልፀው አልነበረም።

👉 ማንችስተር ዩናይትድ ግቡን በጊዜ አሳክቶ ለመርሀግብር ማሟያ የሚመስል ጨዋታ አድርጎ አቻ ተለያይቷል።

👉 ሊቨርፑል እና ቼልሲ ነጥብ ተካፍለዋል።

ዛሬ

ዌስትሀም ከአርሰናል
ቶተንሀም ከ ሊድስ
ባርሳ ከ ሪያል ማድሪድ

ማን ያሸንፋል?በኮሜንት ሳጥን ሀሳባችሁን አካፍሉን

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

08/05/2026

367

ግጭት!

ዕለተ አርብ ሚያዝያ 30/2018 የኢትዮአዲስ ስፖርት የእኛና የእናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 አየር ላይ ይቆያል።

ሳምንቱ የግጭት ነበር። በተለያዩ ክለቦች ተጫዋች ከተጫዋች ፣ተጫዋች ከአሰልጣኝ ፣ አሰልጣኝ ከክለብ አመራር ጋር መጋጨታቸውን ደግመን ደጋግመን ሰምተናል። የስፔን ኃያል የሆነው ሪያል ማድሪድ ደግሞ በልዩነት በዚህ ጉዳይ ስሙ የተነሳው ክለብ ነው።

ከወደጣልያን ግን ሌላ አዲስ መረጃ ወጥቷል። ቀይና ጥቁሮቹ(ሮሰኔሪ) ኤሲ ሜላኖች ቤትም ይኸው እሳት ገብቷል። የቡድኑ አሰልጣኝ ማክሲ አሌግሬ እና ጥበበኛው የመስመር ተጫዋች ራፋኤል ሊያዎ ያላቸው ግኑኝነት ንፋስ እንደገባበት መነገር ጀምሯል። የዚህ ግጭት አንድምታ ምንድነው? በቀጣይስ ምን ሊፈጠር ይችላል? የዛሬ የትኩረት ነጥባችን ነው።

የሳምንቱ መጨረሻ እጅግ ወሳኝ በሆኑ የሊግ ጨዋታዎች ተመልሷል። በእንግሊዝ ፕ/ሊግ መሪው አርሰናል በለንደን ደርቢ ዌስትሐምን ሲገጥም ማን.ሲቲ ከብሬንትፎርድ ይፋለማል።

✅ሊቨርፑል ከቼልሲ
✅ሰንደርላንድ ከማን. ዩናይትድ

ሌሎቹ የሚጠበቁ መርሃ ግብሮች ናቸው።
በስፔን ላሊጋ በኤል-ክላሲኮ ባርሴሎና ከሪያል ማድሪድ ጋር ሻምፒዮንነቱን ሊያረጋግጥ የሚችልበትን ጨዋታ ያደርጋል።

በጣልያን ሴሪ ኤ ሻምፒዮንነቱን ያረጋገጠው ኢንተር ሚላን ወደሮም አቅንቶ ከላዚዮ ሲጫወት ኤሲሚላን ከአታላንታ፣ቬሮና ከኮሞ፣ሌቼ ከጁቬ ይፋለማሉ።

በእነዚህና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ሐሳባችሁን በኮመንት አስቀምጡልን።

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

03/05/2026

366

ሻልከ 04 ተመልሷል።

ዕለተ እሁድ ሚያዝያ 25 /2018 ዓም የኢትዮ-አዲስ ስፖርት መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ አየር ላይ ይውላል።

በጀርመን ቡንደስሊጋ የኃያልነት ታሪክ ካላቸው ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ሻልካ 04 ከሶስት አመት ቆይታ በኋላ ዳግም ወደሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ እርከን ተመልሷል። ከዚህ ቀደም በኃያላን ክለቦች የምናውቃቸው አንጋፎች የስኬቱ ቁልፍ ነበሩ።

ዛሬ በቆይታችን ከሌሎች አጫጭር ጉዳዮች ጋር አድርገን የምናነሳው ጉዳይ ነው።

ትናንት በአውሮፓ የሊግ ጨዋታዎች ተደርገዋል

👉 አርሰናል መሪነቱን ወደ6 ነጥብ ማስፋት ችሏል።

👉 ባርሴሎና ለሁለተኛ ተከታታይ አመት የላሊጋ ሻምፒዮን መሆናቸውን ያስረገጠ ውጤት አስመዝግበዋል።

👉 ኤፕስዊች ዳግም ወደፕሪምየር ሊግ አድጓል።

👉 የወራጅ ቀጠና ፉክክር በየሊጎቹ ተፋፍሟል።

ዛሬ

ሊቨርፑል ከማንችስተር ዩናይትድ

ነገ

ኤቨርተን ከማን.ሲቲ ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ።

ማን ያሸንፋል?በኮሜንት ሳጥን ሀሳባችሁን አካፍሉን

- የሚሳተፉበትና የሚዝናኑበት

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Lideta
Addis Ababa