Kambata Tube

Kambata Tube

Share

Photos from Kambata Tube's post 03/05/2026

አቤል ብርሃኑ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 በተለያዩ ሀገራት ጉብኝት በማድረግ እንቅስቃሴዎቹን በራሱ ዩቲዩብ የሚያጋራው አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) የአፍሪካን ጎልደን አዋርድስ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሽልማትን አሸንፏል፡፡

አቤል ብርሃኑ በዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዘርፍ ለመጨረሻ የቀረቡትን ሶስት አፍሪካዊ ዩቲዩበሮችን በመበለጥ ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡

ትናንት በኬኒያ መዲና ናይሮቢ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት በዩቲዩብ ከ2 ሚሊየን በላይ እንዲሁም በፌስቡክ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ያሉት አቤል ብርሃኑ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

አቤል ሽልማቱን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት÷ ”ኢትዮጵያን ወክለን ተሸልመናል” ሲል ደስታውን አጋርቷል፡፡

በርካታ ሀገራትን አቋርጬ የራሴ አህጉር አፍሪካ እውቅና ስትሰጠኝ የሚሰማኝ ደስታ ወደር የለውም ብሏል።

በአሮጌ ስልክ ካሜራ የሀሳብ ውጥኑን ሲጀምር ዓለምን የማየት እና ታሪኮችን የማካፈል ህልም እንደነበረው አስታውሶ÷ ህልሙ እንዲሳካ ከጎኑ ለነበሩ ተባባሪዎቹ ምስጋና አቅርቧል፡፡
Kambata Tube @ዋና ደጋፊዎችደጋፊዎች

02/05/2026

ቃሉ ፑቲክ በኢንስታግራም (Instagram) ታሪክ አዲስ ሪከርድ ሰበረ!

ኢትዮጵያዊው ቃሉ ፑቲክ (Kalu Putic) በኢንተርኔት ዓለም ላይ አስገራሚና ታሪካዊ የተባለለትን ስኬት አስመዝግቧል።

ቃሉ በኢንስታግራም ገጹ 1 ሚሊዮን ተከታዮችን (1M Followers) ለማግኘትና ከደጋፊዎቹ ጋር ደስታውን ለማክበር በዝግጅት ላይ ሳለ፣ ነገሮች ግን ከእሱ እቅድና ግምት በላይ ሆነዋል።

ባሳለፍነው አንድ ለሊት ብቻ በለቀቃት አንዲት "Viral" የሆነች ቪድዮ ምክንያት፣ የገጹ ተከታዮች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት በመጨመር ከ1 ሚሊዮን ተነስቶ 2.5 ሚሊዮን ላይ አልፏል።

በአሁኑ ሰዓትም ተከታዮቹ ቁጥር 2.8 ሚሊዮን ላይ ደርሷል።

እሱ ለ1 ሚሊዮን ተከታዮች የደስታ መግለጫ ዝግጅት ላይ እያለ፣ አድናቂዎቹ ግን በድንቅ የፈጠራ ጥበቡ ተማርከው ከ2.8 ሚሊዮን በላይ አድርሰውታል።

ይህ ስኬት ቃሉን በኢንስታግራም ገጽ ላይ ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን በማግኘት የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል።

በፈጠራ ስራዎቹ ዓለምን እያነጋገረ የሚገኘው ይህ ወጣት፣ የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ የዲጂታል መድረክ ላይ በጉልህ እያስጠራ ይገኛል።

ለቃሉ ፑቲክ እና ለጥበብ አድናቂዎች በሙሉ
እንኳን ደስ አላችሁ!

👏👏👏

© ጉርሻ page

🌴🌴🌴

Photos from Kambata Tube's post 02/05/2026

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Mekanisa
Addis Ababa
0000