Daregot Media
30/06/2021
የመጀመሪያው የዳረጎት ዘተዋሕዶ የወረቀት ህትመት መጽሔት ለአንባቢዎች ሊቀርብ ነው።
''አለቃ መሠረት'' የተሰኘውና የዳረጎት ሚዲያ አባላትን ጨምሮ በርካቶችን በማስተማር መሠረት በሆኑት መጋቤ ምሥጢር መሠረት ተሰማ የሕይወት ታሪክ፤ የጿፏቸውን የሥነ-ጹሑፍ ሥራዎች፤ የተደረሱላቸውን ቅኔያት፤ የልጆቻቸውን ምስክርነትን የያዘ መጽሔት ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን ሊቀርብ ነው።
በመጽሔቱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መንበረ ፓትርያሪክ ጠ/ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊና የአርሲና የምሥራቅ ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ጨምሮ የሀገረስብከቱ ከፍተኛ አመራሮችና አባቶች መልዕክት አስተላልፈዋል።
በ48 ገጾች የተዘጋጀው የዳረጎት ዘተዋህዶ መጽሔት ልዩ ዕትም ስለ መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሰረት ተሰማ ተነግረው የማይጠገቡና ለጆሮ አዲስ የሆኑ ታሪኮችን በውስጡ አካቷል።
በጽሔቱ በ700 ቅጂ ለህትመት የሚበቃ ሲሆን ከፊታችን አርብ ጀምሮ በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን የአባታችንን የ፵ ቀን መታሰቢያ አስመልክቶ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ በይፋ ተመርቆ ለአንባቢያን ይቀርባል።
በዚህ የመታሰቢያ ጉባኤ ላይ ታላላቅ መምህራነ ወንጌልና ዘማሪያን እንዲሁም ተማሪዎቻቸው ይገኛሉ። በህይወት ታሪካቸው ላይ ያተኮረ አጭር ዶክመንተሪም ለዕይታ ይበቃል። ዳረጎት ሚዲያ በአሰላ ከተማና አከባቢዋ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ በዚህ ትልቅ ጉባኤ ላይ ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ ያቀርባል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
1000