Finfinne Press
19/05/2026
በኤፕሪል 19 ቀን በማንቸስተር ሲቲ ስታዲየም ተካሂዶ በነበረው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ለተከታታይ ወራት ሊጉን ሲመራ የነበረው አርሰናል ፡ በማንቸስተር ሲቲ በገባበት ሁለት ጎል ተሸንፎ የወራት መሪነቱን ለሲቲ አስረከበ ።.....
እና የአርሰናል የዋንጫ ግስጋሴ የተገታ በመሰላቸው የአርሰናል ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ ድንጋጤ ተፈጠረ
በዚህ ወቅት ታዲያ በሜዳው ውስጥ የነበረው የአርሰናሉ ኮከብ ዴክላን ራይስ ፡ ለቡድኑ መሪ ማርቲን ኦዲጋርድ አንድ ነገር ሲናገር በቲቪ ካሜራዎች ላይ ታየ ።....
ራይስ የተናገረው ቃል " It's not done" የሚል ነበር ።.......
አርሰናሎች የነበራቸውን ሰፊ የነጥብ ብልጫ ቀስ በቀስ አጥተው ተስፋ በመቁረጥ ሜዳ ላይ ወድቀው በነበረበት ወቅት ዴክላን ራይስ ግን ነገሩ ገና እንደሆነ ፡ አሁንም የማሸነፍ እድል እንዳላቸው ፡ የሚያስረዳ ፡ ትልቅ ተስፋና ብርታትን የሚሰጥ መልእክት ያለው ንግግር ነበር የተናገረው ።......
ይህ የዴክላን ራይስ ንግግር ከተሰማ በኋላ ከእግር ኳስም አልፎ በብዙዎች ዘንድ መነቃቃትን እና ተስፋን የሚፈጥር ቃል ሆኖ ቆይቶ ዛሬ የአርሰናልን አሸናፊነት ተከትሎ ደግሞ እንደገና ቫይራል ሆኖ አምሽቷል ።
It's not done" ....
ራይስ ትክክል ነበር ። የአርሰናል ነገር ያለቀ ፡ ሽንፈቱ የተደመደመ አልነበረምና ፡ ከ22 አመታት ጥበቃ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማንሳት ችሏል ። ...
ይህ ከተሰማ ከደቂቃዎች በኋላም ዴክላን ራይስ በኢንስታግራም አካውንቱ የኛ ነገር ገና እንደሆነ ፡ ገና ብዙ ነገር እንደምናይ ነግሬያችሁ ነበር ፡ አሁን እደምንፈልገው ሆኖ ተጠናቋል ። የሚል ይዘት ያለው መልእክት አስተላልፏል ...
ከጥቂት ሳምንታት በፊት አርሰናላውያን ተስፋ ወደመቁረጥ እየገቡ ባሉበት ሰአት የተነገረው የዴክላን ራይስ ንግግር ስለኳስ ብቻ አይደለም ። ስለህይወትም ነው ።
It's not done !
Via wasihun tesfaye
19/05/2026
𝐂𝐎𝐍𝐆𝐑𝐀𝐓𝐔𝐋𝐀𝐓𝐈𝐎𝐍𝐒 𝐀𝐋𝐋 𝐀𝐑𝐒𝐄𝐍𝐀𝐋 𝐅𝐀𝐍𝐒! 🎉🎉
𝐀𝐑𝐒𝐄𝐍𝐀𝐋𝐒 𝐂𝐇𝐀𝐌𝐏𝐈𝐎𝐍𝐒 😍
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
19/05/2026
ዮሃን ክራይፍ ሶቅራጥስ ቢሆን እርሱ ፕሌቶ ነው፣
ወይንም ክራይፍን ፕሌቶ ነው ብንል ያለጥርጥር አሪስቶትል እርሱ ነው፣
ጉብዝናው ዋንጫ መሰብሰብ እና ማሸነፍ ብቻ አይደለም። እርሱ የማሸነፊያ መንገድም ነው፣ እርሱ የእግርኳስ aesthetic ነው። ደግሞም ብርቱ መምህር... እራሱ School of thought! የሀሳብ ጎተራ፣ የልህቀት ማዕከል፣ ከእውቀት ጎተራው ለሌሎች ቀለብ ለመስፈር ስስት የማያውቅ ቸር፣ ቅን ፈላስፋ ነው።
ተመልከት
ቪሳንተ ኮምፓኒ የእርሱ ደቀመዛሙርት ብቻ ሳይሆን የእርሱ ውጤት ነው፣
