Reader is Leadar

Reader is Leadar

Share

06/12/2025

ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም/ደብረ ድማህ\

ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነማይ ወረዳ ከብቸና ከተማ 28 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የገዳሙ መጠሪያ ስም ደብረ ዲማህ ሲሆን ትርጓሜውም ራስ ወይም ጭንቅላት ማለት ነው ፡፡

የዲማ ቅድስ ጊዮርጊስ ገዳም የተመሠረተው በአጼ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት በ1297 ዓ.ም ነው። በአፄ ይሥሃቅ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ደግሞ ገዳም ሆኖ ስፍትና ክብር ተጨምሮለት መኖር እንደጀመረ የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ ፡፡

ዲማን የመሰረቱት አባት አባ በኪሞስ ሲሆኑ ተከስተ ብርሃን የተባለው ስም የተሰጣቸውም በጎጃም እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክ እየጠመቁ ሳለ አንድ ቀን ከአማንያን ብዛት የተነሳ የማጥመቅን ስራ ሳይጨርሱ ጀንበር ስትጠልቅባቸው አምላክን በመለመን ብርሃን ወርዶላቸው ስራአተ ጥምቀቱን ፈጽመው እንደሄዱ ታሪክ ይነገራል ፡፡

ይህ ገዳም በውስጡ በረካታ ጥንታዊ ቅርሶችን የያዘ ሳሆን ከእነዚህም የንጉሥ ተክለሃይማኖት ጦር፤ እና የራስ መኰንን ካባ ከብዙ በጥቂቶቹ የሚጠቀሱ ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ በመጻሕፍት ትርጓሜ ቤት የሚታወቅ ሲሆን በረካታ የትርጓሜ መምህራን የፈለቁበት ታላቅ ገዳም ነው።

@ሀብታሙ ሲሳይ

Want your university to be the top-listed University in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Abeba
Addis Ababa