ETHIO SAT DISH TEC

ETHIO SAT DISH TEC

Share

Photos from ETHIO SAT DISH TEC's post 04/03/2026

አስቸኳይ የፍለጋ ጥሪ ሙባረክ ሰይድ እንድሪስ ⭐️⭐️⭐️ ሼር ሼር ሼር
***
ለሰው ልጅ በሙሉ ይድረስ! አንድን እናት ከጭንቅ፣ አንድን ህፃን ከጥፋት ለመታደግ ሰከንዶችን እንጠቀም።

ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው መብራት ሀይል አካባቢ የጠፋው ህፃን ሙባረክ ሰይድ እንድሪስ ይባላል በቀን 23/06/2018ዓ/ም ከቀኑ 11:0 ሰዓት አካባቢ ከመኖሪያ አካባቢው የጠፋው እድሜው 6 ዓመት ቀይ በእለቱ ጥቁር ትሸርት እና ነጭ ሱሪ ለብሷል

* ስም ሙባረክ ሰይድ እንድሪስ
* እድሜ 6 ዓመት

* ይህ መረጃ ለብዙ ሰው እንዲደርስ በማድረግ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። የእርስዎ አንድ ሼር የህፃኑን ህይወት ሊታደግ ይችላል።

* ይህን ህፃን ያያችሁ ወይም ያለበትን የምታውቁ በነዚህ ስልኮች በአስቸኳይ ደውሉልን፦

* 0921635499
* 0912714945
* 0912268653

03/03/2026

የእስራኤል ጦር የሄዝቦላህ የስለላ አዛዥን መግደሉን አስታወቀ
***
የእስራኤል ጦር የሄዝቦላህ የስለላ ዋና መሥሪያ ቤት ኃላፊ ሆኖ ያገለገለውን ሁሴን ማክሌድን በአንድ ሌሊት መግደሉን አስታውቋል።

በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት መገደሉን ወታደሮቹ አስታውቀዋል።

የሄዝቦላህ ታጣቂ ቡድን የኢራኑን ሉዓላዊ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒን ግድያ "ለመበቀል" በሚል በእስራኤል የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ይታወቃል።

​የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ በኢራን ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ለመመከት ወደ ጦርነቱ መግባቱንና የመጀመሪያዎቹን ሮኬቶች ወደ ሰሜን እስራኤል መተኮሱን አረጋግጧል።

የቡድኑ መሪ ናይም ቃሲም "ወረራውን የመመከት ግዴታችንን እንወጣለን፤ የክብርና የጥንካሬ ሜዳውንም አንለቅም" ሲሉ ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።

ሄዝቦላህ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን ተከትሎ፥ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ከ50 በላይ ከሚሆኑ የሊባኖስ መንደሮች ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ አዟል።

እስካሁን በስለላ አዛዡ ግድያ ዙሪያ ከቡድኑ የተሰጠ ምንም አይነት አስተያየት የለም።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Asco
Addis Ababa