ሚካኤል አርቴታ የእርሱ ተማሪ ነው፣
በቀውሱ ዘመን ባርሳን ወደ ሊጉ አሸናፊነት የመለሰው ዠቪ ሄርናንዴዝ የእርሱ ፍሬ ነው፣
ኢንዞ ማሬስካስ የእርሱ ቅጥቅጥ አይደለምን፣
በሙኒክ ሳለ ዠቪ አሎንሶም ከእርሱ ብዙ ተምረዋል፣
እነዚህ ሁሉ የአዲሱ ዘመንና ትውልድ ብርቱ የእግርኳስ መሪዎች የሚጋሩት ዋና የቀለም አባታቸው ፔፕ ጋርዲዮላ ሳላ ነው።
ዓለማችን ከየቻቸው የክፍለዘመኑ ተላለቅ ሰዎች አንዱ ነው። ከዮሃን ክራይፍ በኃላ እግርኳስ ላይ አዲስ ቅመም እና ጠዕም የጨመረ ፈላስፋ ነው። አስተሳሰቡ ረቂቅ ነው። የሕይወት ዘዬው ያስደንቃል። ትጋቱ ለሚሊዮኖች ተምሳሌት እንዲሆን አስችሎታል።
ድብን ያለ ክራይፊስታ! ግን የክራይፍን ሙሉ ሀሳብ በመቅዳት ሳይሆን rebrand በማድረግ አዳዲስ እሳቤዎችን ወደ እግርኳስ አምጥተዋል። በአጭሩ ዘመናዊ የእግር ኳስ ታክቲኮችን redefine ያደረገ ታክቲካል ጂነስ ብቻ ሳይሆን እራሱ የዘመናዊ እግርኳስ ፍልስፍና innovator ነው። ያለ እሱ አእምሮ false nine, Controlling Space, Fluidity, Positional playing, inverted fullbacks የእግርኳስ ፋሽኖች ባልሆኑ ነበር።
በመሪነቱ ከአሌክስ ፈርጉሰን እሳቱን ተውሶ ከካርሎ አንቼሎቲ ውሃ የተዋሰ ብልሃተኛ መሪ ነው። እሳትም፣ ውሃም ሆኖ ይታያል። እንደ አርሰን ቬንገር ለእግር ኳስ ውበት ታምኗል። በአእምሮ ጥንካሬ ጆሴ ሞሪንሆን መሳይ ነው።
ሁለት ጊዜ Continental treble'ን በማሸነፍ ብቸኛው አሰልጣኝ ነው። በላሊጋ፣ ቡንደስሊጋ እና ፕሪምየር ሊግ ብዙ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ባለክብረ ወሰን ነው። በአሰልጣኝነት በትንሽ ዕድሜ ቻምፕዮንስ ሊግን ያሸነፈ ጀግና ነው። በፕሪሚየር ሊግ ለአራት ተከታታይ ዓመታት ያለርሱ ሻምፒዮን መሆን የቻለ የለም። መቶ ነጥብ ያስመዘገበ ብቸኛው አሰልጣኝም እርሱ ነው። 97 ነጥብ ሰብስበህ ሁለተኛ የምትወጣው እሱ ባለበት ሊግ ተፎካካሪው ስትሆን ብቻ ነው። በሊጉ በአንድ ሲዝን 106 ጎሎችን ያመረተስ ከእርሱ ሌላ ማን አለ? እስከአሁን 40 የሚደርሱ ዋንጫዎችን አሸንፏል። መቼስ አጃኢብ ነው!
ደግሞ ሲነሳበት ወደ ኒዉዮርክ ሄዶ ስለ ባራክ ኦባማ የምርጫ ቅስቀሳ ንግግሮች ያጠናል። ንግግሮቹን ይበልታል። ለኳስ አሰልጣኝነት ምን እንደምጠቅመው አንድዬ ይወቀው። ቴኒስ እና ቅርጫት ኳስ ውስጥ ያየውን ወደ ኳስ ሜዳ ለማምጣት የሚጥር እንደ ማርሴሎ ቢዬልሳ [ EL LOCO ] እብድ ብጤ ነው። ሌላኛው እብደቱ ከታሉኒስታ ሆኖ የዚዳን አድናቂ፣ በባርሴሎና ከሃዲ ተብሎ ከተፈረጀው ሉዊስ ፊጎ ጋር የተወዳጀ ደፋር ነው።
ነፍስ ሁሉ ከሀጢአት ትራቅ ይላል። ግን በአምላክ መኖር አያምንም። ኤቲስት ነው። ደግሞ ይፆማል። እሱም እንደ አገራችን ኤቲስቶች ቅዱስ ገብርኤልን ይፈራ ይሁን🤔 ብቻ ብዙ መመገብ ብዙ እንዳታስብ ያደርገሃል አይነት እሳቤ አለው። በተለይ ከጨዋታ በፊት መመገብ አይወድም። የገጠር ልጅ ነው። አሁን ግን ዘናጭ ከተሜ...
