EyohaMedia

EyohaMedia

Share

21/03/2026

“ብርቱዋ ገበሬ በፈተና ላይ ናት›— የበረከት ገበሬዋ ወቅታዊ የጤና ሁኔታ መረጃ
አዲስ አበባ — መጋቢት 12 ፣ 2018 ዓ.ም ለብዙዎች የጥንካሬ ተምሳሌትና የሥራ ወዳድነት ተምሳሌት የሆነችው በረከት ገበሬዋ፣ በአሁኑ ወቅት በፅኑ ታማ በሕክምና ላይ እንደምትገኝ ታውቋል። "ወደ ሥራዋ ለምን አልተመለሰችም?" በሚል ከደጋፊዎቿ ለቀረቡ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሆን መረጃ ከቅርብ ምንጮች ለማግኘት ተችሏል።
በረከት ገበሬዋ በእስር ላይ በነበረችበት ወቅት በገጠማት የጤና መታወክ ምክንያት በፖሊስ ሆስፒታል ተኝታ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ በቂ የሕክምና እርዳታ ባለማግኘቷ በጤናዋ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል።
እንደ ምንጮቻችን ገለጻ፣ የበረከት ሕመም ከደም መረጋት (Blood Clotting) ጋር የተያያዘ ሲሆን ለህይወቷም አስጊ ነው ተብሏል::
ከእስር ከተፈታች በኋላ በተለያዩ የመንግሥት እና የግል ሆስፒታሎች የሕክምና ክትትል ስታደርግ ቆይታለች።
ይሁን እንጂ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ጤንነቷ በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ በአሁኑ ሰዓት በጦር ኃይሎች ሪፈራል ሆስፒታል ተኝታ በልዩ ባለሙያዎች ጥብቅ ክትትል እየተደረገላት ይገኛል።
የጤና ባለሙያዎቹ የሚያደርጉት ጥረት ተሳክቶ፣ በቅርቡ ሙሉ ጤንነቷ ተመልሶ ከሆስፒታል አልጋ እንድትነሳ ልባዊ ጸሎታችን ነው።
በረከት ገበሬዋ ለብዙ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የሥራ ክብርን ያስተማረች የቁምነገር ተምሳሌት ናት።
ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ በድል ተወጥታ፣ ፈጣሪ ሙሉ ጤንነቷን እንዲመልስላትና ዳግም ወደ የምትወደው የእርሻ ሥራዋ እንድትመለስ ከልብ እንመኛለን።
ፈጣሪ ምሕረቱን ይላክልሽ 🙏
ጉርሻ page

18/03/2026

"በቅርቡ ለታጨሁት የ Best Female Artist of 2026 ካሸነፍኩ ከ $55,000 ሽልማቴ ግማሹን ለቤተክርስቲያን እሰጣለሁ" አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ

መልካም ዕድል‼️

05/03/2026

'አስተናጋጆችም ህይወት አላቸው‼️

ፋሲካ አስተናጋጅ ናት ፡ ታዋቂው ዩትዩበር አይሾውስፒድ በአገራችን ካደረገው ጉዞ ልንረሳው ያልቻልነውን ጭውውት የሰጠችን ሙያዋንም አገሯንም ያስከበረች ጎበዝ ወጣት ነች።

የህይወቷ ከባዱ ጊዜ አባቷን ያጣችበት ቀን ነበር፡ ከአንድ አመት በፊት ማለት ነው።

ህይወት ይቀጥል የለ..የሃዘን ረፍቷን ጨርሳ ወደ ወደስራዋ ስትመለስ ሃዘኗ ግን ገና ከሷ ጋር አልጨረሰም ነበር።
እናም ቀን ላይ እንግዶቿን ምንም እንዳልተፈጠረ እየሳቀች አስተናግዳ ማታ ቤቷ ስትገባ አባቷን እያሰበች ታለቅሳለች ፡
ቀን ስትስቅ ያያት ተስተናጋጅ ምናልባት ትእዛዝ ቆየብኝ ብሎ ተቆጥቷት ይሆናል ወይም ውሃ ብርጭቆዬ ላይ አልቀዳሽም ብሎ ገላምጧት አመናጭቋት ይሆናልደ

ፋሲካ እንዲህ ትላለች

''እባካችሁ አስተናጋጆችን ተረዷቸው (ተረዱን)፡ እየሳቅን በፈገግታ ምናስተናግደው ለሙያችን ፍቅር እንጂ ምንም ችግር ሳይገጥመን ቀርቶ አይደለም። እኛም የራሳችን ህይወት አለን።''

ፋሲካ ልክ ናት

ምናልባት ዛሬ የተቆጣሃት አስተናጋጅ፣ ቤት ውስጥ የታመመች እናቷን አስቀምጣ አንተ ፊት እየሳቀች ይሆናል ፡
ምናልባትም ዛሬ ያመናጨቅሽው አስተናጋጅ የቤት ኪራይ በዝቶበት ጎዳና ላለመውጣት እየታገለ ይሆናል ፣
መስተንግዶ ሙያ ነው፡ አስተናጋጆችም ሰው ናቸው። ስለዚህ በመስተንግዶ ሲያስደስቱን እያመሰገንን ሲሳሳቱም በክብር እንንገራቸው፡ እነሱም እንደሰው የሚኖሩት ህይወት አላቸው‼️

Via- Getahun Assefa

Photos from EyohaMedia's post 04/03/2026

የሼህ አላሙዲ 4ሚሊዮን ብር እና የአዲስአበባ መስተዳድር የቤት ስጦታ‼️

ለ10 ዓመታት በአልጋ ላይ የቆየችው ሕፃን ብሌን አሸናፊ የ4 ሚሊዮን ብር ድጋፍና የመኖሪያ ቤት ተበረከተላት።

በአንጎል ውስጥ ውሃ መቋጠር እና ግፊት መጨመር (Hydrocephalus) ምክንያት ላለፉት 10 ዓመታት በአልጋ ላይ የቆየችው ሕፃን ብሌን አሸናፊ ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ ለምትታከምበት የ4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጎላታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሕፃኗ መኖሪያ ቤት ተገኝተው ድጋፉን ለወላጅ አባቷ አስረክበዋል።

የሕፃን ብሌን አባት ወጣት አሸናፊ በጽዳት ሠራተኝነት እየተገኘ እናት በሌሉበት ብሌንን፣ ታናሽ እህቷን፣ አካል ጉዳተኛ እህቱን እና አቅመ ደካማ እናቱን የሚንከባከብ ጠንካራ ወጣት መሆኑንም ከንቲባዋ ገልጸዋል።

ቤተሰቡ በአሁኑ ወቅት የሚኖርበት ቤት ለሕፃኗ ጤና አስቸጋሪ በመሆኑ፣ አስተዳደሩ የተሻለ የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ መወሰኑንም አስታውቀዋል።

ለሕፃን ብሌን አጠቃላይ የሕክምና ወጪ የሚውለውን 4 ሚሊዮን ብር የሸፈኑት ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ መሆናቸውን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች፣ ለባለሀብቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክትም ሕፃኗ አስፈላጊውን ሕክምና አግኝታ እንደ እኩዮቿ የምትቦርቅበትና ትምህርት ቤት የምትሄድበት ጊዜ ቅርብ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

Via- EBC

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Africa Avenue/Bole Road
Addis Ababa