Ethio dish and Receiver Technology
21/08/2024
ጀርመናዊው አማካኝ ወደ ቀድሞ ቤቱ የሚመለሰው በነፃ ዝውውር ሲሆን እስከ 2025 ድረሰ የሚያቆየውን የ 1 አመት ኮንትራት ይፈራረማል .... በውሉ ላይም ለተጨማሪ 1 አመት ውሉን የሚያራዝምበት አማራጭ ተካቷል።
04/08/2024
በተከዜ ወንዝ በጀልባ ተሳፍረው ሲጓዙ የነበሩ 12 ሰዎች በድንገተኛ ጎርፍ ህይወታቸው አለፈ
| በዋግ ኽምራ ብሔረ-ሰብ አስተዳደር ከሰሃላ ሰዬምት ወረዳ ወደ ዝቋላ ወረዳ በተከዜ ወንዝ በጀልባ ሲጎዙ የነበሩ 12 ሰዎች በድንገተኛ ጎርፍ ሕይወታቸው አልፏል፡፡
ትናትንት ባጋጠመው አደጋ መነሻቸውን ሰሃላ ሰዬምት ወረዳ መሸሃ ከተማ እና ሰላዝጌ ቀበሌ አድርገው ወደ ዝቋላ ወረዳ ሀገረ- ሰላም ቀበሌ ዘመቁ ደብር ቀብር ለመድረስ ሲጓዙ የነበሩ 26 ሰዎች በጀልባ ተሳፍረው ተከዜ ወንዝን አቋርጠው በመጓዝ ላይ እያሉ ድንገት በተፈጠረ ጎርፍ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኃይሉ ግርማይ፤ እስካሁን ባለው መረጃ በአደጋው የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልፀው፤ 7 ሰዎች ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በጀልባው ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ 7 ሰዎች ደግሞ በዋና ራሳቸውን ማዳናቸውንም አቶ ኃይሉ አስረድተዋል።
ተከዜ ወንዝ የበርካታ ወንዝ ገባሮችን የሚቀበል በመሆኑ የውሃ መጠኑ ከፍተኛ ሊሆን ስለሚችል ማህበረሰቡ ግድቡ እስኪጠናቀቅ እንቅስቃሴውን በጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አቶ ኃይሉ መግለጻቸውን ከዋግ ኽምራ ብሔረ-ሰብ አስተዳደር ከሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የጀልባ ባለቤቶች ከአቅም በላይ በመጫን ሊደርስ ከሚችለው ጉዳት ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዋና አስተዳዳሪው በሰሃላ ወረዳ ተከዜ ወንዝ በጎርፍ አደጋ በደረሰው የሰዎች ህይወት ማለፍ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልፀው፤ ለሟች ቤተሰቦች እና ለመላው የብሔረሰብ አስተዳደሩ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።
17/05/2024
NOTCOIN መሸጥ የምትፈልጉ አዋሩኝ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa