Markos Tewodros - Mac
27/02/2026
You may not know what tomorrow holds, but you know who holds tomorrow.
09/01/2026
በወንድሞቹ የተከዳ፣ ለባርነት የተሸጠ፣ በሐሰት የተከሰሰና ወደ እስር ቤት የተጣለ ሆኖ ስናየው — የዮሴፍ ጉዞ በፍትሕ መጓደልና በመዘግት የተሞላ መስሎ ይታያል። ነገር ግን በእያንዳንዱ ወቅት እግዚአብሔር ከጀርባ በስራ ላይ ነበር፤ ባህርይውንና ማንነቱን እያቀና ለታለመለት ታላቅ ዓላማ እያዘጋጀው ነበር።
ጊዜው ሲደርስ ዮሴፍ ከእስር ቤት ወደ ቤተ-መንግሥት ተጠራ፤ ህልሙ እንዲሆንለት ብቻ ሳይሆን ህዝቡን ደግሞ ሊያድንበት። የዮሴፍ ታሪክ በእምነት እና በታማኝነት ለሚፀና በመከራ ውስጥ እንኳን ቢሆን እግዚአብሔር ለተስፋ ቃሉ ታማኝ እንደሆነ ያስታውሰናል። ከተስፋ ቃሉ ተነጥለን የጠፋን በሚመስለን ጊዜ እንኳን መንገዳችን የመለኮት መንገድ (direction) እንደሆነ እንድናምን እና እንድንፀና ያስተምረናል።
ወዳጄ እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው፤ አልተወህም፤ አይተውህም፤ አልጣለህም፤ ይጥልህም፤ በአንተ የጀመረውን ደግሞ ይፈጽመዋል ፤ ተስፋውም ከቶ አይጠፋም።
His promises never fail. 🙌✨
01/11/2025
ኤፊን እየሰማውት ነው ያደኩት። በልጅነት መዝሙር እንድወድ ካደረጉኝ ፊተኞች (my inspirations) ውስጥ ነው። ብቻ ቃላት የማይገልፀው ፍቅርና አክብሮት አለኝ ::
ነገ ጥቅምት 23 ደግሞ በሚሊንየም አዳራሽ ከቀኑ 7:00 ሰአት የሚጀምር ድንቅ የአምልኮ ድግስ አዘጋጅቶልናል::
አይቀርም 🙏
ወንጌል ያሸንፋል..✝️
19/05/2025
#ሞገስ (ተወዳጅነት) እና #ታታሪነት ከፍታ ላይ ሊያደርሷችሁ ይችላሉ - ነገር ግን የወጣችሁበት ከፍታ ላይ የሚያሰነብተው ስብዕና ብቻ ነው።
ፀጋና ስጦታዎቻችሁ በሮችን ሊከፍቱላችሁ ይችላሉ - ቆይታችሁ የሚወሰነው ግን በታማኝነት፣ በትህትና እና በአቋም ወጥነት ነው።
ስኬትን ስትፈልጉ ጎን ለጎን- ስኬታችሁን መሸከም የሚችል ስብዕናን ገንቡ።
👉 ለስኬት የምትጥሩትን ያህል በልባችሁ ላይ ስሩ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Address
Addis Ababa
1000