MaBizplus

MaBizplus

Share

25/05/2026

በአንድ ሚሊየን ብር ምን መስራት ይቻላል?
በአንድ ሚሊየን ብር ምን መስራት ይቻላል?

ብዙ ጊዜ ብር ሞተ ሲባል እሰማለሁ በትክክል የሞተው ብሩ ነው ወይስ የገበያው መዋቅር፣ የማምረት አቅም እና የፋይናንስ ሲስተሙ ነው? መቸስ ብር ምንዛሬው ምንም ይሁን ምን የትም ዓለም ያለን ምርትም ሆነ አገልግሎት የመግዛት አቅሙ እኩል የሚሆንበት ነጥብ አለ Purchasing Power Parity (PPP) የሚሉት። ለምሳሌ አንድ ግራም ወርቅ ኢትዮጵያ ውስጥ 25,000 ቢሆን አሜሪካ በዚሁ መጠን በሚመነዘር ዶላር ይሸጣል። በዚህ ስሌት ሄደን ስለስራ እናውራ።

ተመልከቱ አንድ ቻይናዊ 43,000 የቻይና ዮዋን ቢኖረውና ቻይና ስራ ልጀምር ቢል ከ 9,000 በላይ የተመዘገቡ ጥቃቅን ግን አትራፊ ስራወች መስራት ይችላል። ኬንያ በዚህ ብር ከጥቃቅን እስከመካከለኛ ስራወች መጀመር ይቻላል።

ይሄንኑ ብር ወደአሜሪካ ውሰዱት ከስድስት እስከ ሰባት ሺዶላር ይሆናል። ምን ይሰራል? የሆነ ስራ አላችሁ እንበል በዚህ ብር ዳውን ፔይመንት(ቅድሚያ ክፍያ) አይናችሁ ያረፈበትን አዲስ መኪና ማውጣትና ኡበርም ስሩበት ሌላ ዘና ብላችሁ ከ5-7 ዓመት ቀሪውን ትከፍላላችሁ። ሌሎች በርካታ ሰራወችን መስራትም ትችላላችሁ። በተለይ የምግብ ዝግጅት፣ ወይም የእጅ ሙያ ካላችሁ ጥሩ መነሻ ነው። በእርግጥ አሁን የዓለም ኢኮኖሚው መሳከር ነገሩን እንደወሬው ቀላል ላያደርገው ይችላል።

ይሄንኑ ገንዘብ ወደኢትዮጵያ መንዝሩት አንድ ሚሊየን ብር ማለት ነው። ምን ትሰሩበታላችሁ? ለምን ሌላ አገር ያውም ግዙፍ የሚባሉ አገራት ጥሩ ስራ ሊያስጀምር የሚችል ገንዘብ አገራችን ላይ ጉልበት አነሰው?

ቻይና ውስጥ በ43,000 ዩዋን (1 ሚሊየን ብር ገደማ) በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን ስራዎች የሚገኙት አምራች ማሽኖች፣ ጥሬ ዕቃ እና የሎጂስቲክስ ሲስተሙ እጅግ ስለረከሰና ስለቀለጠፈ ነው። አሜሪካም ውስጥ በ6,000 ዶላር መኪና በዱቤ አውጥቶ በኡበር መስራት የሚቻለው ጠንካራ የብድር (Credit) ሲስተም ስላለ ነው። ኬንያ ክፍት እና ፈጣን የንግድ እንቅስቃሴ ስላላት ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ከብሩ በላይ የፋይናንስ ሲስተሙ ነው ያቀነጨረን። አስተያየት አላችሁ?

Photos from MaBizplus's post 25/05/2026

PUBLIC NOTICE | NOTICE ON FX DIRECTIVE AMENDEMENT AND RATIONALIZATION OF FEES AND CHARGES ON LETTERS OF CREDIT
MaBizplus
https://t.me/Mabizpluse

Want your business to be the top-listed Media Company in Debra Markos?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Sudan Street
Debra Markos