Beta ICT

Beta ICT

Share

14/10/2025

Are you a graphics designer ?

You should know these terms !

Photos from Beta ICT's post 06/03/2025

የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች አቅራቢ የሆነው ቴክኖ በባርሴሎና በየዓመቱ በሚካሄደው MWC 2025 የቴክኖሎጂ አውደርእይ ላይ በመሳተፍ አዲሱን የAI ሲስተም የሚጠቀሙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋውቋል።

በዚህ አመታዊ የቴክኖሎጂ ሁነት አዲሱን የTECNO AIን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ከዘመናዊነት ጋር ያጣመሩ ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች ያቀረበ ሲሆን ከነዚህም መካከል የMEGABOOK S14 የተሰኘው ላፕቶፕ አንዱ ሲሆን በዓለም እጅግ ቀላሉ እና የ14 ኢንች OLED ስክሪን ቴክኖሎጂ ያለው ነው።

የኩዋልኮም Snapdragon® X Elite ፕላትፎርም እና የTecno AI ሲስተምን በማካተት እጅግ የላቀ ፕሮሰሲንግ አቅም ያለው እንደሆነም ተገልጾዋል።

በተጨማሪም TECNO AI Glasses Pro ሌላኛው በዚህ መድረክ የተዋወቀ አዲስ ምርት ሲሆን የ50MP ካሜራ ፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን በቀጥታ ለመተርጎም የሚያስችል አቅም፣ የMicroLED AR ዲስፕሌይ እና በAI ቴክኖሎጂ በመታገዝ ጥራት ያላቸው ምስሎችን ማንሳት የሚያስችል ዲጂታል መነፅር ነው።

ከዚህም ባለፈ የMEGABOOK T14 Air እና K15S ተከታታይ የላፕቶፖ ሞዴሎችን ያስተዋወቀ ሲሆን በAI ሲስተም በመታገዝ ለተጠቃሚዎች የዕለት ተዕለት ተግባራት ለማቅለል የሚያስችል እጅግ ቀልጣፋ ቴክኖሎጂን ይዟል። ቴክኖ ከ MediaTek ፣ Qualcomm እና Google Cloud የተሰኙ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር የ AI ቴክኖሎጂን ለአፍሪካ ገበያ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም በቴክኖሎጂ ሁነቱ ይፋ ተደርጓል።

"Stop at Nothing" በሚለው መርሁ የሚታወቀው ግዙፉ ቴክኖ የተለያዩ አዳዲስ እና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለአለም ገበያ በማቅረብ ይታወቃል።

11/08/2022

ስማርትፎን በምንገዛበት ጊዜ ሊታሰብባቸው የሚገቡ 9 ነገሮች❗️🤔
***
በዚህ ዘመን ስማርት ስልኮች የሕይወታችን ዋና አካል ሆነዋል፡፡ ከወዳጆቻችን ጋር ተደዋውለን ለመገናኘት፣ ፎቶ ለማንሳት፣ ቪዲዮ ለመቅረጽ፣ መረጃዎችን ክላውድ ላይ ለማስቀመጥ፣ ሌሎችን ስልኮች ቻርጅ ለማድረግ፣ ኢንተርኔትን ለመጎብኘት… ምን አለፋችሁ የስማርት ስልኮች አገልግሎት እጅግ በጣም ብዙ ነው፡፡



ነገር ግን በገበያ ላይ ካሉት የተለያዩ ስማርትፎኖች መካከል የትኛውን እንደሚመርጡም መወሰን ቀላል አይደለም፡፡ ስለዚህ ስማርትፎን ለመግዛት ከመወሰናችሁ በፊት የሚከተሉትን ጉዳዮች ልብ በሉ፣

1. የተሰራበት ቁስ ጥራት

ጠቅለል ተብሎ ሲታይ አንድ ስልክ በፕላስቲክ አልያም በብረት የተለበጠ ሊሆን ይችላል፡፡ በርግጥ አንዳንዶች ከመስታወትም እንደሚሰሩ ልብ ይሏል፡፡ ነገር ግን ለምሳሌ እርስዎ ስልክዎትን በተደጋጋሚ የሚጥሉ ከሆነ ረዥም እድሜ የሚኖረው ስልክ ያስፈልግዎታል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከፕላስቲኩም ከመስታወቱም ይልቅ በብረት የተለበጡት ስማርትፎኖች ምርጫዎት ሊያደርጉ ይገባል፡፡

