Divers Media Network - DMN
01/06/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ
*******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።
31/05/2026
በ1950ቹ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጥ የነበረው የቴፒ መለስተኛ የአየር ማረፊያ ለብዙ አመታት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ከአቬሽን ባለስልጣንና ለሎች አካላት ጋር በመሆን የሸካ ዞን ዳግም ወደ ስራ ማስገባት ችሏል ።
በዚህም የመጀመሪያ በረራ ተጠቃሚዎች እንደገለፁት
በትራንስፖርት ዘርፍ በሸካ ዞን ከዚህ በፊት ከፍተኛ ችግር መኖሩን ገልፀው አሁን የተጀመረው በረራ ያለውን እንግልት የቀነሰና ለተገልጋዩ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጠ ነው ብለዋል።
በተመጣጣኝ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን የተናገሩት መንገደኞች የመጀመሪያ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በመሆናቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቁመዋል ።
የሸካ ዞን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ያለበት በመሆኑ ይህን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግና አካባቢ ላይ ያለውን ምርት ለማስተዋወቅ በረራ አገልግሎት መጀመሩ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ካፕቴን አብረሃም ጆሴፍ ተናግረዋል።
የበረራ አገልግሎት መጀመሩ ለሸካ ዞን ብቻ ሳይሆን በአካባቢ ላይ ትልቅ እድል የፈጠረና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር ያስቻለ መሆኑን የገለፁት ካፒተን አብረሃም ይህም በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ በመሆኑ መጠቀም አለባችሁ ብለዋል።
የፍላይት ቡክንግ አስተባባሪ አቶ ብሩክ በለጠ በበኩላቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት booking app የተሰኘውን መተግበሪያ ከአፕስቶር በማውረድ ባሉበት ሆነው ቲኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል ።
በዚህም ተገልጋዮች ያለምንም እንግልት መጠቀም መጀመራቸውን የገለፁት አቶ ብሩክ የአካባቢው ማህበረሰብ ይህን አገልግሎት መጠቀም እንዳለበት አሳውቀዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ ቴፒ ግሪን ኮፊ የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገፆች ላይ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚቻል ገልፀው ተጠቃሚዎች የሚኖራቸውን አስተያየት በዚህ ላይ ማስቀመጥ እንደሚችሉም ተናግረዋል ።
በረራው ሰኞ እና አርብ ከሳምንት ሁለት ጊዜ
ዘወትር እንደሚኖር ገልፀው ይህም አካባቢውን ለማስተዋወቅና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ትልቅ አቅም አለው ብለዋል።
Masha FM
30/05/2026
#ፒኤስጂ አሸናፊ ሆኗል
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa