Gojo Media
27/05/2016
I can NOT stop watching Rihanna 's performance. AMAZING. Watch here!
https://m.youtube.com/watch?feature=youtu.be&v=SuFKZ6P4paE
Rihanna - Love On The Brain (Live From the 2016 Billboard Music Awards) Rihanna - Love On The Brain (Live From the 2016 Billboard Music Awards) http://vevo.ly/YvKK5d
23/09/2015
አንድ በጣም ስሜትን የሚነካ ታሪክ ላስታውስህ።
በእስራኤልና በፍልስጥኤም መካከል ለዘመናት ያላበራው ግጭት፣ ጥፋት እና ሃዘን አሁንም ከየእለቱ ዜና
ጠፍቶ አያውቅም፡፡ ነገሩ፤ የሙስሊሞች በዓል የሚከበርበት ቀን ላይ ያጋጠመ ነው፡፡ የታሪካቸው ቅርበት
ያህል የብዙዎቹ ኑሮም ቅርብ ለቅርብ ነው፡፡ ከመንገዱ ወዲህ ፍልስጤኤማውያን፣ ከመንገዱ ወዲያ
ደግሞ እስራኤላዊያን ይኖራሉ፡፡ ጥዋትም ከሰዓትም በኋላም ማዶ ለማዶ ይተያያሉ። ፋታ የሌለው ጥርጣሬ
ግን በሰላም እንዲተያዩ አላደረጋቸውም፡፡
እና በዚያ የበዓል ቀን፤ አባት ለልጁ አዲስ ልብስ ገዝቶለታል፤ አዲስ መጫወቻም አምጥቶለታል፡ በተገዛለት
መጫወቻ የተደሰተው ህፃን፣ አዲስ ልብሱን እንዳደረገ ከቤት ውጭ ይጫወታል፡፡ ቦታው ትንሽ ከፍ የለ
ነው፡፡ ወደ ታች ብዙም ሳይርቅ የእስራኤላዊያን መንደር አለ፡፡ከመሃል ባለው መንገድ ላይ ለጥበቃ
የተመደቡ የእስራኤል ወታደሮች አካባቢውን ይቃኛሉ። እና ከወታደሮቹ አንዱ፣ ከጉብታው አካባቢ የሰው
እንቅስቃሴ ሲመለከት፤ አደጋ ተሰማው፡፡ የተነጣጠረ መሳሪያ ታየው፡፡ ሳይቀድመኝ ልቅደም ብሎ
ይተኩሳል፡፡
አባቱ የገዙለትን ውሃ የሚረጭ ሽጉጥ ይዞ ሲጫወት የነበረው ህፃን በጥይት ተመታ፡፡ አባት የተኩስ ድምጽ
ሰምቶ በድንጋጤ ከቤት ወጥቶ ይመጣል፡፡ ልጁ ወድቋል፡፡የእስራኤል ወታደሮችም ተጠግተው አይተዋል፡፡
የተነጣጠረ መሣሪያ የመሰላቸው ነገር ውሃ የሚረጭ ሽጉጥ መሆኑን ሲያዩ ደነገጡ፡፡ ህፃን መጉዳታቸውን
ሲያዩ አዘኑ፡፡ በአስቸኳይ ሄሊኮፕተር ተጠርቶ ልጁ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ አደረጉ፡፡ ነገር ግን ወደ
ሆስፒታል የተወሰደውን ህፃን ለማዳን ሃኪሞች ቢጣጣሩም አልተሳካላቸውም፤ ህይወቱ አለፈ፡፡ ይሄ አባት፣
ከዚያች ቅጽበት በኋላ ምን አይነት ሰው እንደሚሆን አስበው፡፡ በሀዘን የተመታው አባት፤ ሃኪሞቹን
ጠየቃቸው። “የልጄ ልብ ንፁህ ነው ወይ” አላቸው፡፡ ያልጠበቁት ጥያቄ ነው፡፡ “አዎ ጤናማ ነው” አሉት፡፡
እንግዲያውስ፣ በልብ ህመም ለሚሰቃዩ እስራኤላዊ ሕፃን አስተላልፉለት” አላቸው፡፡ ያልተለመደ በጣም
አስገራሚ ታሪክ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ውስጥ ይበዛም ይነስ በጐ ነገር አለ፡፡ አደገኛነት ብቻ ሳይሆን
ታላቅነትም የሚወለደው እንዲህ ካለ ጥልቅ ጉዳት ውስጥ ነው፤ ምክንያቱም ፍቅር ሳይሰቃይ አያሸንፍምና፡፡
(ቴዲ አፍሮ®)
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa