Sumayyaa

Sumayyaa

Share

17/08/2023

አዋጅ አዋጅ አዋጅ

~ ጉዳዩ:- የሥራ ኃላፊነትን በፍቃዴኝነት ስለመልቀቅ

ውድ የቆቀማ ማህበረሰብና የቆቀማ ማዕከላዊ ኮሜቴዎች በሙሉ እስከ ዛሬ "በጸረ ቆቅማና አሀዳዊ የባትማ ኃይሎች ትግላችን በፍጹም አይቀለበስም!" በሚል መሪ ቃል ማህበረሰባችንን ሥመራ መቆየቴ ይታወቃል። ሆኖም ዛሬ የሥራ ኃላፊነቴን በፈቃዴ የለቀቅሁ መሆኔን እንዲታውቁልኝ ለማስገንዘብ እወዳለሁ!

ለዘመናት በቆሞ ቀርነት ጸንታችሁ ለኖራችሁ ውድ የቆቀማ ማህበር ታማኝ ደጋፊዎችና ብሶት የወለዳችሁ የላጤ ማህበረሰብ አባላት በሙሉ በዛሬው እለት ማህበራችን እንዲያውቅልኝ የምፈልገው ነገር፤ ይህን አፍዝ አደንግዝና አንገዝግዝግ ቆቀማ ለቅቄው ለመሄድ መገደዴን ነው። እናንተም አስቸኳይ ኢ-መደበኛ ጉባዔ አድርጋችሁ ከጫካ የትጥቅ ትግል ጀምሮ ለረዥም ዘመናት አላገባም፣ አልዳርም አልኳልም በማለቴ ብዙ ድል ሳስመዘግብ የነበርሁ ግምባር ቀደም ታጋይና መሪ መሆኔን የሚገልፅ የሽኝት ደብዳቤ እና የአገልግሎት ጥቅማ ጥቅም በማህበሩ ሥራ አስፈጻሚነት እንዲወሰንልኝ ለማሳሰብ እፈልጋለሁ ። አይ ካላችሀ ብዙ የቆቀማ አባላትን የማስኮብለል ሸፍጥ እሰራለሁ።

እናም እኔ ወ/ሪት ሱመያ በደህና ከሚኖርበት የቁሞ ቀርነት አፍዝ አደንግዝ አንገዝግዝ ህይወት በማናለብኝነት በመውጣቴና ለትዳር (ባትማ) የባለ ትዳር ማህበር እጄን ልሰጥ በመሆኔ ማህበሩ ቆራጥ እርመረጃ እንዲወስድብኝ እና ሽኝት እንዲያደርግልኝ ስል በእውነቱ እንባ እንባ እያለኝ አሳስባለሁ። ከዚህ በፊት ማህበሩ በነበረው ግምገማ ይሄ ንግሥተ ነገሥት ወቆቀማ ምንም ስጦታ፣ ቁልምጫ፣ እንጥጫ፣ ግብዣ፣ ጅንጀና ጅኒጃንካ የሚሉትን ጸረ ቆቅማዊ አካሄድ ያላስተናገድሁ መሆኑ ግምት ውስጥ ገብቶ ለተተኪ ቆቀማውያን ጥሩ ምሳሌ መሆኔንም እንዲታውቃልኝ እሻለሁ።

ያው በቆቀማውያን እይታ ትዳር አስከፊ የመጣመርና ቃል ኪዳን የማሰር ጎጂ ባህል ህዝባችን ላይ ለዘመናት የተጣበቀ ኮሶ መሆኑን በማመን ማህበራችን ሲታገልበት የቆዬ ጉዳይ መሆኑን ባቅም እጅግ ውብና የተቀደሰ ነገር ትዳር መሆኑን ስላመንኩ ከዚህ በኃላ ቆቀማን ለማታገል ቆርጨ የተነሳሁ መሆኑንም ልብ እንዲታደርጉልኝ እፈልጋለሁ።

የቆቀማ ማህበረሰብ ማዕከላዊ ኮሚቴ "በጸረ ቆሞቀርነትና ላጤነት ኃይላት ተጠልፈው ለዚህ በመዳረጋቸው ስማችንን ያዋረደ ተግባር ነው" ሲሉ ደብደቤ የጣፋልኝ ቢሆንም ይህ የክፋዎች ሴራ እኔን በጭራሽ እንደማያቆመኝ ስናገር በኩራት ነው።

እናም በዛሬው እለት ሁሉም የቆሞ ቀሮች ማህበር ቆቀማ ምክር ቤት አባላት፣ ለቆቀማ ደጋፊዎችና ለቋሚ የፍቺ ነጻነት ግንባር ፓርቲዎች ወደ ባትማ ላቀና መሆኑን ለማሳወቅ እገደዳለሁ። በዚህም መሠረት ተተኪ ሻሚዎች እና ቆቀማዎች ሥልጣናቸውን እስኪያደላድሉ ድረስ በበጎ ፍቃድ ማህበሩን የማግዝ መሆኑ ይታወቅልኝ እያልኩ ከታች ያለውን አቋም መግለጫ እሰጣለሁ!

