Ethiopian programmer and Technology

Ethiopian programmer and Technology

Share

23/09/2020

=============
የኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርትን መማር ለምትፈልጉ
#5 የነፃ የኮምፒዩተር ሳይንስ መማሪያ ድህረገፆች
(ብዙ መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ ሼር ያድርጉት)
1) Stanford Engineering Everywhere(SEE)
ይህ ድረገጽ በአሜሪካ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የሚዘጋጅ ለተማሪዎችና ለባለሙያዎች ያለምንም ክፍያ ትምህርቶችን በኢንተርኔት የሚያሰራጭ ነው። ድረገጹ በሶስት ዋና ዋና ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን እነርሱም በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኤሌክትሪካል ምህንድስና ናቸው።
2) MIT Open እና Courseware
የማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት የሚያሰራጨው # የድረገጽ ዓይነት ሲሆን ለተማሪዎች ለመምህራን እንዲሁም ለባለሙያዎች
# የኢንተርኔት ትምህርትን ያለገደብ በነጻ የሚያቀርብ ነው። ይህ ድረገጽ የተለያዩ ኮርሶችን ባማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ሲሆን ሜካኒካል ምህንድስና፣ ሂሳብ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ እና ሌሎችም የትምህርት ዘርፎች ይሰራጩበታል።
3) GitHub.com
በአለም ላይ የኮዲንግ ምሳሌዎችን በቀላል አቀራረብ የሚያቀርብ እና ተማሪዎችን ከታወቁ የሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ጋር የሚያገናኝ ድህረገጽ ነው። እንዲሁም የተለያዩ ታዋቂ ባለሙያዎች ያበለጸጓቸውን ሶፍትዌሮች በቀላሉ በማቅረብ ተማሪዎች እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት የሚያስችል የድህረገጽ ዓይነት ነው።
4) W3 Schools
ይህ ድህረገጽ በተለየ መልኩ የፕሮግራሚንግ አሰራርንና የኮዲንግን ቋንቋ በተግባር አስደግፎ የሚያሳይ ሲሆን ቀላል ምሳሌዎችን ጥልቀት ካለው ቲቶሪያል ጋር እንደ AJAX፡ SQL፣ ASP፣ CSS፣ JAVA Script እና HTML ባሉ የኮዲንግ አሰራሮች ላይ ትምህርት ይሰጣል።
በተጨማሪም # በድረገጹ የሚቀርቡት የተለያዩ የመማሪያ ግብአቶች ተማሪዎችን በሁሉም ደረጃ የሚፈልጉትን መረጃ እንዲያገኙ በማስቻል ፕሮጀክታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ይረዳቸዋል።
5) Codecademy
አዳዲስ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሃሳቦችንና ቴክኒኮችን በቀላሉ የሚያቀርብ ሲሆን ራስን በራስ ለማብቃት የሚረዱ የተለያዩ ኮርሶችንም ያለምንም ክፍያ በማቅረብ የሚታወቅ ድህረገጽ ነው። በተለይ # ለኮዲንግ ጀማሪዎች አሰራሩን ከመነሻው እንዲረዱት ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ ክህሎቶችንና አሰራሮችን ለማግኘት ተመራጭ ነው።
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ # ሼር ያድርጉት..
የቴሌግራም ቻናል ይቀላልቀሉ
https://t.me/MuhammedComputerTechnology

Photos from Ethiopian Space Science Society's post 27/12/2019
Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa