Eyob1X tube
With ቴዶ ዘቅዱስ ሩፋኤል – I just got recognized as one of their rising fans! 🎉
20/09/2025
20/09/2025
20/09/2025
20/09/2025
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢትዮጵያ በእግር ኳስ ከአለም 147ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ ፊፋ ገለፀ፡፡ የአለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሆነው ፊፋ አዲስ ባወጣው(የሴፕቴምበር ወር) የአለም አገራት የእግር ኳስ ደረጃ በቁጥር 1 ላይ ያስቀመጣት ስፔንን ነው፡፡ ስፔን ባለፈው ወር 2ተኛ ደረጃ ላይ የነበረች ሲሆን ባለፈው ወር 1ኛ የነበረችው አርጀንቲና አሁን 3ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ባለፈው ወር 3ተኛ የነበረችው ፈረንሳይ ደግሞ አሁን 2ተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ እንግሊዝ ባለችበት 4ተኛ ደረጃ ላይ ፀንታለች፡፡ ፖርቹጋልና ብራዚል ደግሞ ቦታ ተቀያይረው በ5ተኛና 6ተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ችለዋል፡፡ በፊፋ የዚህ ወር ደረጃ አሰጣጥ ከአፍሪካ በቀዳሚ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ሞሮኮ ናት፡፡ የሞሮኮ ቡድን ባለፈው ወር ከአለም 12ተኛ ደረጃ ላይ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በ11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ የምትገኝበትን የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ(ሴካፋ) ቀጠናን ስንመለከት ደግሞ ከአለም በ82ተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኡጋንዳ ከቀጠናው ቀዳሚ ደረጃን አግኝታለች፡፡
በመቀጠል ከአለም 107ተኛ የሆነችው ታንዛኒያ ስትቀመጥ፣ ከአለም 111ኛ የሆነችው ኬንያ በቀጠናው 3ተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህ ቀጠና ቀጣዩን ደረጃ የያዙት ደግሞ ሱዳን፣ ሩዋንዳና ብሩንዲ ሲሆኑ ከእነሱ በመከተል ኢትዮጵያ ቦታውን ይዛለች፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ወር በፊፋ ያገኘችው ደረጃ 147ኛ ነው፡፡
በሴካፋ ቀጠና ከኢትዮጵያ በመቀጠል የተቀመጡት ከአለም 160ነኛ የሆነችው ደቡብ ሱዳን፣ እንዲሁም ከአለም 193ተኛ የሆነችው ጅቡቲና ከአለም 201ኛ የሆነችው ሱማሊያ ናቸው፡፡ በዚህ ቀጠና የምትገኘዋ ሌላኛዋ አገር ኤርትራ ግን በዚህ የፊፋ ደረጃ ውስጥ አልተካተተችም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ብሄራዊ ቡድኗ ከአለም አቀፍ ውድድሮች ውጭ በመሆኑ ነው፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Abeba
Addis Ababa