1ኛ ቆቀማን በምክትልነት ሲመሩት የነበሩት አቶ የኑስ የዘመናት ላጤነታቸውንና ለአንዳንድ ጸረ ቆቅማ ሴቶች የትዳር ማባበያ ሽንገላ የማይታለሉ የለየላቸው ቆሞቀር መሆናቸውን በማዬትና በዘርፉ ያላቸውን ልምድ ከግምት ውሰጥ በማስገባት ይህንን ፓርቲ እንዲመሩ ስል በትህትና እጠይቃለሁ።

2ኛ አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ይህንን ተነጥለህና ተገልለህ ለየብቻህ በላጤነት ኑር የሚለውን የኮንፌደሬሽን መርህን ለማዳከም የሚያደርጉት ጥረት በፍጹም እንደማይሳካላቸውና ማህበሩ ወደፊት ሚሊዮኖችን አስቁሞ ከማስቀረት የሚያስቆመው ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ለመግለጽ ቢፈለግም ፈፅሞ አይሳካላቸውምና ድል ለባትማ።

ከወዳጅ አገራት በምናገኘው ዓመታዊና ስልታዊ ድጎማዎችም የፍቅር አዝማሚያዎችንና መተጫጨቶችን ባጭሩ እንዳይቀጩ ለባትማ ተግተን እንሠራለን። እንዲሁም ማህበራችንን ለማፍረስ በማሰብ በእምነትና መሰል ተቋማት ፋሽሽታዊና ድብቅ አጀንዳ የተመሰረተውን ባትማን (ባለትዳር ማህበር ሚኒስቴር መስሪያ ቤትን) ከስሩ ለመንቀል የሚታገሉ አካላትን የማንታገስ መሆኑን እንዲታውቁልን!

3ኛ ማህበራችን በቀጣይ የተሳካ ትግል ያደርግ ዘንድና ለመላው ባትማ መብት ይታገል ዘንድ በአገሪቱና በመላው ዓለም የምትገኙ ባትማዎች ጥሪ እናቀርባለን።

እንዲሁም ጸጉራችሁ ገባ ገባ ያለ ጎልማሶች፣ ወጣት መሳይ ሽማግሌዎች፣ ሴት ባይኔ አታሳዩኝ የምትሉ ፈላስፋዎች፣ ወንድ በዞረበት ዞሬ አልተኛም የምትሉ ሴቶች፣ ትዳር የሰውን ልጅ ማፍዘዣና ማሰቃያ እንዲሁም ማናጠቢያ ማዕከል መሆኑን በጽኑ የምታምኑ አርቆ አሳቢ ጀዝቦች፣ በአጠቃላይ ለመላው ላጤ አደር ወንዶችና ሴቶች ወደ ባትማ ማህበራችን ጎን እንድትሆኑና አብረን ቆቀማን እንድንታገል ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን።

"ባትማ እንደ ቆቀማ በመሰሉ ጸረ ባትማዎችና የትዳር ሽብርተኞች አይደናቀፍም!"

"ለዘመናት ከላያችን ላይ ተጣብቆ የቆየውን ቆሞ ቀር የሚሉትን የአፍዝ አደንግዝ ተላቀን ወደ አህዳዊ ባትማ ስንቀላቀል፤ የጨፍልቀህ አብኩተህ አካክተህ አጣምረህ ግዛ መርህን በፍቅር ተቀብለን ነው!

ድል ለባትማ፤ ምርኮ ለአፍዝ አደንግዝ አንገዝግዝ የቆቅማ ስርዓት"

እጩ የባትማ ንግሥተ ነገሥት ሱመያ

አዲስ አበባ

19/07/2023

Qabaan rabbii cimaadha
Najaa nuhaa baasu.

17/07/2023

ሽንኩርት፣ድንች እና ጎመን ሳይጨምር ነው አደለ 500.....?

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Lidata
Addis Ababa