Awash 90.7 FM

Awash 90.7 FM

Share

Photos from Awash 90.7 FM's post 27/03/2026

በማኒፉክቸሪንግ ዘርፍ የስራ እድል ተፈጥሮልናል ሲሉ የመሀመድ በድሪ ማኒፉክቸሪንግ ሰራተኞች ተናገሩ።

መሀመድ በድሪ የአልባሳት ማኒፋክቸሪንግ ከተመሰረተ ስድስት አመታትን ማስቆጠሩም ተሰምቷል።

አዋሽ ኤፍ ኤም እንዳጣራው ድርጁቱ ከዋና ገዢዎቹ ጋር እንዲገናኝ የኢትዬጵያ ታምርት ንቅናቄ ጉልህ አስተዋፆ አድርጓል።

ጣቢያችን ይህን ያጣራው መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሚዲያን ከአምራች ኢንደስትሪ ጋር ያገናኛል በተባለው የጉዞ መርሀግብር ላይ ነው።

ድርጅቱ እንዳስታወቀው በአሁኑ ሰአት የሰራተኞች እጥረት የሰው ሀይል እንቅስቃሴውን ገድቦታልም ነው የተባለው።

Photos from Awash 90.7 FM's post 27/03/2026

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባደረገው ድጋፍ የሀይል መቆራረጥ መቀነሱን ካይት ማኑፋክቸሪንግ PLC አስታውቆናል።

ካይት ማኑፋክቸሪንግ PLC የሸገር ከተማ ቦታ በማመቻቸቱ ፣ በፉይናንስ አቅርቦት ደግሞ ብድር ከባንክ በመመቻቸቱ እንዲሁም በኢትዩጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አማካኝነት ባለው የሀይል አቅርቦት ስራዬን አከናውኛለሁ ሲል ነው ያሳወቀን።

ካይት ማኑፋክቸሪንግ PLC ከ ሁለት አመት በፊት መመስረቱን እንዲሁም በኢትዩጵያ ታምርት መድረክም ብዙ ደምበኞች ጋር መገናኘቱን ደግሞ ያሳወቁን የድርጅቱ የግዢ እና ሽያጭ ሀላፊ የሆኑት አቶ አሸናፊ ናቸው።

ከተግዳሮትም ጋር በተገናኘ ለገበያው አዲስ መሆን እና የጥሬ እቃ ግብአት እንደ ምክንያትነት ያነሱት ሀላፊው ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት ሁለት መቶ ሀያ ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉትም ለአዋሽ ኤፍ ኤም ጠቁመውናል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Ambassador Theatre
Addis Ababa