Samvision eye Clinic

Samvision eye Clinic

Share

21/02/2018

የዓይን መነፅር እይታችንን እነዴት ያስተካክላል?
በመነፅር መስተካከል የሚችል የእይታ ችግር የምንላቸዉ በርቀት የማየት ችግር (Myopia) እንዲሁም በቅርበት የማየት ችግር (hypermetropia) ናቸዉ፡፡
በርቀት የማየት ችግር (Myopia):- የሚፈጠረዉ ምስል ብርሀን መቀበያ (retina) ጋረ ሳይደርስ በሚፈጠርበት ጊዜ ነዉ፡፡ ይህም ችግር ከዓይን በሌን (cornea) እስከ ብርሀን መቀበያ (retina) ያለዉ የዉስጥ ርዝመት ትልቅ ሲሆን ወይም የብሌን (cornea) ብርሀን ጨረርን የመስበር አቅሙ ከፍተኛ ሲሆን የሚፈጠር ነዉ፡፡ ይህን የእይታ ችግር በስርጉድ ሌንስ (concave lens) መስተካከል ይቻላል፡፡ ስርጉድ ሌንስ የብርሀን ጨረር በዉስጡ ሲያልፍ ይበትናል ይህም የዓይናችን ሌንስና ብሌን ምስሉን ብርን መቀበያ ላይ እንዲፈጥሩ ይረዳቸዋል፡፡
በቅርበት የማየት ችግር(hypermetropia) :-ችግሩ የሚፈጠረዉ ምስል ከብርሀን መቀበያን (retina) አልፎ ሲፈጠር ነዉ፡፡ ይህም የበሌን ብርሀንን የመስበር አቅም ከዓይናችን የውሰጥ ርዝመት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ወይም የዓይናችን የዉስጥ ርዝመት አነስተኛ ሲሆን ይፈጠራል፡፡ በእድሜ ከ 40 ዓመት በላይ ሲሆን ሌንሳችን ቅርፅ የመቀየር ችሎታዉን እያጣ ይመጣል ይህም ምስል በትክክል ብርሀን መቀበያ ላይ እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ ችግር ፕረስባዩፒያ (presbyopia) ይባላል፡፡ እብጥ ሌንስ (convex lens) ይህንን ችግር ለማስተካከል እንጠቀምበታለን፡፡ ብርሀን በእብጥ ሌንስ (convex lens) ዉስጥ ሲያልፍ ይሰበሰባል ይህም ሌንስንና ብሌንን በማገዝ ምስል ብርሀን መቀበያ ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ሳም ቪዝን ልዩ የዓይን ክሊኒክ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0944751322/0941545454 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

Photos 26/01/2018

Red-green color blindness is the most common type of color vision loss. Eye care professionals use the Ishihara Color Test to check for red-green color blindness — and it looks a little something like this.

Learn more about color blindness: https://nei.nih.gov/health/color_blindness/facts_about

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa