Arts Tv World

Arts Tv World

Share

10/07/2026

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ የኮኮቦች ሽልማት

10/07/2026

Arts Plus | No matter the weather outside, there’s always warmth in a great story. The countdown is almost over. We’re about to go live.

This rainy season, get ready to discover the very best of Ethiopian cinema on Arts Plus.

The Gateway to African Cinema. Download the App Now :

🌐 ድህረ ገፅ: https://artsplus.tv/

📱 Android (Google Play): https://play.google.com/store/apps/details?id=com.arifpay.artsplus

🍎 iOS (App Store): https://apps.apple.com/app/id6752890250

Photos from Arts Tv World's post 10/07/2026

ኢትዮጲያ ቡና አሠልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌን ለማስፈረም ከጫፍ ደረሰ

በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዓመቱን በሁለት አሠልጣኞች በመመራት በሊጉ ስምንተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁት ቡናማዎቹ አዲስ አለቃ ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል።

ከቀናት በፊት አሠልጣኝ ሳምሶን አየለን ያሰናበተው ቡና አንጋፋውን አሠልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌን ለማስፈረም የላቀ ድርድር ላይ ደርሷል ተብሏል።

አሠልጣኙ ከዚህ በፊት የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ከጅማ አባጅፋር ፣ መቀሌ 70 እንደርታ እና ኢትዮጲያ መድን ጋር ማሳካታቸው ይታወሳል።

ስኬታማው አሠልጣኝ አሁን ደግሞ ወደ መዲናይቱ ክለብ ለመድረስ የተቃረበ ሲሆን የኢትዮጲያ ቡና አመራሮች ባለፉት ጥቂት ቀናት ከአሠልጣኙ ጋር ስኬታማ ውይይት አድርገዋል የተባለ ሲሆን የክለቡ ፍላጎትም የሊጉን ዋንጫ ማሳካት እንደሆነ ለአሠልጣኙ አስረግጠው ተናግረዋል ተብሏል።

አሠልጣኙ ከጣቢያችን ጋር ባደረገው አጭር የስልክ ቆይታ ድርድሮች መቀጠላቸውን በማረጋገጥ ቀሪ የወረቀት ስራዎች እንደሚቀሩ ነግረውናል።

ተጨማሪ ይፋዊ መረጃዎች በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ ይደረጋሉ።

በዮናስ ግርማ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Bole Medhanialem, Awlo Business Center, 8th & 9th Floors, Cameroon Street
Addis Ababa