Brightmind

Brightmind

Share

Photos from Brightmind's post 07/10/2024

✍️✍️✍️✍️✍️✍️ፍቅርና ህይዎት

ዛሬን ኖረናል ነገን እንደምንኖር ወይንም እንደማንኖር እርግጠኛ ሆነን መናገር አንችልም። ምክንያቱ ደሞ ህይወት በተስፋ ስለት የተሳለች እና በአጋጣሚዎች ስብስብ የቆመች የእስትንፋስ ጓዳ ናት። ስለ ህይወት ሳወራ ቀድመዉ የሚመጡብኝ ለወደፊት ይሆኑልኛል ያልኳቸዉን ነዉ። ሞትን የምፈራዉም እንድሆኑልኝ የተመኘኋቸዉን እንዳያቸዉ ስለምጓጓ እንጅ የማየዉ እና እንድሆንልኝ የምመኘዉ ባይኖረኝ ኖሮ ህይወት ለራሷ ምን ትርጉም ይኖራት ነበር። ፍቅር የህይወትን ጣዕም የሚያጣፍጥ የመኖርንን ጉጉት የሚያሰፋ የደስታ ንጉስ የሆነ የተፈጥሮ ግሩም ስጦታ ነዉ። ለኔ መኖሬም መመኘቴም ለፍቅሬ ስል ብቻ ነዉ። ፍቅርን ተርጉሜ አስሸ እና መርምሬ ያልጠገብኩ ነኝ። ፍቅሬን ሳስብ ነገን እናፍቃለሁ ሞትን እፈራለሁ ፍቅሬን ስመኝ ትናንትን ነገ እንድሆን ዛሬን ሌቱ እንድጎድል የማልመኘዉ ነገር የለም። ግን ስለሁሉም ነገር ስለፍቅር አሳብቤ ልንገራችሁ እንጅ ፍቅር እኮ ከኔጋ የለም። ዛሬማ ተለይቶኛል ዉደታ የሚባል የለም ናፍቆት በራሱ ሳይረሳኝ አልቀረም። ለመወደድ ምኑ ነበር የቀረኝ ህይወት ትኑር ከምንየዉም በላይ ታስደስተኛለች ለኔ ፍቅሬ ህይወቴ ናት፤ እወዳታለሁ አፈቅራታለሁ እሳሳላታለሁ ሁሌም ፍቅሬ ናት ከህይወት በላይ ምን ፍቅር አለ። ፍቅር በብዙ ቦታ ሊኖር ይችላል የገንዘብ ፍቅር የሰዉ ፍቅር የስራ ፍቅር የእናት ፍቅር ብሎ ቢዘረዘር ወደር የሌለዉ ነዉ....... ፍቅር የሌለበት የለም። ፍቅር የሌለበት አለ ካላችሁ እራሱ እንደለለ እኔ እመሰክራለሁ።
ከምነየዉም በላይ ግን ለኔ ትዝታየም ፍቅሬም ናፍቆቴም ሀሳቤም ህይወቴ ብቻ ናት። ሁሉን ነገር ልታሳየኝ የምትበቃዉ ህይወቴ ስትኖር እና በፍቅሯ ጣዕም ስጎነጭ ብቻ ነዉ።

ቀጣይ የምትሉ ....በኮሜንት ግለፁልኝ

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa