ETHIO FM 107.8
05/06/2026
ኢራን በሊባኖስ ስምምነት ላይ ጥርጣሬ እንዳላት ገለጸች
በሊባኖስ ውጊያው በመቀጠሉ ምክንያት ቴህራን በሊባኖስ ስምምነት ላይ ጥርጣሬ አሳድራለች ተብሏል
በአሜሪካ አሸማጋይነት የተኩስ አቁም ስምምነት ቢታወጅም፤ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትሰነዝረውን ጥቃት ቀጥላለች።
በዚህም ምክንያት እስካሁን የሟቾች ቁጥር 3 ሺህ5መቶ26 የደረሰ ሲሆን፤ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
የሄዝቦላህ መሪ ናኢም ቃሲም ስምምነቱን ‹‹ቀልድ›› ሲሉ ውድቅ ያደረጉት ሲሆን፤ እስራኤል ጥቃቷን ካላቆመች የሰሜን እስራኤል አካባቢዎች የጥቃት ኢላማ መሆናቸውን እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቀዋል።
በሌላ በኩል የኢራን ከፍተኛ መሪ አማካሪ የሆኑት ሞህሴን ረዛኢ በረቂቅ ስምምነቱ ላይ አሁንም ግልጽ ያልሆኑ ነገሮች እንዳሉ በመጥቀስ አሜሪካ በቴህራን ላይ ጫና ለመፍጠር እየሞከረች ነው ሲሉ ከሰዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦማን በሚገኝ ዋና የነዳጅ ተርሚናል ላይ በድሮን ጥቃት ምክንያት በተከሰተ ፍንዳታ የወጪ ንግድ ስራ መስተጓጎሉ ተገልጿል።
ሳራ ዮሐንስ
ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bole Medehanialem, Selam City Mall 5th Floor
Addis Ababa