Ethio Legal Hub

Ethio Legal Hub

Share

25/05/2024

የኮንዶሚንየም ቤት ሽያጭ

==============
የኮንዶሚንየም ቤት የደረሰው ሰው ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ሊያስተላልፍ የሚችለው ቤቱን ከገዛ 5 አመት ሲሞላው ብቻ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 19/97 ተደንግጓል። ይሁንና ይህ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው እጣው ከወጣ በኃላ ነው ወይስ እጣውን ተከትሎ ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ጋር ውል ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ነው የሚለው ሲያከራክር የነበረ ሲሆን በአዋጁ ላይ በግልፅ ባይቀመጥም ከጠቅላላ ድንጋጌዎቹ ይዘት የምንረዳው የኮንዶሚንየም ቤት እጣ ከከተማው አስተዳደር ጋር የቤት ግዢ ውል ለማድረግ መብት የሚሰጥ እንጂ እራሱ የቤት ግዢ ውል አይደለም፡፡ ስለዚህም የኮንዲሚንየሙ ባለቤት ለ3ኛ ወገን በሽያጭ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ የሚችለው ቤቱን በገዛ 5 አመት ሲሞላው ነው የሚለው ጊዜ የሚቆጠረው እጣ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሳይሆን የሚቆጠረው የቤት ሽያጭ ውል ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡

/የሰበር መ/ቁ 158899/
=======
Join us on Telegram👇👇

https://t.me/ET_Legalhub

👉 Tiktok 👇

https://vm.tiktok.com/ZMMEL5E2W/

04/05/2024

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ።🙏

Ethio Legal Hub መልካም የትንሳኤ በአል እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

04/05/2024

ወራሽነት መብት ቢሆንም ሟች ወይም የኑዛዜ አድራጊው በህጉ በተሰጠው መብት መሰረት በሚያደርገው ኑዛዜ ህጋዊ ወራሾቹን የውርስ ሀብት ተካፋይ እንዳይሆኑ ከውርስ ሊነቅላቸው ይችላል።

ከውርስ መንቀል ጋር በተገናኘ ከብዙ በጥቂቱ በአጭሩ እንዲህ አዘጋጅተንላችኋል።

በዚህ ርዕስ ላይ ያዘጋጀነውን ዝርዝር ፅሁፍ ለማንበብ የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ👇

https://t.me/ET_Legalhub

Ethio Legal Hub

10/04/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ።

🌙

Want your practice to be the top-listed Law Practice in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa