Seattle Academy,Kality -Addis Ababa
ዓለም አቀፉ የታዳጊ ልጃገረዶች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ
መስከረም 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዓለም አቀፉ የታዳጊ ልጃገረዶች ቀን ዛሬ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
ይህ ቀን በተባበሩት መንግሥታት ደረጃ በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን፣ በአዲስ አበባም በሲያትል አካዳሚ ትምህርት ቤት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂክማ ክሬዲን፣ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ወ/ሮ ምህረቴ ክርስቶስ፣ የአየርላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌዝሊ፣ የኦስትሪያ አምባሳደር ሲሞን ክናፕ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኮፊ ክዋሜ፣ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአካዳሚው ማኅበረሰብ ተገኝተዋል።
የዚህ ዓመት ጭብጥ፣ ታዳጊ ልጃገረዶች ራሳቸው ለውጥን የሚመሩ መሆናቸውን የሚያመላክት ነበር።
የዘንድሮ በዓል በሲያትል አካዳሚ ትምህርት ቤት ሲከበር፣ ታዳጊ ተማሪዎች የሰሯቸውን የፈጠራ ውጤቶች ለተገኙ እንግዶች በማቅረብና የተለያዩ መልእክቶችን በማስተላለፍ በድምቀት ተካሂዷል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/
#መናኸሪያሬዲዮ #መናኸሪያኤፍኤም #ራዲዮ #ሬዲዮ #መናኸሪያሬዲዮ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Addis Ababa