Brhanu

Brhanu

Share

03/06/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከተማ የተጀመሩ የክረምት በጎ ፈቃድ ልማት ስራዎችን ከገጠሩ ክፍል ጋር የማስተሳስር አካል የሆነውን የገጠር የኮሪደር ልማት አሰጀመሩ ፡፡

AMN - ግንቦት 26/2017 ዓ.ም

Photos from Brhanu's post 01/06/2025

አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት ይኖርባቸዋል
ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም

ሠራዊቱ በአካባቢው ሰላምን በማስጠበቅ የህብረተሰቡን የልማት ተግባራት ያለ እንቅፋት እንዲቀጥል የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ መሆነን የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገለፁ።

ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ይህንን ያሉት በኦሮሚያና በሲዳማ ክልል የዞን የመስተዳድር እና የፀጥታ በለድርሻ አካላት ጋር በአካባቢው ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ወይይት ባደረጉበት መድረክ ነው።

በውይይቱ ላይ የደቡብ ዕዝ በተሰማራበት አካባቢ ህዝብና መንግስት የሰጡትን ሰላም የማስፈን ተግባሩን ከመቸውም ጊዜ በላይ በአስተማማኝ ብቃት እየተወጣ ነው ለዚህም በየደረጃው ያለው የፀጥታ መዋቅሩ ቅንጅት ሠራዊቱ ተልዕኮን በሚፈፅምበት አካባቢ ውጤታማ ስምሪት ለማከናወን በአካባቢው ከሚገኙ የፀጥታ መዋቅሮችና የሥራ ሃላፊዎች ጋር በቅንጅት በመስራት አስተማማኝ ሰላም ማምጣት መቻሉን ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገልፀዋል።

አብሮ የመኖር እሴቶችን የመሸርሽሩና በአጎራባች አካባቢዎች ለግል የፖለቲካ ትርፍ ሲሉ በህብረተሰቡ ውስጥ መጠራጠር እና ጥቃቅን ግጭቶችን ለመፈጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የፀጥታ መዋቅሩ የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣትና የልማት እንቅስቃሴውን ማቀላጠፍ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊታችን ያለ እረፍት በምንም የማይተካ ውድ ህይወቱን እየሰጠ የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ የህዝብ አልኝታነቱን እያስመሰከረ ነው ምንግዜም ኩራታችን ነው ብለዋል።

ሠራዊቱ ለህዝብ ደህንነት ሲል ዋጋ እየከፈለ የአካባቢውን ሰላም ለማፅናት ቀን ከሌሊት የሰላማችን ዘብ ነው ያሉት የፀጥታ ሃላፊዎች ሰላም የማስፈን ጉዳይ ለመከላከያ ሠራዊቱ ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት መሆኑንና በተለይ የባለድርሻ አካላት የፀጥታ መዋቅሩን በማጠናከር የሠራዊታችንን ተልዕኮ መደገፍ እንደሚገባቸው አንስተዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Photos from Brhanu's post 30/05/2025

ተልዕኮን አደራጅቶ በመምራት የአመራር የመሪነት ጥበብ ማሳየት መቻል አለበት!
አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም

በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት መደበኛ የፓርቲ ተግራቶችና ወቅታዊ ተልዕኮዎች ላይ ውይይት አደረገ።

የአመራር የመሪነት ጥበብ በመላበስ ተልዕኮ በብቃት የመፈፀም አቅም በመጨመር የተቋም ግንባታ ስራ አጠናክሮ በመያዝ የተደራጀ የአመራር ስምሪት መስጠት እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም ገልጿል።

የአመራር የመፈፀም አቅም ከፍ እንዲል ሁለንተናዊ የድጋፍ አግባቦች አጠናክረን በመቀጠል ተልዕኮ ያለ ምንም መንጠባጠብ በመምራት የፓርቲያችን ተልዕኮ በአመራር ዲስኘሊን መፈፀም እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትልና የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ አስገንዝቧል።

የተደራጀ የአመራር ስምሪት መስጠት የጠንካራ መሪ መገለጫ ነው ያሉት በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ተልዕኮዎችን በእቅድ በመምራት አንፀባራቂ ድሎች ማስመዝገብ ይገባል ብሏል።

በመጨረሻም በመደበኛ የፓርቲ ተግባራቶችና በወቅታዊ ተልዕኮዎች ላይ አቅጣጫና የጋራ መግባባት በመስጠት ተጠቃለዋል።

Photos from Brhanu's post 30/05/2025

በመከላከያ ዋር ኮሌጅ የስትራቴጂክ አመራር ተማሪዎች የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 22 ቀን 20 17 ዓ.ም

ጉብኝቱ በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት ከተግባር ጋር ለማቀናጀት የሚያስችልና የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያጠናክር መሆኑም ተገልጿል፡፡

ጎብኝቱ በተቀናጀ ዘመቻ በስትራቴጂክ እና በፀጥታ ደህንነት ላይ በንድፈ ሃሳብ ያገኘነውን እውቀት ለመተግበር በሚያስችል መልኩ የተካሄደ ነው ያሉት ተማሪዎቹ የዘመኑን ዲጅታላይዜሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሰው ሀይልና ሎጂስቲክስን አስተሳስሮ ለመምራት እንዳሁም በተግባር የታገዘ የፅንሰ-ሃሳብ ትሞህርት መማር ለመከላከል ሠራዊታችንና ለሀገራችን ያለው ፋይዳ የጐላ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ባሻገር የተለያዩ የሀገሪቱን የመሰረተ ልማትና የመከላከያ ኢንዱስትሪ ተቋማት የጎበኙት ተማሪዎቹ በንድፈ ሃሳብ ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa