EVEN Pharmacy

EVEN Pharmacy

Share

Photos from EVEN Pharmacy's post 07/09/2022

የጡት ካንሰር ለምን ይከሰታል?

የጡት ካንሰር ሁልጊዜም የሚከሰተው በ genetic abnormality (በዘረ-መል ችግር) ምክያት ነው። የዘረመል ችግር በዘር የተላለፈ ወይም በዘር ያልተላለፈ ሊሆን ይችላል።

በዘር በሚተላለፍ የዘረ-መል ችግር ምክንያት የሚከሰት የጡት ካንሰር ከ5-10% ያህል ብቻ የሚሆነው ነው። ይህም ማለት ትክክለኛ ያልሆነ (የተቀየረ) ጂን ከወላጅ ሲወረስ የሚከሰት ነው።

የቀረው 90% ያህል የጡት ካንሰር ግን በዘር የማይተላለፍ ነው። ይህም ማለት ታማሚው ጤነኛ ዘረመል (gene) ከቤተሰብ ወርሶ/ሳ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ያ ጤነኛ gene ወደ ካንሰር አምጪነት ሲቀየር ነው

ይህም ማለት የጡት ካንሰር ካለባቸው 10 ሴቶች ውስጥ አንዷ ብቻ ናት በዘር የሚተላለፍ የጡት ካንሰር የሚኖርባት ሌሎቹ ዘጠኙ በቤተሰብ የጡት ካንሰር ታሪክ የሌለባቸው ነው የሚሆኑት።

ይህንን ማወቅ/ መረዳት በዘር ወይም በቤተሰብ የጡት ካንሰር ስለሌለብኝ እኔን አይዘኝም ብለን እንዳንዘናጋ ይረዳናል።

ለጡት ካንሰር ተጋላጭ የሚያደርጉ ነገሮች
- ማንኛውም ሰው ወንድም ሆነ ሴት በጡት ካንሰር የመያዝ እድል አለው
- አንዳንዶች ከሌሎች ሰዎች በተለየ ከፍ ያለ ተጋላጭነት ሊኖራቸው ይችላል

በሃገራችን የተደረጉ ብዙ ጥናቶች ባይኖሩም በሌላው አለም ግን ከስምንት ሴቶች አንዷ በጡት ካንሰር ትያዛለች

ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲወዳደር በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው በጣም አነስተኛ ነው። ከ800 ወንዶች አንድ ወንድ ላይ ይከሰታል። ይህ ቁጥር ግን የሚናቅ አይደለም። ስለዚህም ወንዶች ከሴቶች እኩል ስለ ጡት ካንሰር በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል።

የጡት ካንሰር ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች (risk factors)

1- እድሜ (ከ50 አመት በላይ መሆን)

2- የተቀየረ ጂን ከቤተሰብ መውረስ (BRCA1እና BRCA2 የሚባሉ ጂኖች)

3- የተራዘመ የወር አበባ ጊዜ: የመጀመርያ የወር አበባ ከ12 አመት በታች ማየት እና የወር አበባ የቆመበት ጊዜ ከ55 አመት በኋላ መሆን

3- የጡት የተፈጥሮ አይነት (በህክምና ቋንቋ dense breast የምንለው)

4- ከቤተሰብ አባላት ውስት የጡት ወይም የዘር ፍሬ ካንሰር (ovarian ca) ታሪክ መኖር

5- ለሌሎች በሽታዎች የሚሰጥ የጨረር ህክምና (radiation therapy)

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት እኛ በጥረታችን ልንቀይራቸው የማንችላቸው የጡት ካንሰር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ሲሆኑ ከታች የተዘረዘሩት ግን መቀየር የምንችላቸው ነገሮች ናቸው

1- የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ

2- ከመጠን ያለፈ ውፍረት

3- ኢስትሮጅን እና ፕሮጄተሮን የተባሉ ሆርሞኖች የያዙ መድሃኒቶችን መውሰድ

4- የመጀመርያ ልጅን ከ30 አመት በኋላ መውለድ እና ጡት አለማጥባት

5- አልኮሆል መጠጦችን መጠጣት

6- ማጨስ

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ነገሮች ተጋላጭነትን ይጨምራሉ ማለት ነው እንጂ ቀጥታ ከጡት ካንሰር ጋር ይያያዛሉ ወይም የጡት ካንሰር ያመጣሉ ማለት አይደለም።

አንዲት ሴት ሁሉም ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁነታዎች (risk factors) ኖረዋት የጡት ካንሰር ላይዛት ይችላል። በተቃራኒው ደግሞ ምንም አይነት የሚታወቅ risk factors የሌላት ወጣት ሴት ደግሞ የጡት ካንሰር ሊይዛት ይችላል።

ስለዚህም ማስቀረት ወይም መቀነስ የምንላቸውን ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ማስተካከል, በየጊዜው ጡታችንን መፈተሽና ከሃኪም ጋር በመመካከር ምርመራዎችን ማድረግ ብቸኛው መፍትሄ ነው።

ዶ/ር ቤተልሄም መዝገቡ ፤ ራዲዮሎጂስት ፣ የጡት እና የሴቶች ኢሜጂንግ ፌሎው::

Want your business to be the top-listed Health & Beauty Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Yerer-Goro
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 22:00
Tuesday 09:00 - 22:00
Wednesday 09:00 - 22:00
Thursday 09:00 - 22:00
Friday 09:00 - 22:00
Saturday 09:00 - 22:00
Sunday 10:00 - 22:00