ኳስን ብቻ ሳይሆን ፖለቲካንም ይበልታለ። ስፔናዊነት በግድ ተጭኖብኝ እንጂ ስፔናዊ አይደለሁም የሚል የከታሉኛ ብሄርተኛ ነው። ስለ ከታሉኒያ አገርነት ይብሰለሰላል። አንድ ቀን ነፃ አገር ይኖረናል የሚል መፈክር ያሰማል። ስለከታሉኒያ ሪፐብሊክ ምስረታ ይቀሰቅሳል። በስፔን አንድነት ደጋፊዎች እጅግ የተጠላ ሰይጣን ነው። እርሱም እንዲህ ይላል... [ የሚበላውን ባጣ እንኳ የስፔን ብሄራዊ ቡድንን አላሰለጥንም ]
ደግሞም ሰው ነው፣ ለሰው የሚያዝን፣ ለሀቅ የሚቆም!
በፍልስጤም ጉዳይ በግልፅ ገለልተኛ አይደለሁም ከፍልስጤማውያን ጎን ነኝ ይላል። የእስራኤል ወዳጅ በሆነችው አገር የተያዘውን ካምፓኒ እየመራ የእስራኤልን እርምጃ በይፋ ይኮንናል። የዓለምን ዝምታ ይወቅሳል።
አርሰን ቬንገር፣
የርገን ክሎፕ፣
አሁን ደግሞ ፔፕ!
የማይተኩ የፕሪሚየር ሊግ አእምሮዎች!
በተለይ በተለይ ፔፕ!
ሌጋሲው ዘላለማዊ ነው!
በ - [ጥላዬ ያሚ] የተፃፈው ✍️
19/05/2026
🎁 የባሕረ ሰላጤው ሀገራት መሪዎች ባደረጉት ግፊት ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ #ኢራን ላይ ሊሰነዝሩት የነበረውን ጥቃት አዘገዩት።🥺
የ #አሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት በኢራን ላይ ሊሰነዘር ታቅዶ የነበረውን ወታደራዊ ጥቃት ማዘገያቸውን አስታወቁ። ጥቃቱን ያዘገዩት የባሕረ ሰላጤው ሀገራት መሪዎች ዋሽንግተን ለድርድር ዕድል እንድትሰጥ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ‘ትሩዝ-ሶሻል’ በተሰኘው በራሳቸው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ትላንት ባስተላለፉት መልዕክት፣ “እጅግ ትልቅ ጥቃት” ሲሉ የገለጹትን ወታደራዊ እርምጃ ለጊዜው ለማቆም የወሰኑት ከኳታሩ አሚር ታሚም ቢን ሐማድ አል ታኒ፣ ከሳዑዲው አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን እና ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትሱ ፕሬዚዳንት መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ከተወያዩ በኋላ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
ቴሌግራም፦
📌t.me/Brics4ethiopia
19/05/2026
🇮🇷 ኢራን በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳ እንዲሁም የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ የሚጠይቅ ሃሳብ አቀረበች
ኢራን በሁሉም ግንባሮች የተከፈቱ ጦርነቶች እንዲቆሙ እና ለደረሰባት ጉዳት ካሳ እንዲከፈላት የሚጠይቅ የስምምነት ሃሳብ አቀረበች።
አዲሱ የሰላም ዕቅድ በሊባኖስ ውስጥ የሚካሄደውን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች የሚደረጉ ጦርነቶች እንዲቆሙ፣ በኢራን አቅራቢያ የሰፈሩ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ እና በጦርነቱ ለደረሰባት ውድመት ካሳን እንዲከፈላት የሚጠይቅ መሆኑን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ቴህራን የሰላም ዕቅዱን በሚመለከት በሰጠችው የመጀመሪያ አስተያየት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካዘም ጋሪባባዲ ማዕቀቦች እንዲነሱ፣ እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ ንብረቶቿ እንዲለቀቁ አንዲሁም የአሜሪካ ባሕር ኃይል የጣለውን እገዳ እንዲያነሳ መጠየቃቸውን ኢርና የዜና ወኪል ዘግቧል።
የኢራን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ የቴህራን አዲሱ ዕቅድ ከዚህ በፊት ካቀረበችው እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ቆሻሻ” ሲሉ ውደቅ ካደረጉት ብዙም የተለየ አይደለም።
ትራምፕ ሰኞ ዕለት አቅደውት የነበረውን ጥቃት ያቆሙት ቴህራን ለዋሺንግተን አዲስ ሰላም ዕቅድ መላኳን ተከትሎ መሆኑን ተናግረው፤ የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ለመገደብ እና ከስምምነት ላይ ለመድረስ “በጣም ጥሩ ዕድል አለ” ብለዋል።
ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ “አሜሪካ እንዲሁም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ሊቀበሉት የሚችሉት ስምምነት ላይ ሊደረስ ይችላል” በማለት ጥቃቱ እንዲዘገይ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ሰኞ ዕለት ቴህራን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ እንዳታገኝ የሚያደርግ ስምምነት ላይ መድረስ ከተቻለ ደስተኛ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
ዘገበው የ ቢቢሲ ነው
ቴሌግራም፦
📌 t.me/Brics4ethiopia
•════••Reminder ••••════•
(⚠️ This content is only for educational, information, and historical awareness purposes.)
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
1000