Abiy Ephrem - PR Director

Abiy Ephrem - PR Director

Share

Photos from Abiy Ephrem - PR Director's post 01/05/2017

በሰሜን ጎንደር ዞን የመስክ ምልከታ እና የነዋሪዎች ምክክር . . .

Photos from Abiy Ephrem - PR Director's post 01/05/2017

"በአመራሩና በማህበረሰቡ መካከል የሚደረግ የገፅ ለገፅ ውይይት ለላቀ የዕድገት ጉዞ ወሳኝ ነው!"

ምክትል ጠቅላይ ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሰሜን ጎንደር ዞን ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ መንግስት የህዝቡን የልማት አምሮት ለማርካት በዕቅድ ዘመኑ በትኩረት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አቶ ደመቀ ጠቁመው ህዝብ እና መንግስት በየደረጃው ተቀራርበው መወያየት መቻላቸው ለላቀ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

የየወረዳው ነዋሪዎች በውይይቱ ላነሱት የመሰረተ ልማት እና የልማት ጥያቄዎች የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በየደረጃው በአመራሩና በማህበረሰቡ መካከል የሚደረግ የገፅ ለገፅ ውይይት ለላቀ የዕድገት ጉዞ ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ~ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

Photos from Abiy Ephrem - PR Director's post 30/04/2017

Gonder ~ "City Of Camelot"

Photos from Abiy Ephrem - PR Director's post 28/04/2017

በ~አብይ ኤፍሬም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጠገዴ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ። ውይይቱ ከጠገዴ ወረዳ ወሰን መካለል እና ከአካባቢው ልማት ጋር በተያያዙ ዓበይት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ነበር።

ነዋሪዎቹ ወሰን የመካለል ሂደቱ ጊዜ መውሰዱን በማስታወስ በአሁን ጊዜ መንግስት በሰከነ አግባብ የአከባቢውን ማህበረሰብ በማወያየት ለጉዳዩ ዘላቂ እልባት ለመስጠት እያደርገ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል። በተለይ በውይይቱ ላይ የጠገዴና የአከባቢው ወረዳዎች በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር በመንግስት በኩል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው የወሰን መካለል ሂደት በመንግስት በኩል ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን በመጠቆም ጉዳዩን ለመቛጨት ድንበሩ የሚካለልባቸው ማህበረሰቦችን የዘላቂ መፍትሄው አካል ለማድረግ በቅርበት ማወያየት ጠቃሚ መሆኑን አስረድተዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር መሰል የውይይት መድረኮች በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ደመቀ ተናግረዋል። የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በዕቅድ መሰረት በአፅንኦት እንደሚከናወኑ አስረድተዋል።

Photos 05/11/2015
Photos 29/06/2015

“. . .ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን የማስቀረት አጀንዳ ከሚያስከትሉት ከባድ ጉዳት እና ከሚያስከፍሉን ያልተገባ ዋጋ አንፃር በተግባር እያዳበርን የመጣነውን ህብረታዊ ቅንጅት አጥብቀንና ጠብቀን ማስቀጠል ይኖርብናል፡፡”

የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa
1293