Semera-Logya Communication Office

Semera-Logya Communication Office

Share

Photos from Semera-Logya Communication Office's post 11/06/2026

የሰመራ-ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ልምድ ልውውጥና የሥራ ጉብኝት አካሄደ።

​ሰመራ፣ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰመራ-ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር አህመድ ኑር ሳሊም፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመገናኘት የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ተገለጸ።

​ክቡር ከንቲባው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም የወንዝ ዳርቻና ኮሪደር ልማት አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል። በጉብኝቱ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን በአካል በመመልከት፣ በገቢ አሰባሰብ እና በዘመናዊ የኮሪደር ልማት ስራዎች ዙሪያ ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ተችሏል።

​ኢንጂነር አህመድ ኑር ሳሊም እንደገለጹት፣ ጉብኝቱ ለሰመራ-ሎጊያ ከተማ የወደፊት ሁለንተናዊ እድገትና ለከተማዋ የተቀናጀ የልማት እቅድ አፈፃፀም ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ነው። የከተማ አስተዳደሩ በከተማ ልማት ዘርፍ እየታዩ ያሉ የለውጥ ስራዎችን በመቀመር ወደ ስራ እንዲገባ መነሳሻ የፈጠረ መሆኑንም አክለዋል።

​በውይይቱ ማጠቃለያም፣ የሰመራ-ሎጊያ ከተማ አስተዳደር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀጣይነት ያለው የልምድ ልውውጥ ለማድረግና በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ማዕቀፎች ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል። ይህ የጋራ ስምምነት የሁለቱን ከተሞች የልማት ትስስር እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል።

​የሰመራ-ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
Semera-Logya Communication Office
Afar Communication Bureau

Photos from Semera-Logya Communication Office's post 10/06/2026

የጉባ ብሥራት ጅማሮ፡ ሜጋ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ የሚያፋጥኑበት አዲሱ ምዕራፍ
**********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ማዕቀፍ ያስተላለፉት ታሪካዊ መልዕክት እና ያወጇቸው ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ጅማሮ ብሥራት ዛሬ በላብ እና በጥናት ወደ ተጨባጭ ተግባር እየተቀየሩ ይገኛሉ።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በልዩ ትኩረት ከጠቀሷቸውና ‘የጉባ ብሥራት’ ተብለው ከሚጠሩት ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል ግዙፉ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ እና የተፈጥሮ ጋዝ ማቀነባበሪያ ፕሮጀክቶች ዛሬ በተግባራዊ የሥራ ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ።

በመሠረተ ልማት ዘርፍ ኢትዮጵያን የአፍሪካ አዲሱ የአቪዬሽን እና የንግድ ማዕከል ለማድረግ የታለመው ግዙፉ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት በመንግሥት ሙሉ ትኩረት ግንባታው ተጀምሯል።

ይህ ታላቅ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት ከ100 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን የማስተናገድ ግዙፍ አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ የሀገራችንን የቱሪዝም ዘርፍም ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት በዘላቂነት ለመደገፍና በምግብ ዋስትና ራስን ለመቻል ታልሞ የተጀመረው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታም በተቀናጀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ክልል ጎዴ በመገኘት የዚህን ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት የክንውን ሂደት መጎብኝታቸው ለመርሃ ግብሩ የተሰጠውን ከፍተኛ ሀገራዊ ትኩረት ያሳያል።

የተፈጥሮ ጋዝ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የመጀመሪያው ምዕራፍ በይፋ ተመርቆ ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ የዚሁ ፕሮጀክት ግዙፍ ማስፋፊያ አካል የሆነው ቀጣይ ሥራም በስኬት ተጀምሯል፡፡

ይህ ሜጋ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በኢነርጂ እና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ መሸጋገሯን የሚያሳይ ታሪካዊ እመርታ ነው።

ፕሮጀክቱ ሀገራችን ለዘመናት ለነዳጅ እና ማዳበሪያ ምርቶች ስታወጣ የነበረውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ፣ ወደ ዘላቂ እና ለአካባቢ ተስማሚ የኃይል አማራጮች እንድትሸጋገር ያደርጋታል።

የዚህ ታላቅ የሽግግር ውጤት ደግሞ አሁን ዓለም በመካከለኛው ምሥራቅ ባለው ጂኦፖለቲካዊ ግጭት እና ቀውስ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ በገጠማት በአሁኑ ወቅት በትራንስፖርት ዘርፋችን ላይ ትልቅ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ እፎይታን እየፈጠረ ይገኛል።

ከተለምዷዊ የነዳጅ ፍጆታ ወጥተው በአረንጓዴ ኢነርጂ እና በሀገር ውስጥ በሚመረት የተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ የሕዝብ ማመላለሻ እና የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ገበያ በስፋት መግባታቸው የኢትዮጵያ የኢነርጂ ፖሊሲ በተግባር እየተቀየረ ለመሆኑ ቁልፍ ማሳያ ነው።

ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ ምዕራፎች ጀምሮ የተነሱት ታላላቅ ሀገራዊ ራዕዮች በቃል ደረጃ ብቻ የቀሩ ሳይሆኑ በተጨባጭ የልማት ውጤቶች መሬት ላይ እየተገለጡ መሆናቸውን ተረጋግጧል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ከኃይል ማመንጨት ባለፈ የኢነርጂ ሽግግርን፣ የኢንዱስትሪ ዕድገትን፣ የግብርና ራስን መቻልን እና የመሠረተ ልማት አብዮትን በአንድ ላይ እውን የምታደርግበትን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በቁርጠኝነት እየጻፈች ትገኛለች።

በሃና ምንዳሁን

Photos from Semera-Logya Communication Office's post 10/06/2026

በአፋር ክልል ኪልበቲ ራሱ በራህሌ ወረዳ ሃለ-ጉቢ ቀበሌ የተቀሰቀሰው ስደድ እሳት መቆጣጠር አልተቻለም የበራህሌ ወረዳ አስተዳደር

ሰመራ፣ ስኔ 03 ፣ 2018 (አፋ.ብ.መ.ድ)

በአፋር ክልል ኪልበቲ ራሱ ዞን በበራህሌ ወረዳ ሃለ-ጉቢ ቀበሌ፣ በደት-ጋራብ (አፍዓዶ ጓሎ እና ኤሊ-ጋራብ) አካባቢ የተቀሰቀሰው ስደድ እሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር ከወረዳው ማህበረሰብ አቅም በላይ ሆኗል የወረደው አስተዳደር አቶ አሊ ሁሴን

የአካባቢው ማህበረሰብ እና አመራሮች በተቀናጀ መልኩ እሳቱን ለማጥፋት የሚችሉትን ጥረት እያደረጉ ቢሆንም እሰከሆን እሳቱን መቆጣጠር አለመቻሉን ገልጿል

አካባቢው በለው የመንገድ ችግር ምክንያት፣ የውሃ አቅርቦት ማቅረብ ባለመቻሉ መሆኑን እና አካባቢው በጫካና በደን የተሸፈነ በመሆኑ እሳቱን በሰው ኃይል ብቻ ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኗል ብሏል

ይህ እሳት በአካባቢው ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ እንስሳት እና የማህበረሰቡ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር በመሆኑ ሁሉም አጋር አካላት ትኩረት እንዲሰጥ ስል ጥሪ አቅርበዋል

Afar Mass Media Agency
Semera-Logya Communication Office

Photos from Semera-Logya Communication Office's post 10/06/2026

የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ከዩኤንኤፍፒኤ (UNFPA) የሀገር ተወካይ ጋር በጤናው ዘርፍ የትብብር ስራዎችን ለማጠናከር መከሩ
​ሰመራ፣ አፋር ክልል – ሰኔ 3፣ 2018 ዓ.ም።

​የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሐጂ አወል አርባ፣ የተባበሩት መንግሥታት የህዝብ ተቋም (UNFPA) የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑትን አቶ ኮፊ ኩዋሜን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በሁለቱ ወገኖች መካከል የተካሄደው ይህ ከፍተኛ ደረጃ ውይይት፣ በክልሉ የጤና አገልግሎትን ማሻሻል እና በክልሉ መንግሥት እና በድርጅቱ መካከል ያለውን የትብብር ግንኙነት ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።
​በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች በክልሉ የጤና ዘርፍ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል።

ከነዚህም መካከል፦
​የእናቶችና የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ማሳደግ፣
​በሩቅ አካባቢዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣
​በክልሉ በመተግበር ላይ የሚገኙ የሞባይል ጤና ጣቢያ ፕሮግራሞችን ማጠናከር፣ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

​ፕሬዝዳንት ሐጂ አወል አርባ፣ የአፋር ክልል ህዝብ በተለይም ሴቶች፣ ህፃናት እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች የጤና ፍላጎቶችን ለማሟላት የተቀናጀ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል። የክልሉ መንግሥት የጤና ውጤቶችን ለማሻሻል እና አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶች ያልደረሱባቸው አካባቢዎች እንዲዳረሱ ቁርጠኛ መሆኑን በዚሁ ወቅት ገልጸዋል።

​በተጨማሪም ውይይቱ የእናቶችን ሞት የመቀነስ፣ የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን የማሻሻል እና ማህበረሰቡ ለጤና ተቋማት ያለውን ተደራሽነት ለመጨመር በሂደት ላይ ያሉ ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ አዳዲስ እድሎች ላይ መክሯል።

Semera-Logya Communication Office

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Semera
Addis Ababa
0000