Armauer Hansen Research Institute
23/06/2026
“ጠንካራ ተቋም ለጠንካራ አገረ መንግሥት!”
-----------------------------------
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) መላው አመራሮችና ሠራተኞች “በምርጫ ማግስት፤ ጠንካራ መንግሥት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ የውይይት አካሂደዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታመነ አጫሞ የ7ኛውን አገራዊ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት ቅድመ ምርጫ፣ የምርጫ ወቅት እና ድኅረ ምርጫን የሚዳስስ እንዲሁም ጠንካራ አገረ መንግሥትን ለመገንባት የተቀመጡ ዓላማዎችን የሚያብራራ ዝርዝር የመነሻ ሰነድ አቅርበዋል።
የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ዘላቂና ጠንካራ መንግሥት ለመገንባት ጠንካራ ተቋማት መሠረታዊ ሚና እንደሚጫወቱ አስገንዝበዋል።
አህሪ በጤናው ዘርፍ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወትና ለሀገር እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው ተቋም መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የተቋሙን ተፅዕኖና አበርክቶ ይበልጥ ለማጠናከር እያንዳንዱ ሠራተኛ የበኩሉን ኃላፊነት በብቃትና በቁርጠኝነት መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር አፈወርቅ አክለውም፣ ኢንስቲትዩቱ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማሳደግ እና በሕክምናና በመድኃኒት ዘርፍ ራስን በመቻል አገራዊ ሉዓላዊነትን ለማጠናከር፣ የምርምር ውጤቶችን ወደ ተግባራዊ ምርትና ፈጠራ ለመቀየር በትጋት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በቀረበው የመነሻ ሰነድ ላይ በተካሄደው ሰፊ ውይይት፣ 7ኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና የሀገርን ዘላቂ ጥቅም ያስቀደመ ሂደት በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ስኬት ያስመዘገበ ምዕራፍ መሆኑ ተጠቅሷል።
በመጨረሻም፣ የተጀመረውን የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና የዜጎችን ፍላጎትና ተሳትፎ መሠረት ያደረገ ጠንካራ መንግሥት ለመገንባት፣ እያንዳንዱ የተቋም ሠራተኛ የዕለት ተዕለት ሥራውን በታማኝነት፣ በብቃት እና በኃላፊነት መፈጸም ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጿል። ውይይቱም በአንድነት በግል ጠንካራ የስራ ባህል÷ ጠንካራ ተቋም እና ጣንካራ መንግስት ለበለጸገች ሀገር ወሳኝ መሆኑ ላይ ግንዛቤ በመያዝ በቁርጠኝነት በስኬት ተጠናቋል።
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopia
21/06/2026
19/06/2026
ምርምርና ሚዲያ ለላቀ ጤና
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) "ምርምርና ሚዲያ ለላቀ ጤና" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀውን 4ኛውን ዓመታዊ የሚዲያ ፎረምና የምርምር ማዕከላትን ጉብኝት በስኬት አካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ ጋዜጠኞች፣ የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የኮሙኒዩኬሽን ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሁሉም ወረዳዎች የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊዎች፣ የተሳተፉ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የሚገኙ ዘመናዊ የምርምር ላቦራቶሪዎች እና በውስጡ የሚገኙ የተለያዩ ቤተ ሙከራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ባደረጉት ንግግር "የጤና ምርምር ጉዳይ ከማኅበራዊና ከኢኮኖሚያዊ አልፎ ከሀገር ሉዓላዊነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ያሉ ሲሆን፣ የሚዲያ ተቋማት የምርምር ውጤቶችን ተፅዕኖ ለማስፋት ከተቋሙ ጋር አብረው እንዲሠሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዓለምሰገድ አብዲሳ፣ በኢንስቲትዩቱ ስለሚሰሩ ስራዎች በገለፁበት ወቅት የጤና ዘርፍ ምርምርን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ እንደ ወረርሽኝ ያሉ የሚያጋጥሙ ችግሮችም ሆኑ በዘርፉ የሚገኙ የምርምር ውጤቶች ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ ያላቸው መሆኑ ነው። ስለሆነም አህሪ የሚያገኛቸው የምርምር ውጤቶች ጥቅማቸው አገራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ አለው ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒዩኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ደጅይጥኑ ሙላው ምርምር እና ሚዲያ በሚል ርእስ የተቋሙን የኮሚኒዩኬሽን እና ሚዲያ ስራዎችን እና ተግባራትን እንዲሁም የተከናወኑ ስራዎች ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የፎረሙ ዋና ዓላማ በምርምርና በሚዲያ መካከል ጠንካራ ድልድይ በመፍጠር ሳይንሳዊ ግኝቶችን ለኅብረተሰቡ ፈጣንና ጥራት ባለው መንገድ ማድረስ መሆኑን በመግለፅ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው አስታውሰዋል፡፡
በእለቱም ከየተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በምርምርና በሚዲያ አጋርነት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ የጤና ምርምር ከሀገር ሉዓላዊነትና ደኅንነት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የተባለ ሲሆን በመሆኑም እነዚህ የሆኑ የምርምር ውጤቶች ተገቢውን አዎንታዊ ተፅዕኖ ማምጣት እንዲችሉ የሚዲያ ተቋማት ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅንጅትና በባለቤትነት ስሜት በጋራ ሊሠሩ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/106861043/admin/dashboard/
Website:
https://ahri.gov.et/
Facebook: https://web.facebook.com/AHRIGovEt/?_rdc=1&_rdr #
Youtube: https://www.youtube.com/
Telegram:
https://t.me/ahriethiopia
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the school
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 17:00 |
| Tuesday | 08:00 - 17:00 |
| Wednesday | 08:00 - 17:00 |
| Thursday | 08:00 - 17:00 |
| Friday | 08:00 - 17:00 |