Gize Media

Gize Media

Share

14/01/2026

በአይሾው ስፒድ (IShowSpeed) የአዲስ አበባ ጉብኝት ወቅት ብዙዎች ወደ እሱ ለመጠጋትና ባህላችንን ለማስተዋወቅ ሲቸገሩ እንዲሁም ሲጋፉ ተመልክተን ነበር።

ቋንቋውም ሆነ ግርግሩ ተደማምሮ መልእክት ለማስተላለፍ ሲከብድ፣ ምራፌ ገብረማርቆስ የተባለ ይህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ግን በፍጥነት ነገሮችን በሙሉ በእርጋታ ተቆጣጠራቸው።

በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት፣ ምራፌ በብቃት ከመተርጎም አልፎ፣ ስፒድ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ባህል ትክክለኛውን መረጃ እንዲያገኝና እንዲረዳ ትልቅ ስራ ሰርቷል።

​በተለይም በአድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ ሲደርሱ፣ ምራፌ ለቦታውና ለሰማዕታት ጀግኖች ያለውን ክብር ለማሳየት ስፒድን ጫማውን እንዲያወልቅና በባዶ እግሩ እንዲራመድ ጠይቆታል።

የሚገርመው ነገር፣ ስፒድም ይህንን ጥያቄ ያለ ምንም ማመንታት ተቀብሎ በባዶ እግሩ በመሄድ ለጀግኖቻችን ክብር እንዲሰጥ አድርጓል። ብዙዎች በግርግር መሃል ሲጠፉ፣ ምራፌ ግን በተረጋጋ መንፈስ ስፒድን እየመራ የኢትዮጵያን ታላቅነት በደንብ አስረድቷል።

​አሁን ላይ የኢትዮጵያ ኢንተርኔት ማህበረሰብ የዚህን ሰው ብቃትና በራስ መተማመን እያደነቀው ይገኛል። እንግዳን በአግባቡ ማስተናገድና ታሪክን ማስከበር ማለት ይህ ነው! ምራፌ፣ በሰዎች መሃል ጎልተህ በመውጣትህና ሀገርህን በዚህ መልኩ በማስጠራትህ ክብር ይገባሃል!

:- Ethio Lead



አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

15/11/2025

! 😮 8 ሚሊዮን ብር ገቢ እንዲገባ ያደረገው ቲክቶክን ወደ ታላቅ በጎ ተግባር የለወጠው ወጣቱ ጀግና!

ዛሬ እጅግ አስደናቂ እና ልብ የሚነካ ታሪክ በቲክቶክ ዓለም ተመዝግቧል! ወጣቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ አዶናይ የረምዚን ሪል እስቴት Challenge ቃሉን ጠብቆ ታላቅ ስኬት አስመዝግቧል!

ረምዚን ሪል እስቴት በቲክቶክ 1 ሚሊዮን ተከታዮችን (Followers) ካስገባችሁኝ፣ 8 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ለባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት አስገባለሁ ባለው መሰረት ቲክቶከሩ አዶናይ ባለው ትልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪነት እና ህዝባዊ ድጋፍ ጥሪ በማቅረቡ ምክንያት በዛሬው ዕለት በአንድ ቀን ውስጥ 1 ሚሊዮን እንዲገባ አድርጓል!

በዚህም ምክንያት 8 ሚሊዮን ብር ለበጎ አድራጎት እንዲገባ አስችሏል!

አንድ ግለሰብ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል በተግባር አሳይቷል!

ይህ ስኬት ከቲክቶክ ባለፈ ትብብርና በጎነትን
የሚያሳይ ብሩህ ምሳሌ ነው! በዚህም ይህ ወጣት አምባሳደር ሆኖ ሊሾም ይገባዋል!

:- Gursha



አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

Photos from Gize Media's post 24/10/2025

S25 ስልክ ቀምቶ ቱቦ የገባው ሌባ

ከአንድ ግለሰብ ስልክ ቀምቶ የቆሻሻ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ በመግባት ሊያመልጥ የነበረ ተጠርጣሪ ከ5 ሰዓታት ቆይታ በኋላ ከነ ኤግዚቢቱ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ።

ተጠርጣሪው የቅሚያ ወንጀሉን ፈጽሞ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ በመግባት ሊያመልጥ ሲል በቁጥጥር ስር የዋለው ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ/ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አቤቤ ሱቅ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪው የግል ተበዳይ ከባንክ ብር አውጥተው ሲወጡ ጠብቆ የዋጋ ግምቱ 120 ሺ ብር የሚያወጣ Sumsung Ultra S25 ስማርት ስልክ በመንጠቅ በአካባቢው ወደሚገኝ የቆሻሻ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ ገብቷል።

የወንጀል ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የግል ተበዳይ የይድረሱልኝ ጥሪ በማሠማታቸው የአካባቢው ህብረተሰብ እና ፖሊስ ወዲያው ቦታው ላይ በመድረስ ተጠርጣሪው በገባበት የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ ተከታትሎ በመግባት ሊያወጡት መቻላቸውን የየካ ክፍለ ከተ ማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ተጠርጣሪው ከቱቦው ውስጥ ሲወጣ ስልኩን ትቶ የወጣ ቢሆንም ፖሊስ ተጠርጣሪውን በድጋሚ ወደ ቱቦው ውስጥ ይዞ በመግባት ስልኩን ከጣለበት ውሃ ውስጥ እንዲያወጣው ማደረጉን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።

በእንደዚህ ዓይነት የወንጀል ተግባር ላይ የሚሰማሩ ወንጀል ፈጻሚዎች ከህግ እንደማያመልጡ አውቀው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።



አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

25/09/2025

"ያስፈራሩኝ የነበሩት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል!"

👉 ድምፃዊት ዳግማዊት ፀሐዬ✍️

ድምጻዊት ዳግማዊት ፀሐዬ፣ በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ለረጅም ጊዜ ሲያስፈራራትና ሲያንገላታት የነበረው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀች።

የግለሰቡ መያዝ በበርካቶች ዘንድ እፎይታን ሲፈጥር፣ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰፊ መነጋገሪያን በመፍጠር ሴቶች በኦንላይን ለሚደርስባቸው ጥቃት የሚሰጠውን ማህበራዊ ምላሽ በድጋሚ እንዲፈተሽ አድርጓል።

ዳግማዊት በማህበራዊ ገጿ ላይ "ትዝ አላችሁ እሱ ካልተያዘ ኢትዮጵያዊነቴን እሰርዛለሁ ብዬ ነበር! ተመስገን ለሁሉም ጊዜ አለው... ወንጀለኛው ተይዟል!" ስትል የደረሰችበትን የስነ-ልቦና ጫናና የግለሰቡን መያዝ ተከትሎ የተሰማትን እፎይታ ገልጻለች።

ግለሰቡ በሌሎች ሰዎች ላይም የገንዘብ ማጭበርበር እንደፈጸመ ፍንጭ የሰጠ ሲሆን፣ ተከሳሹ ነገ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብም አስታውቃለች።

ድምጻዊቷ ላደረጉላት ፈጣን ምላሽ የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊስን አመስግናለች።



አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ👇
https://t.me/gize_media

ፔጃችንን LIKE በማድረግ ቤተሰብ አድርጉን 👇
https://www.facebook.com/GizeMereja?mibextid=ZbWKwL

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa
1000