2. ስክሪን(ማሳያ)

የስልኩ ስክሪን መጠንና ሪዞሊዮሽን ስልኩን ልንጠቀምበት እንደአሰብነው ጉዳይ ይለያያል፡፡ ብዙ ጊዜ በስማርት ስልክዎ ቪዲዮዎችን የሚያሰራጩ ከሆነ፣ ፎቶዎችን ወይም ቪዲዮዎችን ኤዲት የሚያደርጉ ከሆነ ወይም ፊልሞችን የሚመለከቱ ከሆነ ከ5.5 ኢንች እስከ 6 ኢንች full-HD ወይም QHD ጥራት ማሳያ ያለው የስማርትፎን ለእርስዎ ምርጡ አማራጭ ነው፡፡

3. ፕሮሰሰር

ፕሮሰሰር የስማርት ስልኮች ልብ ማለት ነው፡፡ ስልኩ ሁሉንም የሚያቀናብረው እዚህ ነው፡፡ ታዲያ በኦፕሬቲንግ ሶፍትዌር፣ በUI፣ በbloatware እና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች የተነሳ ፕሮሰሰር ከስልክ ስልክ ይለያያል፡፡

ቪዲዮ ጌም የምትጫወቱ ከሆነ፣ ቪዲዮና ፎቶዎችን እንዲሁም ዶክመንቶችን የምታቀናብሩ ከሆነ፣ አልያም ቪዲዮዎችን ከስልካችሁ ላይ የምታሰራጩ ከሆነ እና ሌሎች ከበድ ያሉ ስራዎችን የምትሰሩ ከሆነ Qualcomm Snapdragon 652 ወይም Snapdragon 820/821 ፕሮሰሰር ያሏቸው ስልኮች ያስፈልጉዎታል፡፡

4. ካሜራ

ከፍ ያለ የሜጋፒክስሎች ብዛት ብቻ የስማርትፎን ካሜራ የተሻለ አያደርገውም፡፡ እንደ የካሜራ ቀዳዳ፣ የISO ደረጃዎች፣ የፒክሰል መጠን፣ አውቶፎከስ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች አስፈላጊ ናቸው...

19/06/2022

Microsoft Collaborates with the Ethiopian Ministry of Education to Help Digitize the Education Sector

Microsoft has collaborated with the Ethiopian Ministry of Education to implement a Higher Educational Management Information System supporting the successful digital transformation of the education sector.

06/06/2022

ይሄ ወቅት ከማንም በላይ አስቸጋሪ የሆነው ለወጣት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ምክንያቱም የወጣት ዋነኛ ቀለቡ ተስፋ ነው፡፡አሁን ላይ ደግሞ በቀላሉ አልገኝ ያለው ተስፋ ይመስለኛል፡፡ስራ የማግኘት ፥ ገንዘብ የመቆጠብ ፥ ተምሮ ለውጥ የመፍጠር ፥ የራስን ቤት የማግኘት ፥ ተፍ ተፍ ብሎ ራስን የመቀየር ወዘተ ተስፋዎች ከምንጊዜውም በላይ አሁን ሩቅ ሆነዋል፡፡በዚህም የተነሳ ብዙ ወጣቶች እንዲሁ በቋፍ ላይ እንዳሉ እየታየ ነው፡፡ጥናትም ባላረግበት ከማየው እንደምረዳው ራስን ማጥፋት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡
ወጣቱ ሁሉ እንዲህ በራሱ ጉዳይ አንጎል በሆነበት እና መስመር ላለመሳት በቋፍ ባለበት በዚህ ወቅት ለሰዎች የእርጋታ እና የሳቅ ምንጭ ለመሆን መሞከር እና ተስፋ ጨርሶ እንዳይጠፋ መሞከር ያስፈልጋል፡፡
#ነገየተሻለቀንይሆናል

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Piassa
Addis Ababa