Tzu dire
29/08/2019
24/05/2019
ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበት ጊዜ ተራዘመ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበት ጊዜ መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የ2011 ትምህርት ዘመን የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ማስፈፀሚያ የንቅናቄ ዕቅድ ረቂቅ ሠነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የመፈተኛ ጊዜውን የወሰነ መሆኑ ሚኒስቴሩ አስታውሷል።
ሆኖም በዛሬው ዕለት የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኮማንድ ፖስት ባደረገው ስብሰባ ከኢድ በዓል ጋር በተያያዘ በጥልቀት ተወያይቶ፦
1ኛ .የ10ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ሰኔ 3፣ 4 እና 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ፤
2ኛ.የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሰኔ 6፣ 7፣ 10 እና 11 ቀን 2011ዓ.ም ሲሆን፥
3ኛ. የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 12፣ 13 እና 14 ቀን 2011ዓ.ም. ለአስተዳደራዊ አመቺነት ሲባል የተቀየረ መሆኑን አስታውቋል።
ኮማንድ ፖስቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከህብረተሰቡ ጥያቄ በተጨማሪም ፈተና ተፈታኞችና ፈታኞች ከበዓሉ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ከቦታ ቦታ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠርና የፈተናውን ሂደት የተሳካ ለማድረግ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ያስታውቋል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa